በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ በሚል ጥሪ የደረሳት የቆንጆ መጽሔት ዋና አዘጋጅ በጥሪው መሰረት የሚደርስባትን እስርና መንገላታት በመስጋት ጷጉሜ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ከሀገር መሰደዷ ተረጋግጧል መንግስት በሀገሪቱ የነጻው ፕሬስ ላይ እያደረሰ ያለውን ማሳደድ ተከትሎ በነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም ብቻ 21 የግሉ ፕሬስ ጋዜጠኞች ከሀገር መሰደዳቸው ተረጋግጧል።
ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ ቅዳሜ ጷግሜ 1ቀን 2006 ዓ.ም ታትሞ ለንባብ የበቃውን የቆንጆ መጽሔትን ያተመው ማተሚያ ቤት በመንግስት ባለስልጣናት መታሸጉ ለማወቅ ተችሏል:: መንግስት በጋዜጠኞቹ ላይ እያደረሰ ያለውን ማሳደድ አለም አቀፍ ተቋማት እያወገዙት ሲሆን መንግስትም እስራቱንና ማሳደዱን ቀጥሎ የሎሚ፣የፋክት፣የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኞች የፍርድ ውሳኔ ተከሳሾቹ በሌሉበት መስከረም 8 ቀን 2007 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል