ከሥርጉተ ሥላሴ 29.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ወርቅ ይቀልጣል። ወርቅ ቀልጦ ከፈሰሰ ደግሞ መልሶ ለማግኘት ይቸግራል፤ አበው „ የፈሰሰ ያልታፈሰ“ ያሉን እኮ ለላንቲካ አይደለም። ብሂሉ ተቋም ነው። መርኹ የምክር አገልግሎትን በተመክሮ ያዘመረ ነው። ይህቺ ወቅት አዎን ይህቺ ወቅት የወያኔ …. ማዕከላዊ አካል ተሰቅዞ የተያዘበት ወርቅ …. ወቅት እንዳትሾልክ እንዳታመልጥ … ጥንቁቅ፤ ብልህ፤ ብልጥ፤ ሥልጡን እንሁን። እንብለጠው የወያኔ ሃርነት ትግራይን ደባና ሸር፤ ቂምና በቀል – እንቅደመው።
ወቅቱን እናዳምጠው። ወቅቱን እናጣጥመው። ወቅቱን እንሁነው። ወቅቱን እናዋህደው – በመስተዋድድ። ይነግረናል … ያውጃል …. ይመሰክራል ….. ይጣራል …. ተጋሩኝ እያለ። ተጠቀሙብኝ እያለ። ወቅቱ የቅምጥል ጊዜ አይደለም። የመከራ ጊዜ ነው፤ የሽርሽር ጊዜ አይደለም። በጽሞና መርምረን ወቅቱ ለጠዬቀን ማናቸውም ሁኔታ ወቅቱን በድርጊት አስመችተን ልናስተናግደው በእጅጉ ይገባል። የወቅት ጽናታዊ ተደሞ እኛን እዬቀደመን ነው። የወቅት በሳል ተመክሮ እኛን እዬበለጠን ነው። የወቅት ጽሞናዊ አርምሞ እኛን እያለፈን ነው። እኮ ምን ምን እንጠብቃለን? „አሻምን በተባ ሥራ ለመሞሸር“ አይበቃም እንዲህ በቋሳ ገጀሞ መከትከት …. ሃላፊነት በማይሰማው ወመኔ መታረስ –
አዎን እኔ እላለሁ … ይህ የዘመናዊነት የእናቴ መቀነት የተጨወትነበት፤ ፍላጎታችን ያሾለክንበት ጊዜን መለስ ብለን በመገመገም ቀዳሚወን ጥያቄ ባሊህ እንበለው። ባሊህ ማለት ብቻ በቂ አይደለም – እንቀበለው የዕንባን የጭንቅ ምጥ ጥሪውን። አለሁልህ እንበለው። ጥሪው የደም ዕንባ ጥሪ ነው። ቀንም ፋታም የማይሰጥ። ላሜ ወልዳ ዬት ትታሰር ግብ ግብ በአስቸኮይ ቆሞ ሁሉም እንደ አንድ – አንዱም እንደ ሁሉ ቀዳዳውን በመድፍን፤ ክፍተቱን በሞሙላት ሰባራውን በመጠገን፤ ወለምታውን ወጌሻ በመሆን በመከራ ጊዜ አብረን ሆነን ህዝብና ሀገርን፤ ታሪክና ትውልድን እናድን ዘንድ ዓይናማው ወቅት እያሳሰብን ነው። አስረግጦ እያሳዬን ነው …. ተንበርክክኮ እዬለመነን ነው፤ መሪ ሆኖ እዬመራን ነው …. በሳል ሆኖ፣ ከእኛም ቀድሞ ተመክሮውን እያቀናልን ነው። ሰነፍ አንሁን —
ገለጥ እናድርገው። በተለያዩ ትብትቦች የተሸበቡ ድቡልቡልና ጠፍጣፋ ሙልሙል ፍላጎቶቻችን እናርቃቸው። ወቅቱ እራሱ መሪውን ያዘጋጃል። ለነገም ሻማ ሁኖ ሊቀልጥ ወቅቱ እራሱን አስቀድሞ እዬተጣራ ነው። አቤት እንበለው። ወይ እንበለው። እሺ እንበለው።
ለዛሬም ለነገም ለነገም ለተወዲያም አዎንታዊ ዘላቂ መስመራችን እንዲሆን እንከብክበው። እንወስን። እንቁረጥ። በራሳችን ላይ የማያዳግም የውስጥ ለውጥ አምጥተን፤ አራሳችን ወቅሰን ከወቅቱ ብሄራዊ ጥሪ ጋር አብረን እንሰለፍ … በፈጠራ – በአዳዲስ የለውጥ አብነቶች ፍላጎታችን እናሳምረው – ራዕያችን እናብራው።
አወን ወቅቱ ዓይናችን ሆኗል። መንፈሳችን አብርተን ካለ ቀጠሮ በማናቸውም የትግል መስመር፤ በማናቸውም የነፃነት እንቅስቃሴ በሁለመናነት በመደጋገፍ፤ በመተባበር፤ በመረዳዳት አብረን – አብርን እንሰለፍ። በአንድ እግሩ የተጠለለውን እንሰሳዊ ሥርዓት ለማሰወገድ …. ዓይናችን – የሃቅ ዓይን እናድርገው …. ልባም እንሁን። ሥልጡን እንሁን። የ97 ድል እዲደገም …. 12 አካላችን እናሰራው …. ድል – ድል ይሆናል። ናፍቆት እውን ይሆናል …. ከሰባራ ሰንጣራ ስንጥቅ እራስን መታደግ ከተቻለ ….
ይህን ዓይናችን ለወቅታችን!እርእሰ አንቀጽ በድምጽ ማደመጥ ይሻሉን? የ28.09.2014 የጸጋዬ ራዲዮን ዝግጅት በዚህ አድራሻ ያገኙታል። www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung Radio Lora (Tsegaye Radio)
ስንብት – የኔዎቹ አብራችሁኝ ስለቆያችሁ ወደድኳችሁ ፍቅሬንም ሰጠኋችሁ – አዘናክቼ። መሸቢያ ሰንበት።
ድል ለኢትዮጵ ሰፊ ህዝብ! ሞትና ሽንፈት ለወያኔ ሃርነት ትግራይ!
ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።