ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ
ምግቦች ለአካላዊ ጤና ስለሚሰጡት ጠቀሜታ ብዙ ተብሏል፡፡ በርካታ ጥናቶችም በየእለቱ ለንባብ ይበቃሉ፡፡ ምግቦች ድብርት፣ ጭንቀትንና ተመሳሳይ ስነልቦናዊ ችግሮችን ለመቀነስና ደስተኛነታችንን ለመጨመር እንደሚያስችሉ በተለያዩ የጥናት ቡድኖች የተካሄዱ ምርምሮች ይገልፃሉ፡፡ ደስታን ከሚያርቅ ስሜት (bad mood) ሊያላቅቁን ይችላሉ የተባሉ ሰባት ምግቦችን እነሆ ብለናል፡፡
የስራ ጫናን ተከትሎ ለሚመጣ ድካም (ስትረስ) ቸኮሌት
የስራ መውጫ ሰዓት ደርሷል-ርቦዎታል፣ ደክሞዎታል በቶሎ መውጣት አለብዎ፡፡ ነገር ግን አለቃዎ አንዲት ውለታ እንዲውሉላቸው ይጠይቆታል. . . እንቢ አይሉ ነገር፡፡ ድካምዎ እየተባባሰ ነው፡፡ ከዚህ ስሜት በፍጥነት የሚያወጣዎ ነገር ያስፈልጎታል፡፡ በቢሮዎ አካባቢ ቸኮሌቶችን የሚያስቀምጡ ከሆነ አውጥተው የሚበሉበት ጊዜ ነው፡፡
ኤክስፐርቶች በተለይ ጠቆር ያለ ቀለም ያለው ቸኮሌት (dark chocolate) በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን የስትረስ ሆርሞኖች እንዲቀንሱ እንደሚረዳ በስዊዘርላንድ የተደረገና touna of proteome research ላይ ለንባብ የበቃ አንድ ጥናት ጥቂት ጠቆር ያለ ቸኮሌት መመገብ cortical እና catecholamines የተሰኙትን የስትረስ ሆርሞኖች አቅም ለመቀነስ ያስችላል፡፡
ለሃሳብ መበታተን- የስፒናች ሳላድ
‹‹ሃሳብዎ እየተበታተነ ማተኮር አቅቶታል? አይኖን ከፍቶ ማየትስ ከብዶታል? እንግዲያው ቡናን ይተዉና በምትኩ የስፒናች ሰላጣ ይመገቡ›› ይላሉ ዶ/ር ጆአን ጎልዶፍ ‹‹red light, green light, eat right›› የተሰኘው መፅሃፍ ደራሲ፡፡ ፎሊክ አሲድ ወይም ፎሌት ሰውነታችን የhomocysteine መጠንን ዝቅ እንዲያደርግ ያግዘዋል፡፡ ይህ ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ በከፍተኛ መጠን ከተገኘ የደም ቧንቧዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችልበት ሁኔታ አለ፡፡ በተጨማሪም ወደ አንጎል የሚጓዘው ደምና ንጥረ ነገሮች ላይ መስተጓጎል ሊፈጥር ይችላል፡፡ ይህ የተዛባ የደም ዝውውር ቀርፋፋና ዝንጉ ያደርጎታል›› በማለት ዶክተሯ ንጥረ ነገሩ በሰውነታችን ላይ ሊያደርስ ስለሚችለው ችግር ያብራራሉ፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ በፎሌት (ፎሊክ አሲድ) የበለፀጉ ምግቦችን ይመገቡ፡፡ ስፒናችና ሌሎችም ባለቅጠል አረንጓዴ ተክሎች እንዲሁም ድንች፣ በቫይታሚን የበለፀገ ዳቦ፣ ባቄላ አተርና እንጉዳይ እንዲመገቡ ዶክተሯ ይመክራሉ፡፡
ባልተለመደ መልኩ ቁጣ ቁጣ ይልዎታል? አፕል በኦቾሎኒ ቅቤ ይመገቡ
ልጆችዎ ላይ ሳያስቡት ይጮሁባቸዋል? በትህትና ሊያናግርዎ የሚሞክርን ሰው ጥምብርኩሱን ያወጣሉ?. . . ባጠቃላይ በትንሹ ግንፍል ይላሉ? ይህ ስሜት crankiness ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሰውነትዎ ተጨማሪ ኃይል እንደሚያስፈልገው ያሳያል፡፡
ይህ ኃይልም በአግባቡ መሞላት ይገባዋል፡፡ ከአንድ ሰዓት በኋላ የደም የስኳር መጠንዎ እንዲቀንስ የሚያደርጉ ምግቦችን ያስወግዱ፡፡ ይህን ስሜት ስስ መሆንን ለማስወገድ የተለያዩ ምግቦችን ይመገቡ፡፡
ዶ/ር ጎልዶፎ በካርቦሃይድርትስና በፕሮቲኖች ወይም ፋት ያለባቸውን ምግቦች ቀላቅሎ መመገብ ጠቃሚ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ‹‹ካርቦሃይድሬትስ በፍጥነት ስራ ላይ የሚውል አቅም በመስጠት በኩል የተዋጣላቸው ናቸው፡፡ በዚህ ላይ ጥቂት ፋት ወይም ፕሮቲን መቀላቀል የምግብ መፋጨት ሂደቱን በማዘግየት የደም ስኳር መጠንዎ ሁልጊዜ የተረጋጋና የማይዋዥቅ እንዲሆን ያደርጋል›› ይላሉ፡፡ ምግቦችን ቀላቅሎ ስለመውሰድ ሲነሳ ጥሩ ምሳሌ ሆኖ የሚቀበው አፕል ከኦቾሎኒ ቅቤ ጋር የሚወሰደው ነው፡፡ አፕሉ ካርቦሃይድሬትስን የኦቾሎኒ ቅቤው ደግሞ ጤናማ ፋት ይሰጠናል፡፡ እነዚህን በኃይል የተሞሉ ምግቦች ቀላቅሎ በመመገብ ለሰዓታት የሚዘልቅ አቅም ማግኘት ይችላሉ፡፡
አሣ- ለጭንቀት
ስለ ፋይናንስ አቅምዎ፣ ስለትዳርዎና ስለልጆችዎ አብዝተው ይጨነቃሉ?ጭንቀትና ስጋት ቀንዎን እያበላሽብዎ ከተቸገሩ በተቻለ መጠን ከሰዎች ጋር ለማሳለፍ ይሞክሩ፡፡ ምሳ ከስራ ባልደረባዎ ጋር ለመብላት ይሂዱ፡፡ ምግብዎንም ከዚህ የስሜት ቀውስ ሊያወጣዎ ይችላል፡፡ በተለይ በኦሜጋ3 የበለፀገውን ሳልመን የተባለውን የአሳ ዝርያ ይመገቡ፡፡ ‹‹ኦሜጋ3 ከፍተኛ ጥናት እየተደረገበት ያለ ንጥረ ነገር ሲሆን ድብርትን ለማስወገድ በቀላሉ መናደድን መቀነስ እንደሚችል የሚያሳዩ ጥናቶችም አሉ›› ይላሉ ዶ/ር ስቴፈን ኢላርዲ፡፡
ምንም እንኳን ኦሜጋ 3 ከተክሎችም የሚገኝ ቢሆንም ዶ/ር ኢላርዲ ግን ከአሣ የሚገኘው ላይ እንድናተኩር ይመክራሉ፡፡ ‹‹ይህን ችግር ሊያስወግድ የሚችለው ኦሜጋ 3 በሳልመን፣ ሄሪንግ፣ ሳርዲንና ማካረን የተባሉ የአሳ አይነቶች ውስጥ የሚገኘው ነው፡፡›› ብለዋል፡፡
ለንዴት- አረንጓዴ ሻይ
ለሊቱን ሙሉ የጎረቤትዎ ውሻ ሲጮህ በማደሩ አልያም እርስዎ የሳምንቱን የእረፍት ቀናትዎን ሰውተው የሰሩትን ስራ ባልደረባዎ ተመስግኖበት ወይም በሌላ ምክንያት ቱግ ብለው ቢናደዱም ለእርስዎና በአካባቢዎ ላሉት ሰዎች ሲባል በቶሎ መብረድ ይኖርቦታል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ አንድ ኩባያ አረንጓዴ ሻይ በቂ እንደሆነ የስነ ምግብ ተመራማማሪውና የኒውትሪሽን ኤክስፐርቱ ምግብ ዶ/ር ጃኮብ ቴትልባውም ይናገራሉ፡፡
‹‹አረንጓዴ ሻይ theanine የተባለውንና እንድንረጋጋና አትኩሮታችን እንዲሰባሰብ የሚያደርገውን ንጥረ ነገር ይዟል›› ይላሉ፡፡ beat sugar addiction now! የተባለውን መፅሃፍ የፃፉት ዶ/ር ቴትልባውም፡፡
ከቡና ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ የካፌይን መጠን የያዘው አረንጓዴ ሻይ ቁጣዎን የሚያባብስ ሳይሆን ሰውነትዎን ከቡና በተሻለ የሚያረጋጋ ነው፡፡
ለሃዘን – ኮርን ፍሌክስ በወተት
የሃዘንዎ ምንጭ ስራ ወይም የፍቅር ግንኙነት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ቀርፈው በደስታ መዋጥ ይፈልጋሉ? ይህ የሃዘን ስሜት በቫይታሚን ዲ እጥረት የተከሰተ ሊሆንም ይችላል ይላሉ ዶ/ር ጎልዶፎ፡፡
ቫይታሚን ቢ በሰውነታችን ውስጥ በርካታ ጠቀሜታ አለው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ጥሩ ስሜት እንቢያድርበት የሚያደርገውና feelgoodhonmone የሚሰኘውና ሴሬቶኒን እንዲነረት ይረዳል ይህ ንጥረ ነገር እንድንረጋጋ፣ዘና እንድንልና ደስተኛ እንድንሆን ያደርጋል ብለዋል፡፡
‹‹የሰውነትወ የቫይታሚን መጠን ዝቅተኛ ከሆነ ሙድወን የማስተካከልና ድብርትን የመቀነስ አቅምዎ ይ ዛባል፡፡ የቫይታሚኑን መጠነው ለመጨመር ወተትና በቫይታሚን የበለፀገ ኮርን ፍሌክስ (cereal) ወይን እንጉዳይ ይመገቡ፡፡ አነደ አመጋገብዎ ሁኔታ የካለሲየም ወይም ቫይታሚን ዲ እንክበሎችም መውሰድ ሊኖርብዎ ይችላል፡፡
የወር አበባ የስሜት ነውጥ – እንቁላል በሳላድ ሳንዱች
ይህ አካላዊና ስነልቦናዊ ችግድ በእንግሊዘኛው PMS- premenstrual syndrome ይሰኛል፡፡ pms ን ለማስታገስ ከሚመከሩ ምግቦች ውስጥ እንቁላል ሰላደ ዋነኛው ነው፡፡ የወር አበባ ከመምጣቱ አስቀድሞ ባሉት ቀናት ሴቶች የካርቦ ሃይድሬትስአምሮታቸው ይጨምራል ይላሉ ስቴላ ሜትሶቫስ የተባሉ የስነምግብ ባለሙያ፡፡
እንቁላሉ የሴሬቶኒን መጠንን በማሳደግ ድመቶ እንዲሻሻል ይረዳል፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ስኳርና ስብ የበዛበት ካርቦሃይድሬት የያዙት እንደ ዶናት ያሉትን ያስወገዱ ሙደወን ወደ ባሰ አዘቅት ይከትወታል፡፡ ካለተፈተገ ስንዴ የሚዘጋጅ ዳቦ በፕሮቲን ከበለፀገ የቀቀለ እንቁላልና ሱፍጋር ተቀላቀሎ ሲበላ የሴሬቶኒ መጠን አድንደሚጨምር ባለሙያው ይናገራል፡፡ የእንቁላል ሳላድ በዳቦ ምርጡ የካርቦሃይድሬትና tryptophan ቅንጅት ነው፡፡፡