የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በኋላ የፌዴራል ደህንነት ዋና ባለስልጣን የሆኑት የሕወሐት ፖሊት ቢሮ ባል አቶ ፀጋዬ በርሄ በመቀሌ ልዩ ስሙ “አፕርታይድ መንደር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ያስገነቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አረጋገጠዋል። 10 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደፈጀ የሚነገርለት የአቶ ፀጋዬ ቪላ ለአንድ ባለሃብት 25ሚሊዮን ብር እንደተሸጠ ቢነገረም በትክክል የተሸጠበትን ዋጋ ማወቅ እንዳልተቻለ ምንጮቹ አስታውቀዋል። ፀጋዬ በርሄ የቅዱሳን ነጋ ባለቤት ሲሆኑ ቅዱሳን የስብሃት ነጋ ታናሽ እህት ናቸው።የመቀሌ ነዋሪ “አፓርታይድ መንደር” የሚል ስያሜ በሰጠው በዚህ ቦታ ከአቶ ፀጋዬ በርሄ በተጨማሪ አቦይ ስብሃት ነጋ በራሳቸውና በመጀመሪያ ልጃቸው ስም ሁለት ቪላዎችን ሲያስገነቡ ቴዎድሮስ ሃጐስ፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጎበዛይ ወ/አረጋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ ዘመናዊ ቪላዎችን ካስገነቡ የሕወሐት ባለስልጣናት ሲጠቀሱ ኪሮስ ቢተው በሰባት ሚሊዮን ብር ወጪ በዚሁ ስፍራ ያስገነቡትን ቪላ ከ9 ወራት በፊት መሸጣቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል። በሌላም በኩል የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበሩት የሕወሐት አባል ጄ/ል አበበ ተ/ሃይማኖት (በቅፅል ስማቸው ጆቤ) በቦሌ ያስገነቡትን ቪላ በ24 ሚሊዮን ብር መሸጣቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።
↧
የፀጋዬ በርሔ ቪላ ተሸጠ –ከኢየሩሳሌም አረአያ
↧