Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ አውሮፓ አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ በለንደን ተካሄደ

$
0
0

Andargachew Tsige.jpg2ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመላው አውሮፓ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ይህ የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ደማቅ መሆኑን ወንድማገኝ ጋሹ በስልክ ገልጿል። የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ተላልፈው ከተሰጡበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ መብታቸውን በመግፈፍ በኢትዮጵያውያን እንዳይጎበኙ ከልክሏል። አብዛኛውን ስራቸውን እንዳጠናቀቁ በተደጋጋሚ ሲናገሩ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ወደተለያዩ ቦታዎች በሌሊት እየተዘዋወሩ ምርምራ እየተደረገባቸው መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የኢትዮጵያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን ለመያዝ ከፍተኛ ገንዘብ ለየመን የጸጥታ ሃይሎች መክፈሉን መዘገባችን ይታወሳል።

Source:: Ethsat


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>