በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆነ አንዴ ግለሰብ (የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ባለቤት ወንድም ነኝ የሚል) በሙዚቃው ንጉስ ስም አንዴ የቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈቱን ከሰማሁ ቆየሁ። ለጥልዬ አይደለም አንዴ የቴሌቭዥን ጣቢያ ሌላም ሌላም ይገባዋል። የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው ግን የተከፈተው ቴላቭዥን ጣቢያ የፕሮግራም ጥንጥኑና ቅንብሩ የሙዚቃውን ንጉስ ገድለ-ጥበብ ከመዘከር ይልቅ ዘረኛውን የወያኔ መንግስት ከተቃዋሚ ወገን ጥቃት ለመከላከል ሲተጋ መገኘቱ ነው።
የጥላሁን ገሠሠ ባለቤት የወ/ሮ ሮማን ወንድም ነው የሚባለው ሰው የሚመራው ይህ ቴሌቭዥን ጣቢያ በብርቅዬው አርቲስት ስም ይህን ርካሽ ተግባር ሲፈጽም፤ ተው ባይ ማጣቱ ላሊው በግርምት ያስደመመኝ ጉዳይ ነው።