ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ
* ዝክረ አለባቸው ተካ እና የጆሲ ድንቅ ስራ …
* የልጅ አዋቂው ጆሲ እናመሰግንሃለን …
ጆሲ በ2007 ዓም አዲስ አመት ልዩ ዝግጅቱ ታዋቂው ድንቅ ኮሜዲያን አለባቸው ተካን በተገቢ መንገስ አዘከረው ። አርቲስት አለባቸው ተካ ድንቅ ኮሜዲና የመጀመሪያ ቶክ ሾው አቅራቢ ነበር ። አለቤ በተለይም በኢቲቪ የቶክ ሺው ዝግጅቱ በርካታ አርአያነት ያለው ስራዎችን የሰራ ታላቅ ወንድም ነበር ። አርቲስት አለባቸው ተካ ሰርግ ሰርጎ ከአቅመ ደካማ ድሃ ወገኑን በማብላት በማጠጣት ደስታ አለኝታነቱን አሳይቶ ፣ አርአያነት ያለው ስራ ሰርቶ ያሳየን ብቻኛ አርቲስትም ነበር። ለራሱ ሳይኖር ለሌሎች ኢትዮጵያን ለሚወዱ በተለይም ለድሆችና ለከፋቸው የቆመ ወንድም ነበር ። በድንገተኛ አደጋ አለፈ ፣ አዘንን ! እሱ ካለፈ በኋላ ግን እሱን የሚያስታውስም ሆነ የእሱን ቤተሰቦች የሚደግፋቸው አልነበረም ።
ጆሲ ግን አለቤን አልረሳውም ። በወዳጆቹ አማካኝነት ቀን ዘንበል ያለባትን የአለባቸው ተካ ቤተሰቦች አገኘ። በመጀመሪያ ያገኛት ታናሽ አህቱን አህት የሻሸወርቅን ነበር ። ጆሲ ፕሮግራሙን ሲጀምር በተረካው እንደሰማነውና እንዳየነው የአለቤ እህት የሽዋወርቅ በአነ ድምጻዊ ግርማ ተፈራ ድጋፍ በአንድ መዝናኛ ቡና ማፍላት ስራ ወደ ጀመረችበት ቦታ ሄዶ ተዋወቃት !
ይህ እየተከታተልኩ ፣ አሁን የአዕምሮ በሽተኛ የሆነው ሌላው ከልታማ ታዋቂ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ታወሰኝ ! ልመንህ አሜሪካ በስደት ሲኖር አዕምሮው ተነክቶ ፣ ሀገር ቤት ከገባ አመታት መቆጠራቸውን ሰምቻለሁና የዚያ ዘመኑ ፈርጥ ጥርስ የማስከድነው ፣ ዛሬ ከንፈር የሚመጠጥለት ኮሜዲያን ልመንህ ታወሰኝ ! ልመንህ አሁንም አዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች እየተንከራተተ ይሆን? … ሰብሳቢ ደራሽ አጥቶ እንደነበር ባውቅም ዛሬ ሰብሳቤ ደጋፊ አግኝቶ እንደሁ አላውቅም … በልመንህ ህይወት የጀመርኩት በተመሳሳይ ሁኔታ የሚነወከራተቱ ደራሽ ደጋፊ ያጡ ቀን የዘነበለባቸው ጋዜጠኛ ሰሎሞንን ጋዜጠኛ ዳሪዮስ ሞዲን ፣የጥበብና የስፖርት ሰዎች አሰብኳቸው ! ሁሉም ለዚህች ሃገርና ህዝብ የድርሻቸውን ሲወጡ አጨብጭበንላቸው ፣ ሲደካክሙና ቀን ሲዘነብልባቸው የረሳናቸው ግፉአን ናቸው!
… እንዲህ የተረሱ ወገኖችን ከያሉበት እያስታወሱ ድጋፍ ትብብር እንድናደርግ ትልቁን ስራ አየሰራች ያለችው የኢቢኤስ “አርአያ ሰብ ” ዝግጅት መሪ ጋዜጠኛ ህሊና አዘዘ ብዙ የተረሱና በአዲሱ ትውልድ የማይታወቁ የሃገር ባለውለታዎች የማስተዋቀቋን ድንቅ ስራ አስታወስኩ ። ጋዜጠኛ ህሊና እንዲህ ህይወትና የቀደሙ የተደበቁ ማንነቶችን እያሳየች ማስተማሯን በቀጠለችበት አጋጣሚ የጆሲ ኤንድ ሃውስ አስደማሚ ዝግጅት ቀጥሏል! በዛሬው ዝክረ አለባቸው ተካ ዝግጅት ቀልቤን ከነጎደበት መለሰው …አናም ቀልቤን ከሄደበት መልሸ ወደ የጆሲ ልዩ የዓውዳመት ልዩ ዝግጅት አቀናሁ … !
ጆሲ ባማረው መኖሪያ ቤቱ ባቀረበው ዝግጅት ከእህት የሻበወርቅ ተካ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ስለአለባቸው የልጅነት ህይወት አስተሳደግ ፣ ለወገኖቹና ለቤተሰቦቹ ሲደግም እስከተቀጠፈበት ድረስ የራሱ መኖሪያ ቤት አለመስራቱን ሃብት አለማካበቱን ፣ በሚወደው መኪና መንዳት አደጋ በመጨረሻው በድንገት ማለፉን መራራ መርዶ ፣ በህልፈቱ መርዶ ይደግፍ ይረዳው የነበረ ወንድሙ በድንጋጤ መሞቱን ድርብ ሃዘን ፣ ከዚያም የቤተሰቡ ደጋፊ አልባ መሆን ፣ የሚረዳቸው የወንድሙ ልጆች ትምህርት ሳይቀር ማቆማቸውን ፣ የአንዱን ወጣት የታክሲ ደላላ መሆን ፣ ለአቅመ አዳም የደረሰቸው ያንዷ ጉብል በድህነት የተደቆሱ ቤተሰቦችን ለመደገፍ አረብ ሃገር ለመሄድ አስባ መንገዱ በመዘጋቱ ትምህርቷን በችግር ተከባ መቀጠሏን ፣ የአለባቸው የወዳጅ የስራ ባልደረቦች የተባሉትን ይህ ሁሉ ሲሆን ይህ ነው የሚባል ደጋፍ አለማድረጋቸውን ፣ እንደ ወ/ሮ አሚና ያሉት ጎረቤቶች ለየሽወርቅ ያደረጉት ድጋፍ ሁሉንም ልባችን በሃዘን እየተሰበረው አሳዛኝ ያልሰማነውን ታሪክ ከእህቱ ጋር በአቤቱ ከአለቤ ወንድም ባለቤት ጋር ቁርቁስ ካለው ቤት ደጃፍ የሆነውን ሰማን !
አጠር ላድርገው …ጆሲ ከሃዘን ትካዜው ያወጣነወ ዘንድ እንደዋዛ ወደ ሙዚቃው ዝግጅት ልውሰዳችሁ ብሎ በአስገራሚና ባልተጠበቀ አቀራረብ ለአለቤ እህት አለ የተባለ የኮስሞቲክ ሱቅ ቁልፍ አስረከባት ! ስጦታው ጎረፈ …ያዘነ የተከዘ ልባችን ትፍስህት አገኘች …እኒያን የጨለመባቸው የአለቤን ወንድም እናት ሳናስበው አመጣና እሳቸውንም በሚያስደንቅ ስጦታ አንበሻበሻቸው! በችጋር የተጠበሱ ፣ ያዘኑ ፣ የተከዙ ፣ ተስፋ የጨለመባቸውና የተጨነቁት የአለባቸው ቤተቦች ብቻ ሳይሆን እኛም የጆሲ ታዳሚዎች በጆሲ በጎ ምግባር የምንይዝ የምንጨብጠው አጣን !
ጆሴ ሌላም እንግዳ ነበረው … ሌሎች ያደገችው ሃገር ግፉአን ! አበባና ሮቤል ድሃ አደግነታቸው ሳያንስ ኤች አይ ቪ ተጠቂዎች ናቸው ፣ የደሃ የጀርባ አጥንቱን ያሳየን የጆሲ የክበር እንግዶች ሆኑ ! ልዩ የድጋፍ ገጸ በረከት ተበረከተላቸው። ዝርዝሩን ለወተወው … ትምህርት ያቆመችው አበባ ትምህርት እንድትቀጥል ስጦታ ተበረከላት ፣ ለሮቤልም እንዲሁ : ) ጆሲ ከሜሪ ጆር ፣ ከዳሸን ፣ ከመድሃኒአለም ሞል እና ከቀሩት በጎ አድራጊዎች ጋር በመተባበር ጆሲ ድጋፉን በማቀናጀት በስጦታና በተቆራጭ ሁሉንም ተገፊወች አንበሸበሿቸው: ) ልዩ የአውደ አመት ስጦታ: )
ጆሲ ስለተደረገው ነገር ሁሉ አመሰገነ ! የድጋፍ ትብብር ሲጠይቅ አሻፈረኝ ስላሉት ሲናገር አንረዳም አንሰጥም ማለታቸውን ባይኮንነውም “ለካስ ለመስጠትም መሰጠት አለበት!” ሲል የተናገረው ታላቅ መልዕክት ንፉጎች ልብ ብለን ልንሰማው የሚገባ ቀዳሚ ቁምነገር ነበር ! ከገባን …
ዝግጅቱ ወደ መጠናቀቁ ተቃረበ …ክብር እንግዶቹ የአውደ አመቱን ኬክ ቆረሱ ፣ አልቅሰው ታሪካቸውን ነግረው ልባችን ሰብረው ያሳዘኑን የአለቤ ቤተሰቦ በአሉን በደስታ እየጨፈሩ ብሩሁን መጭ ጊዜ ይቀበሉ ቀን ከፈጣሪ በታች ብልሁ ጆሱ የአንበሳውን ድርሻ ያዘ ፣ ዝግጅቱ ተከወነ ! …
እንዲህም አልኩ ..ጆሲ ጧሪ የሌላቸውን በሚደግፈው መቅዶንያን ባቋቋመው ወጣት እና በመሰሎቹ እጹበ ድንቅ ምግባር ስንደመም ለከረምነው ባሳየህን ፋና ወጊ በጎ ምግባር ኮርተናል : ) በጥቁቷ እንኳ ለበጎ ምግባር ሳይሰለፉ “ሃብታችን ህዝብ ነው! ” እያሉ በሚያደነቁሩን በሃገሬ ጥበብ ባለሙያዎች የታመምን ብዙዎች ባንተ በወጣቱ ድምጻዊና የተዋጣልህ ቶክ ሾው አዘጋጅ እውነተኛ የህዝብ ሃብትነትም ኮራን! ይብላኝ ለሆዳሞች … በእጅጉ እንኮራን እወቀው አልሃለሁ !
እንዲህም ሆነ …ዝግጅትህ እየተላለፈ እያለ በርካታ መልዕክቶች ደረሱኝ …በምኖርበት አረብ ሃገር ሳውዲና በቀረው አለም የሚገኙ ወዳጆቸ በሰራህው ድንቅ ሰብአዊ ስራ ተማርከው እርዳታና ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸውልኛል! በጎ ሃሳብ ነው አልኳቸው ! ዳሩ ግን ያንተን አላማ ለመደገፍ እሰክንደራጅና እስኪሳካ ቢያንስ የተሳካልን በአረቡ አለም ያለን ወገኖች በአጠገባችን ከአፍንጫችን ስር የሚንከራተቱ የተቸገሩትን የኮንትራት ሰራተኞች በመደገፉ ሰብዕናችን እናሳይ ማለት ወደድኩ! ብቻ በአመት በአሉ ልዩ ዝግጅት ጆሲ ባንተ ደምቀናል !
በአሉ በአንተ በጆሶ ኤንድ ሾው ልዩ ዝግጅት ደምቆ ተሸኘ !
የልጅ አዋቂው ጆሲ እናመሰግንሃለን !
መልካም በዓል!