Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የኢትዮጵያውያን የስፓርትና ባህል ፌዴሬሽን 12ኛው ዓመታዊ በዓል በምዩኒክ ከተማ ጀርመን ተጠናቀቀ

$
0
0
MUNICH 2014 ESCFE Festival  Photo courtesy of escfe.net

MUNICH 2014 ESCFE Festival
Photo courtesy of escfe.net

የኢትዮጵያውያን የስፓርትና ባህል ፌዴሬሽን 12ኛው ዓመታዊ በዓል በምዩኒክ ከተማ ጀርመን ክጁላይ 30 ቀን 2014 ዓ..ም. እስከ ኦገሰት 2 ቀን 2014 ዓ.ም በፕሮግራሙ መሰረት ተካሂዶ ተጠናቁኣል፡፡የተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች የአዋቂዎች 25 ቡደኖች ሲዘጋጁ 18ቱ በ1ኛ ዲቪዚዮንና ሰባቱ ደግሞ በ2ኛ ድቪዚዮን ሲመደቡ፤ በ1ኛው ድቪዚዮን 25ቱ ቡደኖች በአራት ግሩፕ እንዲከፈሉ ተደርገዋል፡፡ በሁለተኛው ድቪዚዮን ሰባቱ ቡድኖች በሁለት ግሩፕ ሆነው ተዘጋጅተዋል፡፡ሁለት ቡድኖች እንዳልመጡና እነርሱም ስዊድንና ኢትዮ ፍራንስ መሆናችው ተነግሯል፡፡ የማጣሪያውን ወድድር ከ1ኛው ድቪዚዮን 8 ቡድኖች ሲያልፉ፤ ክ2ኛው ድቪዚዮን 4 ቡድኖች አልፈዋል፡፡ በጥሎ ማለፉ ጨዋታ ከስምንቱ ቡድኖቸ ለመጨረሻው የዋንጫ ጨዋታ ኢትዮ ኖርዌይና ኢትዮ ለንደን ተቃዋሚዎቻቸውን በማሽነፍ አልፈዋል፡፡ከሁለተኛው ደቪዚዮን ኢትዮ ምዩኒክ 96 ና ኢትዮ ሸቱትጋርት ተቃዋሚቻችውን አሸንፈው ለመጨረሻው የዋንጫ ጨዋታ አልፈዋል፡፡በመጨረሻም ኢትዮ ለንደን ከኢትዮ ኖርዌይ ጋር ተጫውተው ኢትዮ ለንደን 2 ለ 1 ውጤት የ12ኛውን ዓመት የኢትዮጵያውያን የአውሮፓ የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን  አሽናፊ ሆኗል፡፡ ከሁለተኛው ድቪዚዮን በኢትዮ ሽቱትጋርትና ኢትዮ ምዩኒክ 96 በተደረገው የዋንጫ ጨዋታ ኢትዮ ሽቱትጋርት አሸንፎ የ2014 ዓመት  የሁለተኛው ድቭዚዮን ውድድር አሽናፊ ሆኗል፡፡ የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኩኣስ ውድድር በቂ ግዜ ተስጥቶት ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ መንገድ ተከናውኗል፡፡ኢትዮ ስዊዘርላንድና ኢትዮ ኢሚሊያ ታዳጋዎች ብዙ ተስፋ የሚጣልባቸው እንደሆኑ በሜዳው ላይ በተግባር አስመስክረዋል፡፡ይህንን በጣም ከባድና አስቸጋሪ ዝግጅት በማቀናበር ለተሳተፉት አስልጣኞች ዝቅ ብለን ከልብ የሆነ ምስጋናችን ይድረሳችሁ እንላለን፡፡ለታዳጊ ወጣቶች አሽናፊዎችም የዋንጫና የሜዳልያን የኩኣስ ሽልማቶች በተገቢው መንገድ ከፌዴሬሽኑ ባልስልጣናት ተስጥቷቸዋል፡፡ሌሎችም አካባቢዎች በዚህ ደረጃ ተዘጋጅተው ለሚቀጥለው ዓመት ውድድር የታዳጊ ወጣቶችን ቡድኖች አዘጋጅተው እንዲቅርቡ ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በስፖርቱ መስክ የሴቶች እህቶቻችንና እናቶቻችን ተሳትፎ እንዲጨምር ሴቶች እራሳቸው ጥረት በማድረግ ካሁኑ ዓመት የተሻለ ሁኔታ ቢፈጥሩ የተሻለ ይሆናል፡፡ባሁኑ ዓመት የኢትዮ ምዩኒክ የቮሊቮል ቡድን በብቸኝነት ቀርቦ ተወዳዳሪ በማጣት ብቸኛው ተወዳዳሪና አሸናፊ በመሆን የሜዳሊያ ሽልማት ተደርጎላቸዋል፡፡ ለሚቀጥለው ዓመት ውድድር በተወዳዳሪነት እንደሚቀርቡ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ 5 ኢትዮጵያውያን የእግር ኩአስ ዳኞች ጠቅላላ የእግር ኩኣስ ውድድሮችን በታዛቢነት በሶስቱም ሜዳዎች በመሆን ፌዴሬሽኑ እየመደባቸው እስከ መጨረሻው ድረስ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ እነዚህ 5 ኢትዮጵያውያን ዳኞች የነበራቸው ሃላፊነት አንድ ጨዋታ ሲደረግ የሚጫወቱበት ሜዳ ላይ በመገኘት የሁለቱንም ቡድኖች የተጨዋቾች መታወቂያ እያንዳንዱን ተጨዋች እሱ መሆን አለመሆኑን ማረጋግጥ ሲሆን ይህን ያላሟላ ተጨዋች አይጫወትም፡፡ ተጨዋች ሲለወጥ የሚለወጠውን ተጨዋች ማንንት ማረጋገጥና ለረዳት ዳኛው በሚቀጥለው የጨዋታ መቁኣረጥ ልውውጥ እንዳለ ማሳወቅና እንዲቀየር ማድረግ፤ በጨዋታው ወቅት ያለውን ሁኔታ መዘግብ ለምሳሌ ጎሎችን፥ ቢጫ፥ ቢጫና ቀይና ቀይ ካርድ መጻፍ፥ ሌሎች ሁኔታዎች ከተከሰቱም ጽፎ በመጨረሻ ለፌዴሬሽኑ ሃላፊ ማቅረብ ናቸው።የታዳጊ ወጣቶችን፥ የሸማግሌዎች ቡድንና የሁለተኛ ዲቪዝዮን የመጨረሻ የዋንጫ ጨዋታ በኢትዮጵያውያን ዳኞች ተመርቷል፡፡ የኢትዮጵያውያን ዳኞች እንዳይገኙ አዘጋጁ የኢትዮ ምዩኒክ ቡድን ፍላጎት ሰለነበረ፥ ፌዴሪሽኑ ከኢትዮጵያውያን ዳኞች ጋር ብዙ የስልከ ግነኙነቶች በማድረግ፥ በተለይም በቴክኒክ ኮሚቴ ሃላፊው ጥረት እንዲገኙ እንደተደረገ ነው ፡፡

የዝግጅቱቦታ

የዝግጅቱ ቦታ በጣም አመቺ ሲሆን በተለይ ለህፃናት ብዙ የሚመች ነው፡፡የእግር ኩኣስ ሜዳዎቹ ሶስት ሲሆኑ ሶስቱም መብራት ዬላቸውም፡፡ አንዱ ሜዳ ቢያንስ መብራት ቢኖረው ችግር ቢያጋጥምና ቢመሽ በመብራት መጫወት የሚቻልበትን ሁኒታ አመቺ ያደርጋል፡፡ወደፊት የሚያዘጋጀው ቡድን ይህንን  ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ ነው፡፡ለነጋዴዎች ብዙ ትናንሽና ትላልቅ ድንኩኣኖች  በመትከል የተለያዩ አገራዊ ምግቦች በ€10 ለተመጋቢዎች ቀርበዋል፡፡ለስላሳ መጠጥ €3 ነበር፡፡ እኔን የምዩኒክ ባህል የሚለው ድንኩኣን ውስጥ የሚሽጠው ደረቅ ጥብስ በእንጀራ ከአዋዜ ጋር ቁኣሚ ምርኮኛ አድርጎኛል፡፡የኢሳት ድንኩኣን ውስጥም „ኢሳት የኢትዮጵያውያን ጆሮ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር“ የሚል ማሰታወቂያ በተደጋጋሚ ያስማ እንደነበር ነው፡፡የተለያዩ አረንጉኣዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያላቸው ጌጣጌጦች፥ሹራቦች፥ ቀሚሶች፥…ወዘተ ለሽያጭ በየድንኩኣኖቹ ቀርበዋል፡፡ የኢትዮጵያን ባንዲራ ቀለም ጫማ ላይ መደረጉን ያዩና ያስቆጣቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ይሄ ለወደፊቱ ቢታስብበት መልካም ነው፡፡ ከድንኩኣኖቹ መሃከል የተለያዩ ዝግጅቶች የቀረቡብት ዋናው መድረክ ላይ የወያኔው ቀኝ እጅ የሆነው  አቶ እስጢፋኖስ ወይም በሌላ ስሙ ጂሚ የሚባለው የኮሎኝ ከተማ ነዋሪ የሆነው የወያኔን ፖለቲካ የእሱን ግሩፖች ጀርመኖችና ሌሎችንም በማቅረብ ፕሮፓጋንዳውን በብቸኝነት እንዲያካሂድ መደረጉ የአዘጋጁን የፖለቲካ ወገንተኝነቱን ያሳያል፡፡የተሻለ የሚሆነው ለሁለቱም ወገኖች ማለትም ለወያኔ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች እኩል ግዜና መድረክ ለየብቻቸው መስጠት ወይም ሁለቱንም ወገኖች መድረክ አለመስጠት ነው፡፡ በተለያዩ ድንኩአኖች ቡና፥ ኤስፐሬሶ፥ አሳምቡሳና ለልጆች የተጠበሰ ድንችና ሌሎች ለስፖርቱ እንግዶች በአማራጭነት ቀርበዋል፡፡ወደ ሁዋላ ለየት ብለው የሚገኙ ድንኩአኖችን ጠጋ ብሎ ለተመለክተ በጣም አሳዛኝና አደገኛ የሆኑ ሸቀጦች የሚሸጡብት ሰፍራ ነበር፡፡ ጫት የሚታኘከበትና የሚሽጥበት፥ ሺሻ የሚሳብበትና ሌሎች አድንዛዥ እፆች ሰፈር ነበር፡፡ይህ ሁኔታ የአዘጋጁ የኢትዮ ምዩኒክ ስምምነት ተግባራዊ ሊሆን ስለማይችል፤ በዚህ ነጥብ ያለ ምንም ይቅርታ መወገዝ ያለበት ነው፡፡ ለታዳጊ ወጣቶች ስለጫት ሽያጭና መቃም፥ሺሻ እንዴት መሳብ እንዳለብትና ከሌሎች አደንዛዥ እፆች ጋር ለማስተዋወቅ ካልሆነ በስተቀር፤ ይህ ዓይነቱ ድርጊት አስመልክቶ ኢትዮ ምዩኒክ በሰራው ጥሩ ስራ እንደተመሰገነው በዚህ ፀረ ስፖርት ድርጊት መወገዝ ያለበት ነው፡፡ፌዴሬሽኑም የዚህ ዓይነት ፀረ ስፖርት ድርጊቶች አዘጋጁ አገር አስተማማኘ በሆነ መልኩ ተግባራዊ እንዳያረግና ከልከል መሆኑን ማሳወቅና ይህንን የማያሙኣላ ቡድን ከፌዴሬሽኑ ሊወገድ የሚችልበትን ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡አዘጋጁ ቡድን ላለበት አገር ፖሊሶች ዝግጀት እንዲያደርጉ በቅድሚያ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

 የኢትዮምዪኒክናኢትዮሆላንድጨዋታ

በኢትዮ ምዪኒክና ኢትዮ ሆላንድ መሃከል የእርስ በርስ መማታት ሁኔታ ተፈጥሮ ሶስቱ ጀርመናዊ ዳኞች ጨዋውን አቁኣርጠው ሄደዋል፡፡ከዚያም በፊት አንድ የኢትዮ ምዩኒክ ተቀይሮ ከወጣ በሁላ አጨዋቹን ዳኛ በመስደቡ ቀይ ካርድ ሲሰጥወ፥ ዳኛውን „ሰምህ ማነው? ከጨዋታ በሁኣላ እገኘሃለሁ“ በማለት ካሰፈራራው በሁኣላ አጨዋቹ ዳኛ „ኣራት ደቂቃ እሰጠሃለሁ፡፡ ከሜዳው ከልል ውጭ ካልሄድክ ጨዋታወን አቁኣረጣለሁ“ ካለው በሁኣላ በመሪዎቹ ገፋፋኒት ሜዳውን ጥሎ እንድሄድ ተደርጉኣል፡፡ከዚያ ጨዋታው በኢትዮጵያዊው ዳኛ የቀረው የጨዋታ ሰዓት እንዲያልቅ ተደርጉኣል፡፡ይሀ ዓይነቱ አስራር ትክክል ሰላልሆነ ለወደፊቱ ሊሻሻል ይገባል፡፡ምከንያቱም  ጀርመንያዊ ዳኛ ጨዋታውን ያቁኣረጠበትን ምክንያት ለፌዲዲሪሽኑ ማሳወቅና ለጨዋታው መቁኣረጥ ምክንያት አንድ ቡድን በቻ መሆኑን ወይም ሁለቱም ቡድኖች መሆናቸውን በግልጽ ሊያስቀምጥ ይገባል፡፡ፌዴሬሽኑ ውሳኒውን ዳኛው በሰጠው መረጃ መሰረት አድርጎ ለጨዋታው መቁኣረጥ ምከንያት አንድ ቡድን ከሆነ፤ ይህንን ቡድን 3 ለ 0 ተሽናፊ እንዲሆን ማድረግ፤ ሁለቱም ቡድኖች ለጨዋታው መቁኣረጥ ምክንያት ከሆኑ ደግሞ ሁለቱም ቡድኖች 0 0 ነጥብ እንዲኖራቸው ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ጨዋታው በምንም መልኩ ሊቀጥል አይገባውም፡፡ይሄ ጥፋተኛውን  ውይም ጥፋተኞችን በተዘዋዋሪ የተስራውን መጥፎ ድርጊት ማበረታታት ይሆናል፡፡ባይገርማችሁ አንድ ወጣት ልጅ አጠገቤ ቆሞ ሲደባድቡ እያየ „እንዴ ትላልቅ ስዎችም ይደባደባሉ ?“ በማለት ሲገረም አድምጫለሁ፡፡የዛሬው አልፏል፡፡ ለወደፊቱ ፌዴሬሽኑ ሊያሰብበት ይገባል፡፡

የታዳጊወጣቶችየቅጣትምትሁኔታ

ዋታው የጥሎ ማለፍ ውድድር ስለሆነና እኩል ለእኩል ስለወጡ፤ አሽናፊውን በቅጣት ምት ለመለየት ተራ በተራ የኢትዮ ፓርሚሊ ከኢጣሊያና የኢትዮ ስዊዝ ቡድኖች ተጨዋቾች ቅጣት ምት ይመቱ ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው ከሁለቱም በኩል ያሉት በእድሜ አንጋፋ ከሆኑት ተጨዋቾች የተሻለ የአመታት ችሎታ የነበራቸው ታዳጊ ወጣቶች ነበሩ፡፡ምሰጋናው በማያሻማ መልኩ ለአስልጣኞቻቸው የሚስጥ ነው፡፡በርቱ በርቱ ያስኛል፡፡ ታዲያ ጥሩ ጥሩ የሚባሉት ሁልግዜ በቅድሚያ የሚመቱት ሲሆኑ፥ ቅጣት ምቱ እኩል ለእኩል በመሆን ለረጅም ደቂቃዎች ስለቀጠለ ጎበዝ የሚባሉት መትተው ሌሎቹም ተራ በተራ መምታት ነበረባቸው፡፡አንድ እናትና አባት አካባብዬ ነበሩ፡፡“ውይ እሱ እንዳይመጣ ብቻ እኔ አላይም፡፡ቅጣት ምቱን የሳተ እንደሆነ በጣም ስለሚናደድ እሱም አይተኛም፡፡ እኛንም አያስተኛንም፡፡“ ስትል አያገባም ያለችው ልጃቸው ተራው ደረስና ሮጣ ላለማየት ሄደች፡፡ አባትዬወም ዓይኑን ወደሌላ እቅጣጫ አዞረ፡፡ እኔ ልጃቸው የፍጹም ቅጣት ሲመታ አየሁና ማግባቱን ነገርኩኣቸው፡፡እንዲያውም የጣሊያኑ ቡድን ልጃችው ያለበት በአሽናፊነት ለሚቀጥለው ውድድር አለፈ፡፡በማግስቱ ባልና ሚስቶቹን እግኝቼአቸው ስለነበር፤ ደህና መተኛታቸውን ጠይኩኣቸው፡፡ ሁለቱም ከት ብለው በመሳቅ በሰላም መተኛታችውን አረጋገጡልኘ፡፡ይሀም የሚያሳየው ወላጆቹም ምን ያህል አብረው እንደሚጨነቁ አንዱን ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ነው፡፡

መብረቅናጨዋታማቁኣረጥ

አንድ መሰረታዊ የሆነ ስህተት በሕፃናት የመጨረሻው የዋንጫ ውድድር ወቅት ተፈጽሟል፡፡ይኸውም ዝናብና የመብረቅ አደጋ በነበረበት አጨዋቹ ዳኛ ጨዋታውን ማቁኣረጥ ሲገባው መቀጠሉና ዳኛው እንኩኣ ቢሳሳት የፌዴሬሽኑ መናገሪያው ውስጥ የነበሩት አባላት ለዳኛ ጨዋታውን እንዲያቆም መንገሩ አስፈላጊ ነበር፡፡ አሁን ሁኔታው ምንም ዓይነት አደጋ ስላልደረስ እስየው በማለት ለወደፊቱ ፌዴሬሽኑ ለሁሉም ዳኞች የዚህ የመብረቅ አደጋ ሁኒታ ሲከሰት ጨዋታውን እንዲያቁኣርጡ በመመሪያ መልክ ተዘጋጅቶ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡እዚህ ላይ ወሳኙ ዳኛው በቻ ሊሆን ይገባል፡፡ የተለያዩችግሮች  

ለቡድኖችየሚጠጣውሃእቅርቦት

አዘጋጁ አገር ለቡድኖች የሚጠጣ ውሃ በየቀኑ ተመጣጣኝ የሆነ የውሃ እቅርቦት  ከዚሀ በፊት በቀጣይነት ይደረግ እንደነበርና በምዩኒክ በዓል ላይ ግን በተገቢው መንገድ እንዳልተሟላ ነው፡፡አያንዳንዱ ቡድን ጨዋታውን እስከጨረሰ ድረስ የሚጠጣ ውሃ አቅርቦት የአዘጋጁ የኢትዮ ምዩኒክ ሃላፊነት ሆኖ ሳለ በተገቢው ተግባራዊ ባለመደረጉ ቅሬታዎች ተስንዝረዋል፡፡ይህ በጣም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ስለሆነ ፌዴሬሽኑም ይሀ ጉዳይ መሙኣላቱን ማረጋግጥ ይኖርበታል፡፡

የቁልፍበዛትማነስ

የተጨዋቾች መልበሻ ቤት ቁልፍ አለመኖር፤ የፌዴሬሽኑ ቢሮ ራሱን የቻለ ቁልፍ አለመኖር ችግር እንደፈጠረ ታይቷል፡፡

ኖራለመቀባት

የቁጥር ሜዳ 1 ኖራ ለማስቀባት ብዙም ትኩረት እንዳልተስጠውና ዳኞች መጥተው ሜዳውን ካዩ በሁኣላ በዚያ ሁኔታ የስምንት ቡድኖችን የማጣሪያ ውድድር ለማጫወት እንደማይችሉ ካሰታወቁ በሁኣላ የሚቀባውን ሰው ፍለጋ መራወጥ ተጀመረ፡፡ ከተባለው ሰዓት በጣም ዘግይቶ ቀቢው ሰውየው መጥቶ ሜዳውን ከቀባ በሁኣላ ጨዋታዎቹ ተካሂደዋል፡፡ከዚህ የምንማረው ትምሀርት ሜዳውን ለመቀባት የሚያሰችል ሁኔታ ዝግጅት አስፈላጊ እንደሆነና ወዲያው መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ማዘጋጀት ተገቢ እንደሆነ ነው፡፡ሁለተኛው አማራጭ ኖራው በድንብ ባልተቀባባት ሜዳ ላይ ለማጫወት 14 የሚተከሉ ባንዲራዎች ወይም በፕላስቲክ የሚስሩ ምልክቶች ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህ የመጨረሻው አማራጭ ነው፡፡

የጀርመኖችዳኞች

የጀርመኖች ዳኞች በመጀመሪያው የማጣሪያ ውድድር ላይ ከነበሩት ብዙዎች ጥሩ አልነበሩም፡፡በተለይ ረዳት ዳኞቹ ለስም የነበሩ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ መሃል ዳኞቹ ሜዳ 1ና 2 የነበሩት በአብዛኛው ጥሩ ዳኞች ነበሩ፡፡ በሜዳ 3 ላይ በማጣሪያው ውድድር ላይ የነበሩት ዋና ዳኞችም ሆኑ ረዳቶቹም በአብዛኛው ጥሩ አልነበሩም፡፡ክጥሎ ማለፍ ውደድሩ ጀምሮ አስከ ፍፃሜው ጨዋታ ድረስ የዳኙት ዳኞችም ሆኑ ረዳቶቹ ጥሩ ነበሩ፡፡ አንድ ጨዋታ ላይ ግን በማጣሪያ ውድድር ወቅት የመጀመሪያውን ግማሽ ግዜ ጨዋታ በሶስት ዳኞች ተመርቶ እረፍት ከተደረገ በሁኣላ  ሁለቱ ዳኞች ወዴት እንደሄዱ ሳይታወቅ ተሰወሩ፡፡ በጣም ብዙ ደቂቃዎች ከቆዩ በሁኣላ ተመለሱ፡፡ዋናው ዳኛ ግን ያለሁለቱ ዳኞች ጨዋታውን ቀጥሏል፡፡ይሀ እነዚህን ዳኞች በጣም የሚያስተች ሲሆን፥ ዋናው ዳኛም እነርሱን ይዞ የመቅረብ ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ ሶስቱም ጀርመናዊ ዳኞች የስሩት ሰራ ትክክል አይደለም፡፡

ኩኣሶች

ኩኣሶች በብዛት ስለሚወስዱ ዳኞችና ታዛቢዎቹ ሁለት ሁለት ኩኣስ ለአንድ ሜዳ ይዘው ቢቀርቡና ጨዋታው ሲያልቅ ለፌዴሬሽኑ ተዋካዮች ኩኣሶቹን ቢያስረክቡ ብዙ ኩኣሶች ሊወስዱ አይችሉም፡፡በተጨማሪ ፌዴሬሽኑ የራሱ የሆን አንድ መንፊያ ቢኖረው መልካም ነው፡፡

ግርማሳህሌናማይክራፎን

የፌዴሪሽኑ ሰራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል የሆነው የኢትዮ ፓሪስ መሪ የነበረው አቶ ግርማ ሳህሌ ማይኩን መቼ ነው የሚለቀው ፥ ለሌላ ሰውስ የሚያቀብለው በማለት ፓልቶክ ቢሆን ቢያንስ ቀይ ከባሰም ባውንስ ሊደረግ እንደሚችል ሲዘባበቱበት ተደምጧል፡፡በዚህም አስታከው ማይኩን ና ሃላፊነቱንም ለሌሎች ቢያስረክብ ሸጋ መሆኑንም እነዚህ ወጣት ጠቅ ጠቅ አድራጊዎች  አልሸሸጉም፡፡ይሀንን ሲሉ ሌሎችንም ለረጅም ግዜ በተለያየ ሃላፊነት ላይ ያሉትንም ስም ሳይጠቅሱ ጎንተል አድርገዋል፡፡

ተጋባዥእንግዶች

ተጋባዥ እንግዶች በምን መልክ እንድሚጋበዙ ግልጽ በሆነ መልክ እንዳልተቀመጠና በጉኣደኝነት እንደሆነ ተደርጎ ሲተች ተደምጧል፡፡ይሀ ትችት ባሁኑ በዓል ላይ የተጋብዙትን ፈጽሞ የሚቃወም አይደለም፡፡ሰለዚህ ሁኔታ ፌዴሬሽኑ እንዴት አንድ ሰው በእንግዳነት እንደሚምረጥ ለማንም ሰው ግልጽ በሆነ መልኩ በጽሁፍ ማብራሪያ ቢሰጥበት ጥርጣሬዎችና አሉባልታዎች ብዙ ቦታ አያገኙም፡፡

የፌዴሬሽኑገቢናወጪምርመራሪፖርትጉዳይ

የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ነኝ ብሎ የሚንቀሳቀስ ከሆነ፥ የፌዴሬሽኑ የሂሳብ ገቢና ወጪ ከመጀመሪያው ገንዝብ ያዥ ወቅት ጀምሮ እስካሁኑ እስከ 2014 ድረስ ነፃ በሆኑ ኦዲተሮች ተመርምሮ ለህዝብ እንዳልቀረበ ነው፡፡አይ ተደርጉኣል ከተባለም በተጨባጭ ፌዴሬሽኑ ሪፖርቱን ለህዝብ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡አቶ ብርሃኑ ገንዘቡ ባንክ ተከፍቶ እንዲቀመጥ ተጠይቆ ገንዝብ ያዥ በነበረበት ወቅት አሻፈረኝ እንዳለ እንደሚታወቅ ነው፡፡ባሁኑ ወቅትስ የፌዴሬሽኑ የባንክ አካውንት ተከፍቶ ገንዘቡ በባንክ ደረጃ የሚንቀሳቀስ ለመሆኑ ምንም ፍንጭ አይታይም፡፡በዚህ ላይ ፌዴሬሽኑ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገበዋል፡፡

መኪናየማቆሚያቦታ

መኪናዎችን ከተፈቀደው ቦታ ሳይሆን ባልተፈቀደ ቦታዎች ሃላፊው እየነገራቸው በትእቢት በማቆማቸው ፖሊሶች መጥተው መኪናዎቹን በማስነሳታችው እያንዳንዱ ባለመኪን በትንሹ €300 ያህል እንደሚከፍል ነው፡፡ የፌዴሬሽኑ ተወካይ በማይክራፎን ደጋግም ቢናገርም ብዙ ስዎች በራሳችው ጥፋት ተቀጥተዋል፡፡ አንዳንዶቹም ሽጋ ኮረዳዎችን ለማንሆልል ትላልቅ ሽንጣም  መኪናዎች ተከራይተው ለማሳየት የመጡም  ከተቀጢዎቹ መሃከል እንደነበሩ ነው፡፡ 

ስለዓርብየመዝናኛምሽት

ዓርብ እለት ማታ የስፖርቱ ዝግጅት አካባቢ ባለው ከተማ ለምዩኒክ ቡድን እርዳታ የሚሆን የሙዚቃ ምሸት፤ በሲዲ ሙዚቃ  አጨዋቾች ውድድርና በታወቁት በይሁኔና በናቲ ዘፋኝነት ተዘጋጅቶ ለተሳታፊዎቹ በቂ በሆነ አዳራሽ ውስጥ የሙዚቃ አፍቃሪዎች በጣም በዝግጅቱ እንደረኩና ለአዘጋጆቹ ምስጋናውን እንዳቀረበ ነው፡፡ ለዚህ ምሽት መግቢያው €20 ነበር፡፡ይህ ዓይነቱ አዘጋጁና የሙዚቃ አፍቃሪዎች ረክተው የሚጠናቀቅ ዝግጅት ይደግም የሚያስኝ ነው፡፡

የቅዳሜው የሜዳ ላይዝግጅት

ቅዳሜ እስክ ቀኑ 6 ሰዓት ወይም ግማሽ ቀን ድረስ በጣም ሙቀት ነበር በሜዳ 1 ላይ ትሪቡን ላይ ከፌዴሬሽኑ ኢንፎርሜሽንስ ከሚተላለፍለት አጠገብ በግራ በኩል ትልቅ ዣንጥላ ተተክሎ ከተሪቩኑ ከፍተኛ ቦታ ላይ አንድ አግዳሚ ወንበር ላይ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ አናቶች መቀመጫውንና ጥላው ሰር በመጠለል ፀሃይን ለመሽሽ አመቺ ቦታይዘው ተቀምጠዋል፡፡ልጆቻቸው ደግሞ በሜዳ ቁጥር 1 ላይ የኩኣስ መጫወት ፍላጎታቸውን ሲያረኩ በመመልከት ይወያያሉ፡፡በመጨረሻም አግዳሚ ወንበሩ በአንድ ክፉ ጀርመን ተነስቶባቸው የትሪቡኑ ስሚንቶ ላይ ጋዜጣ አንጥፈው መቀመጥ ተገደዱ፡፡የመጀመሪያውን የታዳጊ ወጣቶች የዋንጫ ጨዋታ እንደ ስፖንጅ ባይደላቸውም ከፀሃዩ ንዳድ ግን ራሳችውን በማዳን በጥላው ሰር ሆነው ለማየት ችለዋል፡፡ ልክ የሁለተኛው የህፃናት ጨዋታ ከተጀመረ በሁኣላ ሃይለኛ ዝናብ ከመብረቅ ነጎድጉኣድ ጋር ቢያንስ ለሁለት ሰዓት በመጣሉ፤ መጠለያ ፍለጋ ዱብዱብ ወደ አቅጣጫው ሆኖ ነበር፡፡ነጎድጉኣድ ያስከተለው ሃይለኛ ዝናብ ረገብ ብሎ በመጠኑ እየዘነበ በነበረበት ወቀት ሶስት ጨዋታዎች በቁጥር 1 ሜዳ ላይ ተካሂደዋል፡፡በመጨረሻም የሽልማት ሰነ ስርዓት ተካሂዶ በሜዳ ላይ የተዘጋጀው በዓል ፍፃሜ ሆኗል፡፡

የፌዴሬሽኑተወካዮችናየክለቦችተወካዮችስብሰባ

የፌዴሬሽኑ ተወካዮችና የክለቦች ተወካዮች ስብሰባም ተደርጉኣል፡፡የሚቀጥለው አዛጋጅም በዚሁ ስብሰባ ላይ ይወሰናል፡፡ በወሬ ደረጃ ሽኩሹክታ የሰማነው ኢትዮ  አዲስ ፍራንክፈርት እንደሆነ ነው፡፡ይህን ወሬ ሹክ ያለን ሰው በዚያው ቀጥሎ እንዴት ነው ፍራንክፈርት ብዙ ግዜ የማዘጋጅት እድል የሚሰጠው? ሲል አጉረምርሟል፡፡

የቅዳሜማታየሙዚቃምሽት

በቅዳሜው ምሽት ታዋቂው ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ ከጃኖ ባንድ ጋርና በዓርብ ምሸት በሲዲ ሙዚቃ በማጫወት ውድድር አሸናፊ ከሆነው ጋር የሙዚቃ አፍቃሪውን ለማስደሰት እንደተዘጋጁ ነው፡፡መግቢያው €40 ሲሆን ዋጋው ቅዳሜ ከቀኑ 6 ስዓት ድረስ ትኬቱ በሜዳው አካባቢ መሽጥ እስከተጀመረበት ድረስ አይታወቅም ነበር፡፡ይህም እጅ ላይ የሚታስረው እልቁኣል ስለተባለ ውጭ ያሉ ሰዎች ሰብረው እንደገቡና በሁኣላም ሶስት መኪና ሙሉ ፖሊሶች መጥተው በስነ ስርዓት ተሰልፈው ከፍለው እንደገቡና ሙዚቃው እንደቀጠለ ነው፡፡ በመጨረሻም ጥሩና አዎንታዊ የሆኑትን አዳብሮ እንዲቀጥልና ጎጂና አሉታዊ የሆኑትን ደግሞ እንዲያስወግድ ለሚቀጥለው አዘጋጅ አገር ለማስተላልፍና በሚቀጥለው ዓመት የተሻለ ዝግጅት እንዲሆን በማስብ እስከዚያው በሰላም ሁላችንንም ያድረሰን፡፡   ከተንሳይት በቃና ኦገስት 4 ቀን 2014 ዓ.ም   Email:  tsedal2009@gmx.de


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>