“ግዜ ከማባከን ውጭ አሁን ባለው ሁኔታ ለውጥ ማምጣት አይቻልም። ” አቶ ጸጋዬ አላምረው
አንድነት ፓርቲ ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ የሂሳብ ክፍል ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዬት አቶ ፀጋዬ አላምረው ከነሐሴ 30/12/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከሂሳብ ክፍል ሀላፊነታቸው ራሳቸውን በፈቃዳቸው ማግለላቸውን ገልፀዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የጀርባ አጥንት በመባል በትግል አጋሮቻቸው የሚነገርላቸው አቶ ፀጋዬ አላምረው ራሳቸውን ከሃላፊነት ያገለሉበት ምክንያት አሁን ባለው ሁኔታ ፓርቲው ለወጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑና በዚህ ሁኔታ መቀጠሉ ግዜ ከማባከን ውጭ ተጨባጭ ለውጥ ስለሌለው ራሳቸውን ለማግለል መገደዳቸውን ገልፀዋል፡፡የፓርቲው ፕሬዝደንት አዲሱን ካቢኔ ሲያቋቁሙ በተሸሙት ካቢኔዎች ለውጥ ይመጣል ብለው እንደማይጠብቁ ለምክር ቤቱ ማስረዳታቸውም አይዘነጋም፡፡
Yared Amare ከአንድነት ፓርቲ እንደዘገበው