Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ፖሊሱ ራሳቸውን አጋለጡ

$
0
0

ከደቂቃዎች በፊት ኢቴቪ በፖሊስ ፕሮግራሙ ስለ ሐሳዊው ዶክተር ኢንጂነር ሳሙኤል ዘሚካኤል ዘገባ ሰርቶ ነበር፡፡ምርመራውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የከፍተኛ ወንጀል ምርመራ ሃላፊም ስለ ሳሙኤል ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

derሳሙኤልን በኢንተርፖል ትብብር ከኬንያ እንዲመጣ ማድረጋቸውን የተናገሩት ኮማንደሩ ‹‹በእርሱ ላይ መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን፡፡ማስረጃዎቹን ካሰባሰብን በኋላም ማስረጃዎቹ የሚያስከስሱት ይሁኑ አይሁኑ አንመለከታለን››ብለው አረፉት፡፡

ኢንተርፖል ወንጀለኞችን በማደን ለፍትህ የሚያቀርብ አለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡በኢንተርፖል አማካኝነት በወንጀል የሚጠረጠሩ ሰዎች ካሉበት ቦታ ታድነው ለፍትህ እንዲቀርቡ ግን ተቋሙ ጠብሰቅ ያለ መረጃ ይፈልጋል፡፡በኢንተርፖል ውስጥ ያሉ አለም አቀፍ የወንጀል ሞያተኞችም የሚፈለገው ሰው ወንጀል መስራቱን የሚያሳይ አሳማኝ መረጃ እንደቀረበ ካላወቁ በስተቀር ተፈላጊው ሰው እንዲታደን ትዕዛዝ አያስተላልፉም፡፡

ሳሙኤልን በተመለከተ ኮማንደሩ የነገሩን ደግሞ ለኢንተርፖል ፖሊስ ብቻ ሳይሆን የአገር ውስጡ ፖሊስ እንኳን ግለሰቡ የሚያስከስሰው ወንጀል ስለመስራቱ እስካሁን እርግጠኛ አለመሆኑን ነው ፡፡በእኛ አገር ፖሊስ የአይኑ ቀለም ያላማረውን ሰው አስሮ ስላሰረው ግለሰብ መረጃና ማስረጃ ለመፈለግ መኳተኑ ወይም የተጋገረ ክስ በማቅረብ ተጠርጣሪው በሀይል ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ በማለት በራሱ ላይ እንዲመሰክር ማድረጉ እንግዳ ነገር አይደለም ለዚህ የቅርቦቹ ዞን ዘጠኞችና ሶስቱ ጋዜጠኞች ማስረጃ ናቸው፡፡

ጥያቄው ኢንተርፖል ይህንን በፖሊሳዊ ሞያ መቶ ዓመት ያለፈበትን አሰራር በመከተል ተጠረጠሩ የተባሉ ሰዎችን ያድናል ወይ የሚለው ነው ?በግሌ ይህ አይመስለኝም፡፡የኢንተርፖል ይፋዊ ዌብሳይትን መጎብኘት የቻሉ ሰዎችም ሳሙኤል በኢንተርፖል በኩል መጣ የሚለውን ለመቀበል ይቸገራሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በደህንነቶቹ አማካኝነት ወደ ጎረቤት አገራት በማምራት የሚፈልጋቸውን ሰዎች እያፈነ ሲያመጣ መቆየቱን ማስታወስ ከቻልንም ሳሙኤል በኢንተርፖል መጣ የሚለው ሽፋን እንደሆነ ይገባናል፡፡ኮማንደሩ በኢንተርፖል መጣ ብለው መረጃ እያሰባሰብን ነው ማለታቸውም ራሳቸውን ከማጋለጥ ተለይቶ አይታይም፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>