Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

$
0
0

002a8b24df33f103d3de8d882e515849_Lባለፉት አምስት ዓመታት አቢሲኒያ ባንክን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አዲሱ ሃባ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡ ከነሐሴ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ኃላፊነታቸውን ያስረክባሉ፡፡ ያልተጠበቀ ዕርምጃ ነው የተባለው የአቶ አዲሱ ከኃላፊነት መልቀቅ የተለያዩ ምክንያቶች እየተሰነዘሩበት ቢሆንም፣ አቶ አዲሱ ግን፣ ‹‹ከኃላፊነቴን የለቀቀሁት ራሴ ባቀረብኩት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ መሠረት ነው፤›› ይላሉ፡፡

‹‹ወደ አቢሲያ ባንክ ስመጣ ለሦስት ዓመታት ላገለግል ነበር፡፡ ሆኖም ለአምስት ዓመታት አገልግያለሁ፡፡ በዚህ ወቅት መሥራት የሚገባኝን ሥራ ለባንኩ በማበርከት ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ አሁን የምለቅበት ጊዜ በመሆኑ ኃላፊነቴን ለቅቄያለሁ፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡ የመልቀቃቸው ጉዳይ ድንገተኛ ሳይሆን ቀደም ብሎ የነበረ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ እሳቸው ወደ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት ይጎሉታል የተባሉትን ነገሮች በሙሉ እንዲስተካከሉ በማድረግና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን በማስጀመር የሠሩት ሥራ ጥሩ በመሆኑ፣ ቀደም ብሎ በነበራቸው ሐሳብ መሠረት መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተናግረዋል፡፡ አቶ አዲሱ የሥራ መልቀቂያ ነሐሴ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. አስገብተው ቦርዱ አሥር ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ጥያቄውን እንደተቀበላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የሥራ መልቀቂያው ድንገተኛና ግፊት ያለበት ስለመሆኑ የሚልጹ ወገኖች ግን፣ የአቶ አዲሱ መልቀቅ እሳቸው ባቀረቡት ጥያቄ ብቻ መሆኑን ይጠራጠራሉ፡፡ ከግል ባንኮች በተለየ የተለያዩ ፕሬዚዳንቶችን በመቀያየር ስሙ ለሚነሳው አቢሲኒያ ባንክ አቶ አዲሱ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡

የአቶ አዲሱ መልቀቅ ድንገተኛ ነው የሚለውን እምነት ያጠናከረው ደግሞ፣ አቶ አዲሱ ከጥቂት ወራት በፊት በአገሪቱ ውስጥ በሥራ ላይ ያሉትን አሥራ ዘጠኙንም ባንኮች በአባልነት ያቀፈው የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ነው፡፡

አቶ አዲሱ ማኅበሩን እንዲመሩ ከሰባት ወራት በፊት ሲመረጡ የምርጫ ዘመናቸው እስኪጠናቀቅ ማኅበሩን ለማገልገል ቃል ገብተው የነበሩ በመሆናቸው፣ ከአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንትነት መልቀቃቸው ያልተጠበቀ ነው የሚለውን ግምት ያጠናክረዋል የሚሉም አሉ፡፡ ቀደም ሲል ከአቢሲኒያ ፕሬዚዳትነት የመልቀቅ ዕቅድ ከነበራቸው የማኅበሩ ፕሬዚዳነት ሆነው ለመሥራት ፈቃደኛ አይሆኑም ነበር በማለትም ይናገራሉ፡፡

በሌላ በኩል ግን አቶ አዲሱ በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የሚያምኑ ወገኖች ደግሞ፣ አቶ አዲሱ ከኃላፊነት መልቀቅ ግፊት ያለበት ቢሆን ኖሮ የሽኝት ፕሮግራም እንደማይዘጋጅ ጠቅሰው፣ በጥያቄያቸው መሠረት የተፈጸመ እንጂ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት ሰላማዊ ክንውን ነው ይላሉ፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ከባንኩ የለቀቁ ፕሬዚዳንቶች ይህንን ዕድል አለማግኘታቸውን በማስታወስ፣ የአቶ አዲሱ ከሥራ መልቀቃቸውና በክብር መሸኘታቸው፣ ከሥራ የለቀቁት በፈቃዳቸው ለመሆኑ ማረጋገጫ እንደሆነ ያመለክታሉ፡፡ የባንኩ ቦርድና ማኔጅመንት ለአቶ አዲሱ ሽኝት ነሐሴ 24 ቀን 20006 ዓ.ም. ምሽት በሒልተን ሆቴል ፕሮግራም አዘጋጅቶ ነበር፡፡

አቶ አዲሱ በአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንትነታቸው ውጤት ማስመዝገባቸው ይነገራል፡፡ እንደ ምሳሌ የሚቀርበውም እሳቸው የፕሬዚዳነትነት ኃላፊነቱን ሲረከቡ 46 የነበረውን የባንኩ ቅርንጫፍ ብዛት 106 ማድረሳቸው፣ የባንኩን ካፒታል ከ315 ሚሊዮን ብር ወደ 1.5 ቢሊዮን ማሳደጋቸው፣ 100 ሚሊዮን ብር አካባቢ የነበረውን ትርፍም ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ማድረስ መቻላቸውን በአስረጅነት ያቀርባሉ፡፡

ከባንኩ የተገኘው ሌላ መረጃ ደግሞ አቶ አዲሱን ተክተው ባንኩን በተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አስማረን ቦርዱ መሰየሙ ታውቋል፡፡

የአቶ አዲሱ ከአቢሲኒያ ባንክ መልቀቅ ከጥቂት ወራት በፊት የተረከቡትን የባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንትነታቸውን እንዲለቁ ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል አቶ አዲሱ ከአቢሲኒያ ባንክ ለቀው በዚሁ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሆነው የሚቀጥሉ ከሆነ፣ የባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንትነታቸው ሊቀጥሉ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቁት አቶ አዲሱ፣ ‹‹በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የምቆይ ከሆነ በፕሬዚዳንትነቴ እቀጥላለሁ፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የማይቀጥሉ ሆነ ግን ማኅበሩን በምክትል ፕሬዚዳንትነት የሚያገለግሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ አዲስ ምርጫ እስኪደረግ የአቶ አዲሱን ቦታ ተክተው ሊሠሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡ አቶ አዲሱ በባንክ ኢዱስትሪው ውስጥ ከ36 ዓመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ በተለይ የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክን ለስምንት ዓመታት በፕሬዚዳንት መምራታቸው ይጠቀሳል፡፡ በዚሁ ባንክ ውስጥ በምክትል ፕሬዚዳንትነትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡

 

Source:: Ethiopian Reporter


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>