ዛ አስቂኝና ጥርስ የማታስከድን ወጣት ናት። ከእሷ ጋር ለደቂቃ አይደለም ለሰዓታት አብረህ ብታሳልፍ አይሰለችህም፤ በሳቅ ታንከተክትሃለች። አነጋገሯ ፈጠን..ፈጠን ያለ ነው። ..የሷ ቀልዶች አይረሱኝም።..በ1998 ዓ.ም የደረሰባት ነገር እጅግ አሳዛኝ ነው። የተቃዋሚ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ የቅንጅት ደጋፊዎችና ሰላማዊ ዜጎች በጅምላ እስር ቤት ሲጋዙ አጋጣሚ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ለሁለት ወር ገደማ እጁን ሳይሰጥ ተሰውሮ ነበር። የገዢው ባለስልጣናት (በረከትና መለስ ናቸው) ያሰማሯቸው ደህንነቶች ሲሳይን ፍለጋ ብዙ ሲማስኑ ነበር። ያላሰሱትና ያልተከታተሉት ሰው የለም፤ በመጨረሻ ግን እህቱን አፈኑ። እየደበደቡ ወደ ወለጋ ወሰዷት። ሴት ልጅ ልትቋቋመው ከምትችለው በላይ በዱላ አሰቃይዋት። « ሲሳይ የት ነው ያለው? ተናገሪ?» ሲሉ ፍዳዋን አስቆጠሯት። ምንም እንደማትውቅ ነገረቻቸው። ምንም ሲያጡ ወለጋ ላይ ፀጉሯን ላጭተው፣ በድብደባ ጐድተውና አቁስለው፣ እጅግ አዳክመው ጫካ ውስጥ አውሬ እንዲበላት ጥለዋት ሄዱ። ራሷን የሳተችው አቦነሽ (ቴሌ) ፈጣሪ ነፍስሽ ይትረፍ ሲላት ገበሬዎች አገኟት። ተሸክመው ወሰዷት። በመኖሪያ ጐጆዋቸው እንድታገግም አደረጉ። ከዚያም ስልክ ወደ አዲስ አበባ አስደወሉላት። ጋዜጠኞች ስፍራው ድረስ ሄደው አመጧት። ..እነሆ ከ8 ዓመት በኋላ ሌላ ክስ ከሙያ ባልደረቦችዋ ጋር ተመሰረተባትና በዚህ ሰሞን አገር ጥላ ተሰደደች። ይህ ግፍ መቆሚያው የት ይሆን!?…ስለተሰደዱት ጋዜጠኞች እመለስበታለሁ።
(በፎቶው የሲሳይ አጌና እህት በመሆኗ ብቻ በ1998ዓ.ም የተፈጸመባት ግፍ ይህን ይመስላል)
Source- freedom4ethiopian.