Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አስር ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ሲሉ መገደላቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘገበ

$
0
0

ከመስከረም አያሌው

የኤርትራ ድንበር ጠባቂዎች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ የነበሩ አስር ኤርትራውያንን መግደላቸው ተገለፀ።

eritrea_ethiopia_border+mapሱዳን ትሪቡን ከግድያው የተረፈን አንድ ሰው ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ከነበሩ 18 ኤርትራውያን መካከል አስሩ በኤርትራ ድንቡ ጠባቂዎች መገደላቸው ተገልጿል። ከሟቾቹ መካከልም የ18 ወራት ወታደራዊ ግዴታዋን የተወጣች ሴት እንደምትገኝበት ታውቋል። ሳሙኤል ጌዲዮን የተባለው ከግድያው ያመለጠው ግለሰብ እንደገለፀው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት መንገድ ከጀመሩት 18 ኤርትራውያን መካከል አስሩ በድንበር ጣባቂዎች የተገደሉ ሲሆን፣ እርሱን ጨምሮ ሶስቱ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ሳሙኤል እንደገለፀው ከሆነ የቀሪዎቹ አምስቱ ኤርትራውያን እጣ ፈንታ ምን እንደሆነ አልታወቀም። እንደ ሳሙኤል ገለፃ የድንበር ጠባቂዎቹ በተጓዦች ላይ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ተኩስ የከፈቱባቸው ሲሆን በ18 ወራት ወታደራዊ ግዴታዋን ተወጥታ ያጠናቀቀችዋን ወጣት ጨምሮ አስር ኤርትራውያን የተኩሱ ሰለባ ሆነዋል።

ኤርትራ ሀገራቸውን ትተው ወደ ሌላ ሀገር የሚሰደዱ ኤርትራውያንን የመግደል ፖሊሲ እያራመደች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥም በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣት ኤርትራውያን በድንበር ጠባቂዎች እንደሞቱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከኤርትራ ወጥተው የሚሰደዱ ኤርትራውያን ሀገራቸውን እንደከዱ ተደርገው የሚቆጠሩ ሲሆን፤ ከሀገር ሳይወጡ ከተያዙም ብዙዎቹ ለእስር እና ለሰብአዊ መብት ረገጣ የሚደረጉ ሲሆን፣ በተለይ ከተቃዋሚ ኤርትራውያን ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው የተገመቱ በርካቶች ደግሞ የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል።

አሁንም በርካታ ወጣት ኤርትራውያን በሀገሪቱ ያለውን መቋጫ የሌለው ከባድ ወታደራዊ ግዴታ ሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የመልካም አስተዳደር እጦት በመሸሽ በዚህ የድንበር ጠባቂዎች አምልጠው ወደ ጎረቤት ሀገራት እየገቡ መሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ (ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣ)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>