Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዘፈን ከክሊፕ ጋር ሊለቀቅ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሰሜን አሜሪካ ካሊፎርኒያ፣ ኒዮርክ፣ ሲያትል፣ ሚኒሶታና ቴክሳስ የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን ካቀረበ በኋላ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰ ሲሆን እዛም የተመለሰው የጀመራቸውን ነጠላ ዜማዎች ለማጠናቀቅ እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል።
teddy afro
እንደምንጮቻችን ገለጻ ቴዎድሮስ ካሳሁን በቅርቡ የሚለቀው ነጠላ ዜማ ቪድዮ ክሊፕ የሚኖረው ሲሆን አብዛኛው ሥራም መጠናቀቁም ታውቋል። ዘፈኑም የሙዚቃው ክሊፕም አንድ ላይ እንደሚለቀቅ የጠቆሙት ምንጮቻችን ዘፈኑ እንደተለመደው እስካሁን ሌሎች ድምጻውያን ያልነኩትን ሃገራዊና አዲስ ሃሳብ ይዞ እንደሚወጣ አስታውቀዋል።

ቴዲ በሰሜን አሜሪካ ኒዮርክ እና ሚኒሶታ ላይ አዳዲስ ሁለት ነጠላ ዜማዎችን መድረክ ላይ የለቀቀ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን እነዚህን ዘፈኖች በስቱዲዮ ቀርጾ ይልቀቃቸው አይልቀቃቸው ምንጮቻችን የነገሩን ነገር የለም።

ድምጻዊው አዲሱን ነጠላ ዜማ ከክሊፕ ጋር ከለቀቀ በኋላ በላስቬጋስ፣ ዋሽንግተን ዲሲ ዳላስን ጨምሮ የተለያዩ ኮንሰርቶች እንደሚኖሩት ታውቋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>