Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

መብራት የለም በሚል ሰበብ የኢትዮጵያ ሙስሊም መሪዎች ችሎት ሳይደረግ ቀረ፤ “የሌለው መብራት ሳይሆን ፍትህ ነው”–ታዛቢዎች

$
0
0

ድምጻችን ይሰማ እንደዘገበው፦

‹‹የሌለው መብራት ሳይሆን ፍትህ ነው!›› አስተያየት ሰጪዎች
ሐሙስ ነሃሴ 1/2006

muslimከትናንት ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው የብርቅዬ ጀግኖቻችን ችሎት በዛረው እለት ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ምንም እንኳን ችሎቱን ለመታደም በቦታው የተገኘው እና መሪዎቹ ሲወጡና ሲገቡ ፍቅሩን በሰላምታ ሲገልጽ የነበረው በርካታ ሙስሊም በሰዓቱ የተገኘ ቢሆንም አርፍደው የተገኙት የችሎቱ ዳኞች ዛሬ ችሎት እንደማይኖር በመንገር ለዚህም ሰበቡ ‹‹መብራት አለመኖሩ›› መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት እንዲህ በተደጋጋሚ ‹‹መብራት የለም›› በሚል የሐሰት ሰበብ ችሎት ማቋረጡ እጅግ አሳፋሪ መሆኑ ሳያንስ ህንጻው ላይ ጄኔሬተር እያለም እንኳ ‹‹ጄኔሬተሩ አራተኛ ፎቅ ላይ አይደርስም›› የሚል ሰበብ መስጠታቸው የፍትህ ስርዓቱ ከደዌው የመፈወስ እድሉ አነስተኛ መሆኑን ያሳየ ከመሆን አያልፍም፡፡

በመጨረሻም ዳኞቹ የምስክርነት ማሰማት ሂደቱ ነገ አርብ እንደሚቀጥል መጀመሪያ ገልጸው የነበረ ቢሆንም መጨረሻ ላይ ግን ሃሳባቸውን በመለወጥ ለፊታችን ማክሰኞ ነሃሴ 6 የችሎት ቀጠሮ አስተላልፈው ችሎቱን አጠናቀዋል፡፡

ምንም እንኳን በህግ ሊቃውንት ሳይሆን በደህንነት እና የጸጥታ አካላት ፊሽካ ነፊነት የሚሾፈረው የፍትህ ስርዓት ለከፍተኛ ህዝባዊ ትዝብት መጋለጡ እና ዜጎች ቦታ እየነፈጉት መምጣታቸው ለመንግስት ግድ እየሰጠው ባይመስልም የፍትህ ስርአቱ ግን የማስፈጸም አቅሙ ከቀን ወደቀን እየሰለለ ሄዷል፡፡ ዓይኖቹን የዛሬ ክስተት ላይ ብቻ የተከለና አርቆ ማሰብ የተሳነው አካል ነገን ማየት ባይችልም አንገቷ ታንቆ እያጣጣረች ያለችው ፍትህ ነጻ የምትወጣበት ቀን ግን መምጣቱ፣ ግፈኞችም የእጃቸውን ማግኘታቸው ግን አይቀሬ መሆኑን የቅርብም ሆነ የሩቅ የሰው ልጆች ታሪክ ያስተምረናል፡፡ ቀጠሮ በማራዘም ንጹሃን የህዝብ ጀግኖችን መልካም ዝና ማጠልሸትም ሆነ በህዝብ ዓይን ‹‹አሸባሪ›› ማድረግም ሊሳካ የማይችል ከንቱ ሕልም ነው!

ንጹሃንን በማጉላላት የፍትህ ስርዓቱን መሸርሸር ይብቃ!!!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>