Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

እየተገባደደ ባለው ክረምት ስድስት ሰዎች በጐርፍ አደጋ ሕይወታቸው አልፏል

$
0
0

ታምሩ ጽጌ

 በብዙ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል -መርካቶ ጆንያ ተራ ለሁለተኛ ጊዜ የእሳት አደጋ ደረሰበት

የክረምት ወቅት ከገባ ጀምሮ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜ እስከቀረው እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ስድስት ሰዎች በጐርፍ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ታወቀ፡፡

ሕይወታቸው በጐርፍ አደጋ ካለፉት ስድስቱ ሰዎች መካከል ሦስቱ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ቴዎድሮስ አደባባይ ኤክስትሪም ሆቴል አካባቢ ሲሆኑ፣ ሦስቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሃና ማርያም አካባቢ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላና ሰሚት ኮንዶሚኒየም አለፍ ብሎ በሚገኙት ቦታዎች መሆኑ ታውቋል፡፡

news addisከሌላው የክረምት ወቅት ጋር ሲነፃፀር በዘንድሮ የጐርፍ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር የቀነሰ ቢመስልም፣ በተለይ በንብረት ላይ ግን በብዙ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ከመግለጽ ባለፈ፣ እርግጠኛውን አኃዝ ማስቀመጥ እንዳልተቻለ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን አስረድቷል፡፡

የባለሥልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በተለይ በንብረት ላይ ነሐሴ 19 ለ20 አጥቢያ 2006 ዓ.ም. ሌሊቱን ሲጥል ባደረው ዝናብ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሪቼ አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ እንደ ኦፊሰሩ ገለጻ የጐርፍ አደጋ በተደጋጋሚ በሚያጠቃቸው አፍንጮ በር፣ አምባሳደር፣ ሲኤምሲ፣ አዋሬ፣ ቀጨኔ፣ ኦሎምፒያ፣ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል ውስጥ፣ መነን አካባቢ፣ መካኒሳ፣ ካቴድራልና ጀሞ (23 መኖሪያ ቤቶች ላይ) የጐርፍ አደጋ ደርሶ ንብረት ማውደሙን አስረድተዋል፡፡

አቶ ንጋቱ ጨምረው እንደገለጹት፣ በክረምት ወቅት ብዙም የእሳት አደጋ የሚያሰጋ ባይሆንም፣ ነሐሴ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. መርካቶ ጆንያ ተራ አካባቢ አደጋው ተከስቷል፡፡ በ2006 ዓ.ም. በተመሳሳይ ቦታ የደረሰው የእሳት አደጋ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን የተናገሩት ኦፊሰሩ፣ አራት ሱቆች ብቻ መቃጠላቸውንና ግምቱ 360 ሺሕ ብር የሚሆን ንብረት መውደሙን ገልጸዋል፡፡ ስምንት ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መትረፉንም አክለዋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>