በማስረሻ መሀመድ
የደም መርጋት ወይም ትርምቦሲስ የሚባለው አንድ የደም ስር ውስጥ የደም መርጋትን በመፍጠር በደም መዘዋወሪያ ሲስተም ውስጥ የደም ፍሰትን ሲያውክ ነው፡፡ አንድ ትሮምቦስ ደም ከልብ የሚያጓጉዘውን የደም ስር አካባቢ ከ75 በመቶ በላይ ሳይዝ ወደ ቲሹ የሚፈሰው የደም መጠን አቅርቦት በጣም ስለሚቀንስ ህመም ይፈጥራል፡፡ በዚህ ብቻ ሳይወሰን እንደ ላክቲክ አሲድ የመሳሰሉ የሜታል ውጤቶች ይከማቻሉ፡፡ እንቅፋቱ ከ9ዐ በመቶ በላይ ከሆነ እኔክስያን /Anoxia/ ያስከትላል፡፡ ይህ ሙሉ በሙሉ ኦክሲጅን እንዳይገኝ ያደርጋል፡፡ በዚህ ብቻ ሳይወሰን የሴል መሞትን ወይም Infraction ያስከትላል፡፡
መንስኤዎቹ
በህክምናው ረገድ ትሮምቦሲስ የሚከሰተው ባልተለመደ ሁኔታ ከዚህ በታች ካሉት በአንዱ ወይም በብዙዎቹ ምክንያት ነው፡፡
• የደሙ ሁኔታ /Hypercoaguiabity/
• የደም ስሩ ጥራት /Endothelial cell injury/
• የደም ግፊት ባህሪ /Hemostasis/ ናቸው፡፡
ብዙውን ጊዜ ትሮምቦስ የሚፈጠረው በቫሪስኮቬንነው፡፡ ይህ ሲብራራ ለምሳሌ ለረጅም ጊዜ የአውሮፕላን በረራ ከተደረገ የደም ፍሰቱ የዘገየ ወይም የታገደ ይሆናል፡፡ ወይም በጅን /ህዋስ/ ጉድለት ይህ በሽታ ሊከሠት ይችላል፡፡
አከፋፈል
ሁለት የተለያዩ የትሮምቦሲክ ዓይነቶች አሉ፡፡
1. ቬነስ ትሮምቦሲስ
ቬነስ ትሮምቦሲስ አንድ ደም ወደ ልብ በሚያጓጉዘው የደም ስር ውስጥ የደም መርጋት ሲፈጠር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የሚመጡ ብዙ በሽታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የልብ ድካምና ስትሮክ
2. ዲፕ ሼን ትሮምቦሲስ
ዲፕ ሼን ትሮምቦሲስ አንድ ጥልቅ በሆነ ወደ ልብ ደም በሚያጓጉዘው ስር ውስጥ የደም መርጋት ሲከሰት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚያጠቃው የእግር የደም ስሮችን ማለትም እንደፊሞረስ የደም ስር የመሳሰሉትን ነው፡፡ አንድ ጥልቅ የደም ስር ውስጥ የደም መርጋት ከመፍጠር ሶስት ምክንያቶች ወሳኝ ናቸው፡፡ ይህም የደም ፍሰቱ መጠን፣ የደሙ ውፍረትና የደም ስሩ ግድግዳ ኳሊቲ ናቸው፡፡ የዲፕ ቬይን ትሮምቦሊስ ዓይነተኛ ምልክቶች ውስጥ እብጠት ህመም የሚያጠቃው አካባቢ መቅላት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
መከላከያ
የደም መርጋትን በከፊል መከላከል ይቻላል፡፡ በጣም በሰፊው ከሚታዩት የደም መርጋት አይነቶች ውስጥ አንዱ ዲፕ ሼን ትሮምቦሲስ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ የረጋው ደም ከመጀመሪያ ሳይቱ በመነሳት ወደ ዋናው የደምቋት ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ ከተከሰተ የረጋው ደም ሌላ ሰውነት ክፍል ውስጥ ይከማቻል፡፡
ሆስፒታል እንዲተኙ ከተደረጉ ሰዎች ውስጥ ትሮምቦሲስ የኮምፕልኬሽኖች እና አልፎ አልፎም የሞት ዋና መንስዔ ነው፡፡ ስለዚህ መከላከያ ዘዴው በሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ከህክምና ባለሞያ ተገቢው የጤና እንክብካቤ በመስጠት ሲሆን ለበሽታው በሐኪሞች አማካኝነት የሚታዘዙ መድኃኒቶችን በተገቢው መጠቀም ነው፡፡