የህወሓት ፖሊሶች ጋዘጠኞቹን ኣግቶ፣ ፈትሾ፣ ኣንገላትቶ ለቋቸዋል።
ትናንት ሰኞ 19/ 01 / 2007 ዓ/ ም ለስራ ጉዳይ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በኣንድ ጣልያን የሚገኝ ቴሌቭዥን ጣብያ የሚሰሩ 4 ጣልያናውያን ጋዜጠኞችና ኣንድ ሌላ ኣገር ጎብኚ ጣልያናዊ ከሁለት ኣብሯቸው የሚሰሩ ኢትዮዽያውያን ጋራ ወደ ተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች የጎበኙ ሲሆኑ እገታው ያጋጠማቸው ወደ ኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ, ሩባ ፈለግ ቀበሌ የዓረና ኣባል የሆነው ኣቶ ሕድሮም ሃይለስላሴ መኖርያ ቤት በመሄዳቸው ነው።
የወረዳው ፖሊስ መኪናቸው ወደ ፖሊስ ጣብያ እንድት ሄድ በማዘዝ ከኣስተዳዳሪዎች ጋራ በመሆን ቪድዮና ፎቶ ካሜራዎቻቸው እንዲፈተሹ በማድረግ፣ ፓስፖርታቸው ፎቶ ኮፒ በማድረግ፣ ወደ የዓረናው ኣባል ለምን ጉዳይ እንደገቡ በመጠየቅና ታስረው እንዲያድሩ ብሎው ውሳኔ ኣስተላልፈው ነበር።
ኣምስቱ ታጋቾች ኣዲስ ኣበባ ወዳለው የጣልያን ኢንባሲ ደውለው በመነጋገር ማታ 2:30 ኣከባቢ ሊለቀቁ ችለዋል።የህወሓት መንግስት እነዚህ ጋዘጠኞች ኣግቶ፣ ፈትሾ፣ ኣንገላትቶ ከፌደራል መንግስት በተሰጠው ትእዛዝ ሊለቃቸው ተገደዋል።