አኩ ኢብን አፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
በአፋር ክልል በኡንዳ ፎኦ ከተማ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊሶች ከሶማሌው ዒሳ ጎሳ ጋር የተዋጉ ሲሆን በግጭቱም 3 ሰዎች ሲሞቱ ከ20 በላይ መቁሰላቸው ታውቋል። ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ አፋር ኡንዳ ፎኦ ከተማ የሚኖሩ የሶማሌ ተወላጅ የኢሳ ጎሳዎች በመጀመሪያ ከፈደራል ፖሊሶች ጋር የተዋጉ ሲሆን ከፖሊስ አንድ ሰው ሲሞት ወደ 18 የሚጠጉ ቆስለዋል።
በኋላ ላይ የአገር መከላከያ ሰራዊት ሃይል የደረሰ ሲሆን ከኢሳዎች ሁለት ሰዎች ገድሏል። ሁለት የመከላከያ አባላት ደግሞ በከፉኛ ቆስለዋል። የውግያው መነሻ የሆነው በቅርብ ጊዜ በፈደራል ጉዳዮች የተወሰነው የመሬት ጉዳይ ሲሆን መሬቱን ለአፋር ክልል መንግስትና ህዝብ ለማስረከብ የተወሰነው ውሳኔ መሆኑን ምንጮቻችን ዘግበዋል።