Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ላቂያ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 8.08.2014 (ሲዊዘርላንድ -ዙሪክ)

ይህቺ ተመስጥራ የኖረች እርዕስ በዬትኛውም መጸሐፌ ላይ የለችም። በዬትኛውም ወጋወጎቼም ላይ ታዳሚ ሆና አታውቅም። ቁጥብ ነበረች። ዛሬ ግን ከማህደረ የህሊና ሰሌዳ ብቅ ብላ እነሆ ለአደባባይ ትውል ዘንድ ቀይ ጃኖዋን ለብሳ ከመንበሯ ላይ ጉብ። ላቂያን የመረጥኩት የበለጠ ፍቅር – አትኩሮት – ትህትና – ተደማጭነት – እንክብካቤ ጥበቃ ሊሰጠው የሚገባ የተስፋ አምክንዮ ይዤ ስለቀርብኩ ነው። ይህቺን የምወዳትን ዬክት እርእስ ይዢ ብቅ ያልኩት።

1. መነሻ

10ዘመናዊቷን የደብረማርቆስ ከተማን ለማዬት የዳጎሰ ህልም ነበረኝ። አብዝቼ እሻቅልም ነበር። ስለምን? የሴቶች ዓለምዐቀፍ የርትህ አንደበት የተከፈተባት ታላቅ ባለውለታ የተግባር ማሳ በመሆኗ። የዴንማርኳ ርዕሰ መዲና ኮፐንሀገን የማህበረሰቡ ጸሐይ ለሆኑት አንስተ – ትጉኃን የአርነታችን ልዩ ጧፍ ነበረች። ዴንማርክ ሀገርነቷ በደሴት ውበት የተነጠፈላት ነው ማለት ልቻል ይሆን?

ዴንማርክ በተፈጥሮ የኃይል ማመንጫ ተጠቃሚነቷ የዘመናቱን ሱናሚያዊ ጥፋትን ለመታደግ በብዙ ሁኔታ መሰናዶዋን ያሟላች አብነታዊ ሀገር ስትሆን፤ በተገጣጣሚ ዬቤት ግንባታ ዘርፍም አንቱነቷ ቁንጮ ነው – ለአውሮፓውያኑ። በእንሰሳት ተዋፆ ምርትም የተባ ብቃት እንዳላት ይነገርላታል። ከዚህ በተረፈ የባሩድ መርዛማ ጪስ፤ የመትረዬስ አሲዳማ ሩምታ ፈጽሞ ያልደፈራት የሰላም ድንግል ምድር ናት። አምላክ መርቆ በፈጠራላት ጸጋዋ ንጹህ አዬርን የምትመገብ ደልዳላ ውብ ወ/ሮ ሀገር። ክረምት በሰማዩ ነጭ የአሻቦ አበባ – በጋ ደግሞ በተፈጥሮ ልምላሜ የፈካች። ታድላ!

የኮፐንሀገን ርዕሰ መዲናዋ ዴንማርክን ስታዩ ልክ ደብረ ማርቆስ እንዳላቸሁ ይሰማችኋል። ልዩነቱ እነሱ በ21ኛው ምዕተ ዓመት ላይ ያሉ ዘመኑ ለፈቀዳላቸውን ሥልጣኔ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ ማርቆስዬ ደግሞ ገና ጎሳ ላይ ባለ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ቡድናዊ አስተዳደር በቀል ከሚደቃቸው ከተሞች አንዷ መሆኗ ነው። ፍትህ – የራባት -የራቃትም።

በተረፈ የተፈጥሮ መልክዕ ምድራዊ አቀማመጧ፤ የከተማዋ አመሰራረትና ግራና ቀኛ ያሉት ዬቤቶች ሰልፍ ሁኔታ ክረምት ላይ ከዝናቡ ጋር ያለው የውቂ ደብልቂ ጠረን ሁሉ ቁርጥ ደብረማርቆስ – የዴንማርክ ርትዑዋ ከተማ ኮፐንሀገን። እናላችሁ የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ገና ወደ ዴንማርክ ለመሄድ ስናሰብው ጀምሮ ነው በመንፈስ አብርን ቤተኛ የሆነው። ማንና – ማን? ይመጣበታል —-

2. ምልሰት

በ2009 ከታህሳስ 18 ቀን ጀምሮ አፈሩ መርግ ሆኖ ይክበዳቸውና የወያኔው ዞጋዊ ድርጅት መሥራች ሄሮድስ መለስ ዜናዊን ጨምሮ የኃያላን ሀገሮች መሪዎች በG20 ዓለምአቀፋዊ ጉባኤ ለመታዳም በዴንማርክ ርዕሰ መዲና ኮፐንሀገን ላይ እንደሚገኙ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ የነፃነት ራህብተኛ ወገኖች በዬተዳራጁባቸው መድረኮች ሆነ ድርጅቶች ስንቃቸውን ማሰናዳት – ለጉዟችው የሚያስፈልገውን ትጥቅ ማሟላት ቀድመ ብለው ነበር ዬተያያዙት። በዬአውሮፓው ሀገር ነፃነት ከናፍቆቱ ጋር በህብረት መከረ። ዘመቻው ማዕከላዊ ከመሆኑም በላይ የተቃዋሚ ድርጅቶችንም ያሳተፈ ነበር። ዋና አዝማቻቸው እረኛው ጋዜጠኛ አህመድ ሲሆን ዬስምሪቱ ጠቅላይ አዛዥ ደግሞ የከረንት አፌርስ ዴስከሽን ፎረም ፊት ላይ ነበር። በዬአካባቢው ዝግጅቱ በግልና በወል ጦፈ። በቂ ፍላዬር ፖስተር በአይነት በብቃት ተዘጋጀ። ኮፐንሀገንን በፍትህ ፈላጊያኑ ኢትዮጵያዊ ድምጽ ቀውጢ ለማደረግ መንፈስ አሳምሮ ተሳለ። የኮፐንሀገን የነፃነት ትግሉ ልጆች ስምንት ብቻ ስለነበሩ ጎደሎውን ሁሉ ለመሙላት በትጋት በዬአካባቢው ይጎድለናል፤ አቅም ያስፈልገዋል ባልናቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ሁሉ ከአገልግሏ ጀምሮ ሰፊ መሰናዶ ለዘመቻው ተደረገበት።

ቀኑ በጉጉት ሲጠበቅ ደረሰልን። አቶ መለስን ከሥፍራው ተገኝቶ እርቃናቸውን ማስቀረት፤ ቀልባቸውን መግፈፍ፤ በአለም አደባባይ ሊዘግቡ በተዘጋጁት ጋዜጠኞች አቤቱታውን ማስቀረጽ ጉልበታሙ ዓላማችን ነበር። በረዶው ታዲያ ጉድ ነበረ። በተለይ ለሲዊዝ ታዳሚ ኤክሲሞስ ምስጋን ይነሳው - 21 ግራድ።

አይዋ በረዶው በነፃነቱ ተጠቅሞ በተመቸው ሁኔታ ተደራጅቶ ማን ነክቶኝ ብሎ፣ ተራራ ሰርቶ፣ ምሽጉን አጠናክሮ ጠበቀን። ታዲያላችሁ ከበረዶው ተራራ የሚልከው በረዳማ ንፋስ ሰውነትን ፍሪዝ አደረገው። ተመሳስለን ቁጭ። ነጩን ባዘቶ ለብሰን በሰማይ አሻቧዊ አበባ ተሽሞንሙነን የጎጠኛውን መሪ ሴራ ለማራገፍ አቅማችን በእልህ አደራጅተን ማን ደፍሮን አለን – እኛው። ሰልፉ ዓለምዓቀፉ ጉባኤ እስኪያበቃ ድረስ በተከታታይ ቀናት የሚከውን ነበር። ውሏችን ከዛው ስለነበር የአርበኛን ስንቅ የተሸከመች ታሪከኛዋ አገልግሏም ተሰላፊ ነበረች። እኔው አጮልቄ ሳያት አገልግሏን እሷንም አይዋ የሰማይ አመልማሎ ጎሰም ያደርጋት ነበር። አልራራላት – ሲገርም።

እውነት ለመናገር የበረዶው ክምር የዴንማርክን ከተማ አስተዳደር በፍጹም ሁኔታ ያሸነፈ ጡንቸኛ ነበር ማለት ይቻላል። ሰፈር አድባሩ በተለይ መንገዱ በመልክ የለሽ ሁኔታ ተለነቆጠ። ታዲያንላችሁ አይዋ በረዶ ሌትና ቀን ከተሰለፍንበት እምንቀር መስሎት ሳይደክመው ያወርደዋል – ያወርደዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰውም መኪናም በማይደርስበት ቦታ በነጭ ተፈጥሯዊ አሻቧዊ አበባ ጋራ ምድሩ ተንቆጥቁጦ ለሽ ባሉት ወንዞቿ ላይ ሳይቀር  ነጭ አልጋ ተዘርግቶ በነጭ አልጋ ልብስ ተሽሞንሙኖ ስታዩት ናፍቆ- ገነት ከዚህ ደግሞ ምን ጣለህ ያሰኝ ነበር።

ጉዙው ደግሞ ሌላው ፈታኝ ጉድ ነበር። ብዙ መንገዶች ዝግ ነበሩ። በበረዶ ብቻም ሳይሆን ለጥበቃ ተብሎም። ስለሆነም የጋራ መጓጓዣዎቻችንም እንዲሁ ሞተራቸውን ለማስነሳት ሆነ ለማራመድ ጋዳ ነበር። እዛው በረዶ  ሳንዱቹ አለሁኝ ቢልም እጅ አልታዘዝለትም ብሎ አሻፈረኝ ስላለ ዬጉርሻዋ ዓይን ከእኛ ራህብ ይልቅ  ወደ አመልማሎው ያደላ ነበር። መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ አሰኘው። እንዲህ  ዬእናት ሀገር ልጆች በዬአሉበት – በዬተገኙበት ፈተናን ለማሸነፍ ስንዱዎች ናቸው። ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር እምለውም ለዚህ ነው።

ከሰላማዊ ሰልፉ ደግሞ ማታ ቅልጥ ያለ እመቤት ኢትዮጵያን ማዕከሉ ያደረገ የሰከነ ህዝበዊ ስበሰባ ይካሄዳል። መስተንግዶው ተሟልቶ። አዳር ላይ ሌላ ጨዋታ የለም። የቀጣዩ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በምን ሁኔታ ቢሆን የበለጠ ተደማጭነት ይኖረዋል ነበር። በዬት አቅጣጫ ቢሆን የዓለምን የሚዲያ አትኩሮት ቀልብ መሳብ ይቻላል ነበር የወልዮሹ ዕድምታ። ፈጽሞ ብዕሬ አቅም ኑሯት ልትገልጸው አትችልም የነበረው አመራር – አደረጃጀት – መተሳሰብ – መደማመጥ – ፍቅር – መከባበር – የወይይት ፍጭት እንዴት ነፍስን ይታደግ ነበር። ዕድለኛነቴን ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ዕጣዬ ሁሉንም ዓይነት ገጠመኝ እንዳጣጥም – እንድኖርበት አምላኬ የመፍቀዱን ሚስጥር ዕሴቱን ሳስተውለው ባልፍም ካለ ጸጸት እንዲሆን አድርጎልኛል። „አድርገህልኛልና አመሰግንሃለሁ“

እስካሁን ከታደምኩባቸው ብሄራዊ ሆነ ዓለምዓቀፋዊ የውጭ ሀገር ዜጎች ጉባኤዎች በሀገር ወስጥም ሆነ በውጭ ከገበሬው መንደር ቀጥሎ የዴንማርኩ የመንፈሴ ልዩ ሙሽራ – የጸደቀ ምዕራፍ ነበር ማለት እችላለሁ። ሌላ ዓለም ሌላ ውበት ነበረው። እናት ሀገር የሁለመና መሠረት ናትና! በስደት ሀገር ደግሞ የዚህ ጥልቅ የአብሮነት መንፈስ ሲገኝ የምድር ገነት ነው። ይህን መንፈስ እንዴት መልሰን ማምጣት እንደምንችል አምላክ ይርዳን። አሜን! ምክንያቱም በዚህ መስዋዕትንት ያላፈን መንፈስ ለማስቀጠል ያለው አሳር፤ የድልድይ ሰባራው ዘመቻ፤ የአቅም ብክነቱ … እሱ ባለቤቱ ይፍታው። የሚገርመው የዛ አቅም ሞገድ ጉልበታምነት በወያኔ አስተዳደር ተፈቅዶላቸው የስበሰባውን ሂደት እንዲዘግቡ የመጡትን ጋዜጠኞች እስከማሸፈት የደረሰ ነበር። መርምሩት —-

2. መዳረሻ

በዚህ ወቅት ከካናዳ ድረስ ፕሮግራሙን ከሰላማዊ ሰልፍ ጋር አደራጅቶ  ከእኛ ጋር ዴንማርክ የነበረ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ወንድም ነበረን። እንደኛው ማደሪያ ዶርሚተሪ ተመድቦለት አብሮን ሰሜን አሜሪካን አውሮፓ ላይ ወክሎ በዕንባ ምጡ ታደመ። የዕንባ ምጥ ቀለበት የአህጉር ድንበር የለውምና። ድንቅ ልዩ ወንድም። የእኔ ጌታ ናፍቆቴን በፍቅር ጠልፌ አክብሮታዊ ምስጋናዬ ይደረስህ እላለሁ። ሌላው የአንድ ቤት ልጆች ስንገናኝ የነበረው የፍቅር ጥበብ፤ የጠረኑ ደም ግባት ዬጸዳሉ ኢትዮጵያዊ ጥሪኝ ለትውፊትነት ብቁ ነበር። ከረንት ልዩ እኮ ነው። መግቢያ ዓውደ ምህረት እኮ ነው። ለከረነት ዋጋ አነሰው። እስኪ ኢሳቶች ስለከረንት ህይወት ገባ ብላችሁ ቃለምልስ አድርጉ በተራቸው እነሱም ይጠዬቁ። ውብ አንባ ወርቅ መንደር ከረንት! ዬታሪካችን ዘለበት ነው ከረንት! የስደቱ የመከራ ዘመን በኽረ በልግ።

በ2009 ከታህሳስ 17 እስከ ፍጻሜው የዴንማርክ ውሎ በተቃውሞ ሰልፉና በህዝባዊ ስበሰባው ለመገኘት ከመላ አውሮፓ  የተውጣጡ ካናዳንም ጨምሮ የተግባር አርበኞች በግልም በድርጅትም ታደሙበት። „ኢትዮጵያዊነትን“ ማዕከላቸው ያደረጉ ደፋር ማህበራዊ ድህረ ገፆች፤ የኮሚኒቲ ራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተሳታፊ ነበሩ። ሞትም ቢሆን አብረን ብለው።

ዬኔዎቹ ዬነፃነት ራህብተኞች ወገኖቼ መነሻዬ ሆነ መድረሻዬ የወያኔ ልብጥ ሁለተኛ ቪዲዮ ነው። አሁን የወያኔ የጎጠኝነት ፍቅረኞች ዝርዝር አገኘን ብለው የሚያላዝኑት ስሰማ ወያኔ እዬተኛ ነው የሚኖረው ለማለት ልድፈረው። እንደነገርኳችሁ ገና ሃሳቡ ሲወጠን ቤተኛ ቤተሰብ ነበርን። ስንደርስ ደግሞ ለቅድመ መሰናዶ ምግብ ለማዘጋጀት ካሳለፍነው ሌሊት በስተቀር እዛው ዴንማርክ ዬሚኖሩትን ጨምሮ በአንድ ካንፕ ውስጥ ነበርን። ለእኔ ከሥጋ ዝመድና በላይ – በላይ  - በላይ ዓላማዬ ላቂዬ ነው።

ዶር. ሙሉአለምን ያገኘሁት በዚህ ወቅት ነበር። እንደሚታወቀው በዘመነ ቅንጅት ድጋፍ ድርጅቶች በዬአካባቢው ተደራጅተው ነበር። ከቅንጅት መራራ ስንብትም በፊትም ሆነ በኋላ አቅም በፈለገው ጅረት ተበትኗል። ኖርወይ ላይ ግን በዚህ ላቂያ በሆነ ብቁ ሙሴ አማካኝነት ሃይል አልባከነም። አቅም አልሾለከም፤ ዓላማዊ ድርጅታችን አልተናደም፤ ቤተሰባዊ ግንኙነቱ በማፍያ ሰላዮች አልተበከለም። ማህበራዊ ዘርፉ ተወሳክ አልበቀለበተም። የወያኔ ሴራም አላፈራበትም – እንዲያውም የወያኔ መርሃ ግብር በውጭ ሀገር ድቅቅ ብሎ አመድ ስንቁ የሆነበት መሰረታዊ አመክንዮ በዶር. ሙሉዓለም ነበር ማለት ልቻል። ኖርወይ ላይ የሚታዬው ቋሚና በተግባር የሰከነ የእኩልነት ዓውደ ምህርት የአብነቱ ተከታታይነት ስምረት ሚስጥር ይህ ነው። ዶር ሙሉዓለም አቅም ነው። እሱ እራሱ ስክነት ነው። ብቁ መሪም አባትም ነው። የቀለም ዕውቀት ተመክሮው አቅም እንዴት እንደሚፈጠር፣ ከዬት እንደሚገኝ፤ ከተገኘ በኋላም እንዴት መያዝ እንዳለበት፤ እንዴትም እንደ መክሊቱ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ለተግባር ሰልጥኖ የተፈጠረ ብቁ ሰው ነው።

ይህን ለምናውቅ – ለምንረዳ ሰዎች የሰሞናቱ ሚስጥር የግንቦት 7 ሰዎች በአውሮፓ ዝርዝራቸው ተገኜ  በማለት ወያኔ የሚረጨው ፍዝ መረጃ  ጭድ ነው። የወያኔ ዘገባ ቀለሙ ያለቀ ቀፎ ነው።

እኛ የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ምን በመዳፋችን እንዳለን ጠንቅቀን እናውቃለን። ዛሬ አይደለም ይህ የነፃነት ትግሉ የተግባር ላቂያ ወንድማችን የምናውቀው ….. እኔ እራሴ በ2010 በጸጋዬ ድህረ ገጽና ራዲዮ ፕሮግራም ቃለ ምልልስ አድርጌለት ነበር። ዶር. ሙሉዐለም የምርምር ሰው ስለመሆኑ በቃለ ምልልሱ ተካቷል። የጸጋዬ ድህረ ገጽ ሆነ ራዲዮ ፕሮግራሜ ታዳሚዎች የምርምር ሰው – ሳይንቲስት ስለመሆኑ በሚገባ ያውቃሉ። ዛሬ አይደለም ወያኔ ለእኛ የሚነገረን አሳምረን ጌጣችን – ክብራችን – ኩራታችን – ተስፋችን እናውቀዋለን። እንዲህ ላለ ብርቅ ወንድም ምንም እንኳን በቅርቡ ሁነን ልንረዳው ልናግዘው ባንችልም በመንፈሳችን ሰሌዳ በውስጡ ስላለ ሰንደቃችን አድርገን እንደታቦት የምንከበክበው የተከደነ ሃብታችን ሲሳያችን ነው። ጥበቃው ደግሞ የመዳህኒተአለም ነው።

ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ታስራ በነበረችበት ጊዜ ቤተሰቧ ምንም ዓይነት የኢኮኖሚ መስተጓጎል ሳይደርስበት ልጇ ሃልዬ የተገባውን ሳታጣ እንድትማር ያደረገው በቋሚ የተግባር ጌታው በዶር. ሙሉአለምም የሰከነ የአመራር ክህሎተ -ብቃት ነበር። እንዲያውም የመጀመሪያ ልጁ ባለው ለሴቶች ቅናዊ አክብሮታዊ ታማንነትም ምክንያት ማን ብሎ እንደጠራት እናውቃለን። አብሶ ለሴት ታጋይ እህቶቹ ሲመሰክር አንደበቱን ከፍቶ፤ ሲከታተል መንፈሱን ውስጡን በፍቅር በልግስና ሰጥቶ በልዩ አክብሮት ነው። በዚህ ዘርፍም ክህሎታዊ አንባሳደራችን ነው ብዬ ደፍሬ መናገር እችላለሁ።

ያ ብርቅና ድንቅ ሳይንቲሰት ከእኔ ከትቢያዋ ከማህይማ ጋር ነበር አብሮ በዛ ብርዱ በሚጋርፍበት ቦታ የታደመው። እራሱን ዝቅ አድርጎ ለኢትዮጵያ ዬዕንባ ዬምጥ ብሄራዊ ጥሪ በግንባር ቀደምትንት መሰለፉ ኢትዮጵያ ሀገራችን ፈጣሪያዋ የማይረሳት መሆኑን የሚያሳይ የሃቅ ዬወርቅ እንክብል ነው። ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ልጆቹን እንዴት ይጠብቅ – እንዴትስ ኃላፊነቱን ወስዶ ይንከባባከብ እንደነበር ላሰተዋለው ዶር. ሙሉ ዓለም የሥጦታ ሥነ – ጥበብ ነው ማለት እችላለሁ። እኔ በኖርዎይ ልጆች አዘውትሬ እቀናለሁ። እዛ ብሆን እልምአለሁ።

ወገኖቼ የእኔዎቹ ያ ሰላማዊ ሰልፍ የለዬለት ነበር። ገንዘባቸውን ከስክሰው ብቻ ሳይሆን ዴንማርኮች 8 ብቻ ስለነበሩ ሌሎችንም ሃላፊነቶች ወስደው የቆረጡ – የወሰኑ የኢትዮጵያ ልጆች ለጦርነት ነበር የሄዱት። ስለዚህ ይህ ዕንቁ ሳይንቲስት ዬኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጅ ዬእናቱን የምጥ ዘመን የጸነሰ፤ ችግሯን ለመጋራት የቆረጠ፤ ማናቸውን መስዋዕትንት ለመቀበል የወሰነ የሰብዕዊነት ተሟጋች ተምሳሌት፤ የሙህርነት ህይወታዊነት ናሙና ልዩ ምልክታችን ስለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው አበክሬ በአጽህኖት ልገልጽ እሻለሁ። በዛ ሰላማዊ ስለፍ እኮ ከሳይንቲስቱ ጋር ብዙ ሚዲያዎች ቃለ -ምልልስ እድርገዋል። ዬት ሄዶ ነበር ወያኔ? ለነገሩ 5ኛ ክፍል ላይ እንዴት ተብሎ …..

ሌላው ሁለተኛው ላቂዬ ደግሞ እኔ እንኳን ቅዱስ ሚኬኤል ነው የምለው ግሩምዬ ነው። ዛሬ አይደለም የጉርምዬን  ዬአይቲ (IT) ባለሙያነት ሽፍታው ወያኔ የሚነግረን። እኔ እንዲያውም እንዳገኘሁት ነበር „አንዲት የነፃነት ታጋይ ሴት ድህረ ገጽ ኖሯት ድህረ ገፆን ሊንክ አልደረጋችሁም። ደግሞ የልጆች ፕሮግራምም አላት እሱን እንኳን እንዴት?“ ብዬ ነበር ዬወቀስኩት። በዕድሜ ታናሼ ነው ገሩሜ። በተግባሩ ደግሞ ከድርጊት የበቀለ ታላቄ። ይህን ጥያቄ እንዳገኘሁት ያነሳሁለት ሙያውን አሳምሬ ስለማወቀው ነበር። ወያኔ የግል ልብሱን አደፈ ብሎ ቆሻሻ ውስጥ ጨምሮ በሌላ ቀን ከቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ አውጥቶ መልሶ ይለብሰዋል ልበልን?

ከዬት ይመጣል ጫካና ሀገር መምራት አራባና ቆቦ ነው ….

ወያኔ የሚያንደፈድፈው፣ ዛሩ እንዲህ የሚቀሰቀሰበት ሙያተኞችን ትጥቅ አስፈትቶ ለእሱ ለራፊ ለፍርፋሪ እንዲያጎነብሱ ማድረግ አለመቻሉ ነው። ሙሁሮቻችን እውቀታቸውን ሃገራቸው መሬት ላይ ተግባራዊ ማደረግ ባይችሉም ቁጭታቸውን ሆነ እልሃቸውን መወጣት የሚችሉት በነፃነት ትግሉ ዬሙያቸውን ሃላፊነት በተባ ድርጊት ማዋህድ ሲችሉ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ለወያኔ አብሾው ነው ያንደፈድፋዋል።  …. ግሩሜ ግን አድርጎታል – አሳብዷቸዋል። ስለዚህ ይህ ቀንበጥ ወጣት ታሪኩም ትውልዱም ዕንባ ያማጠውን ጥሪ የተገበረ የድርጊት ቀንድ እንዲሆን አድርጎታል። ስታዩት እራሱ ወርቅ ነው። ፍልቀቱ ነገን ያበራል። የእውነት የተግባር ጸዳሉ ሌትና ቀን የሚያበራ የሚንቦገቦግ የሰብል አዝመራ ነው። ግሩሜ አዝመራ ነው። እሱም ታዳሚ ነበር በኮፐንሃገኑ የዴንማርክ የተቃውሞ ስለፍም ብሄራዊ ስበሰባችንም ላይ ነበር። እኔ በአካል የማውቀውም እዛ ነው ከተባረከው የዴንማርክ የተቃውሞ የዕንባ ምጥ ጥሪ ላይ።

ግሩሜ ማለት ሲደመር – ሲደመር፤ ሲባዛ – ሲባዛ ሥራ ነው። ሃብትነቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። የግሩሜ የትኩሮት አቅጣጫ አንደኛው ሰብዕዊነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ልዐላዊነት ነው። የደንበር ጉዳይ ለግሩሜ ደሙ ነው። በቃ! እኔ እራሴ ስለ ሰባዕዊነት መረጃ ስፈልግ እማገኘው ከእሱ የመረጃ ቋት ነው። አሁን ለዛ ራሱን በቤንዚን በማቃጠል ሰምዕትነቱን ስለገለጸው ስለ ዬኔሰው ገብሬ ማን ቋሚ ሁነኛ አለው? ለግሩሜ የኔሰው ገብሬ የጭንቅላቱ ህሊና ነው እንዲህ ልግለጸው። ግሩሜ ረቂቅ የብሩህ ተስፋ ብርሃናማ ማዕረግ ነው።  እና ጭዶቹ ሳታውቁት ቀርታችሁ ነው ድህረገጹን boycott እንዳይታይ ያደረጋችሁት – ታላግጣላችሁ …. ተረት ተረቶች fantasise/ize ስልችት ብሎናል ይህን ቆርጦ ቀጥል የጭቃ ለጭቃ ጨቀጨቅ ጉዟችሁ —-

3. ክወና

ሁለቱም ወንድሞቼ ለሥም – ለዝና – ለታይታ – ለዕውቅና አይደለም የሚደክሙት። ኑሯቸውን የሰጡት ዛሬ በወመኔው ወያኔ ለሚጠቀጠቀው „ኢትዮጵያዊነት“ ነው። እነሱ የአደራ የተግባር ሙዳዮች ናቸው፤ የበቀል ብቅሉ ወያኔ በንቀት የእግር ገንባሌ ያደረገውን ሰንደቅአላማችን፤ በተጨማሪም ጨርቅ ተብሎ በሄሮድስ መለስ ስላቅ የተንቋሸሸውን ብሄራዊ ዓርማ እነዚህ ተስፋዎች ወደ ክብሩ ለመመለስ ነው ውስጣቸውን ለነፃነት ትግሉ የሸለሙት። በማናቸውም የርሃብ መስክ ሁሉ እንደ ጥንቸል ሰንሰለታማ የመከራ ሙከራ ለሚደርግበት ሀገራችን ኢትዮጵያ ብሩህ የነገ ቀን ነው የሚባትሉት። በወያኔ ለተገፋችው ለተፈናቀለችው እናት ምድር ነው የሚባትሉት። ክብሯ ለተገፈፈው መሬት ነው ከፊት ለፊት ወጥተው የሚታገሉት። ውለታቸው ጥልቅ ፊኖሚናል ነው።

ስለዚህ ያ — እሮ አሮ የተመለሰበትን ካሳ ለማግኘት ቆራርጦ በሚያቀርበው ልብድ ዘገባ መረታት መፈታት ለአፈታም አይገባም። ነገ እነዚህ የቁርጥ ቀን ልጆች በባዶ ሳጥን ላይ ባለው የሙት መንፈስ  እዬገላበ ያለው የትግሬ ነፃ አውጪ ድርጅት ወያኔ ሞት ሆነ ዬእድሜ ልክ እስራት ሊፈርድባቸው ይችላል። ጉዞው ወደዛ ነው። ሲያሰኘውም የሰው ዘረፋውን ወይንም ዬማጥቃት መርዙን አጋጣሚ ጠብቆ ይፈጽማል – በብዙ መልኩ። ትውልድን መንቀል ነው ተልዕኮው።

ግን ግን የኔዎቹ – ክብረቶቼ አንድ ነገር ወያኔ በቀል ተብሎ ሥሙ ቢቀዬር ምን ይመስላችኋል? ወያኔ እኮ የበቀል ብቅል እኮ ነው። ስለሆነም የበቀሉ መረጃ፤ የበቀሉ የፍርድ ሂደት ሰለባ ላለመሆን የበቀሉ ዘገባ አራጋቢና አሽቃባጭ ላለመሆን  ደጉ ጨዋውና ቻዩ የኢትዮጵያ ህዝብ መሰናዳት አለበህ እላለሁ።

አንተን እዬገደለ ነው የበቀል ብቅሉ ወያኔ ለአንተ ቆሜአለሁ የሚለው -። አንተን እዬደረመሰ ነው ከእኔ ወዲያ ነፃነት ሰጪ ላሳር እያላ የሚደለልህ – የበቀል ብቅሉ ወያኔ። ስለዚህ በጥብጦ ሊግትህ የሚሻውን መርዝ በቃህኝ! ብልህ ልታስቆመው የምትችልበት መንሹም ያለህ ከእጅህ ነው።

በተረፈ በኮፐንሀገኑ የተቃውሞ የዕንባ ዬምጥ ጥሪ ላይ የተገኛችሁ ስበሰባውንም ሆነ የተቃውሞ ስልፉንም እንዲሳካ ያደረጋችሁ ብዙኃኑ የነፃነት አርበኞች፤ የንብ አውራ የነበረውን ጋዜጠኛ አህመድንም አክዬ እንዲሁም የኮፐን ሀገን የነጻነት ትግሉ ብርቅዬ ልጆች አዘጋጆች በተጨማሪም ድርቡን ሃላፊነት የወሰዱት የሲዊዲን ናፍቆቶቼን በድጋሚ አመሰገንኩ። ናፍቅኩኝም።  …. ታሪካችን ይፍልቃል …. አይዞን! የበቀል ብቅሉ ወያኔ እኛን አለማሸነፉን የሚረጋገጠው ማናቸውንም የድውይ ወያኔን መረጃ ማፍሰስ – ማባከን – ማክሰል ስንችል ብቻ ይሆናል። ትጋት ስንቃችን፤ ጥንካሬ ቀለባችን ጽናት ትጥቃችን  ይሁን። በዬትኛውም ቦታ በዬትኛውም ሁኔታ ዬአርበኞቻችን ተስፋ የመጠበቅ ግዴታ ይኖርብናል!  www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung www.lora.ch.tsegaye

የነፃነት ባለውለታው ሰንድቅዓላማችን እንዲህ ያምርበታል! http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33255

 

ውዶቼ የኔዎቹ  - እጣታችሁን እባካችሁ  ከተግባር ጋር አቆራኙት። ፍጥነት …. እሺ – እንበርታ!

http://ecadforum.com/2014/07/31/urgent-campaign-to-call-fax-white-house/

 

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ኢትዮጵያዊነት!

ጀግኖቻችን ቋሚ ዬህሊናችን መንገዶች ናቸው!

ነፃነት ያለው ማንነት ለነፃነት ክብር አለው። ግን የነፃነት የቃና መንፈስ ከተገለጠለት ብቻ!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>