በአንዳንድ የአገዛዝ ሥርዓቶች በሀብት፣ በመደብ፣ ወይም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ አልያም በዘር የተዋቀረ ሥርዓት ይኖራል፡፡ ለምሳሌ በአፄ ኃይለ ስላሴ ጊዜ የነበረው የስልጣን ፍልስፍና ከሰለሞን ስርዎ መንግስት የሚመዘዝ የዘር ሀረግ ባለቤት መሆንን ይጠይቅ እንደነበረ ሁላችንም የምናስታውሰው ነው፡፡ ከሰለሞን ስርዎ (Solomon Daynasty) መንግስት ውጭ ላሉና በዚያ የስልጣን ዘር ሀረግ ውስጥ ያሉ ሆነው በጉልበትም ይሁን በብልሃት ስልጣን ላጡት ስልጣን የሚሰጣቸው በጋብቻ ትስስር እንደነበረ ለማስታወስ የአፄ ኃይለስላሴ ልጆች ከማንና የት ተጋብተው እንደነበረ ማስታወሱ በቂ ምሳሌ ነው፡፡
ከፍ ብዬ የጠቀስኩትን የታሪክና የንድፈ ሀሳብ ማነፃፀሪያ ይዘን የኢህአዴግ አባል ድርጅት ስለሆነው ብአዴን የስልጣን ድልድልና ከሕወሓት በሚሰጣቸው መመሪያ ድርጅቱን በሞኖፖል አንቀው የያዙትን ግለሰቦች የጋብቻ ትስስር፣ በትጥቅ ትግል ዘመን ጊዜ የነበራቸው ተሳትፎን እንዲሁም ዛሬ ያሉበትን ሁኔታ እንደሚከተለው ላቀርብ ተከታተሉ፡–
በክልል ሶስት በዋግ ህምራ ዞን ብርሃኔ አበራ ስለሚባሉ ባልቴት ታጋይ ነው የማወጋችሁ፡፡ ለስሙ የዋግህምራ ዞን ኃላፊ (ሊቀመንበር) ልጃለም ወልዴ ሆኑ እንጅ የዞኑ ህቡዕ መሪ ብርሃኔ አበራ ናቸው፡፡ ይታሰር ያሉት ይታሰራል፤ ይፈታ ያሉት ይፈታል፤ ይባረር ያሉት ሁሉ ከስልጣን ላይ ይባረራል፡፡
ወይዘሮ ብርሃኔ አበራ ለመሆኑ ይኀን ሁሉ ገበሬ ኩሉ ስልጣን ከየት አገኙት? የስልጣን ምንጫቸውን የጨበጡት ከዚህ ቀጥሎ ዝርዝራቸውን በማቀርባቸው ‹‹ታጋይ›› ልጆቻቸው፣ እህቶቻቸውና አማቾቻቸው ወዘተ ነው፡፡
የብርሃኔ አበራ ልጆች
1. መዝሙር ፈንቴ የብአዴን ማ/ኮ አባል የነበረ አሁን የተባረረ፤
2. አሰፋ ፈንቴ፡- የበረከት ስምኦን ሚስት/ሲቭል ሰርቪስ ኮሌጅ የምትማር፤
3. ገነት ፈንቴ፡- አንድ የሕወሓት የደህንነት ባለስልጣን ያገባች፤
4. የሺሀረግ ፈንቴ
5. አሸናፊ ፈንቴ
6. መላኩ ፈንቴ
7. አበባ ፈንቴ፡- የሟቹ ሙሉአለም አበበ ሚስት የነበረች፤ በአገር ውስጥ ጉዳይ የኢሚግሬሽን ቪዛ ኃላፊ የነበረች፤ (የብርሃኔ አበራ እንጀራ ልጅ)
8. አለሚቱ ፈንቴ፡- በክልል ሶስት የምክር ቤት አባል የነበረች፤ አሁን እንግሊዝ አገር ያለች (የብርሃኔ አበራ የእንጀራ ልጅ)
9. ኃይሉ ፈንቴ፡- የጢጣ ት/ቤት አስተዳደር
10. አድና ፈንቴ (የተሰዋች)
የወይዘሮ ብርሃኔ አበራ ታጋይ እህቶች
1. የሺ አበራ የጄኔራል ኃይሌ ጥላሁን ሚስት፣ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል በኃላፊነት ቦታ የምትሰራ፤
2. ነጻነት አበራ፡- የታደሰ ጥንቅሹ (ካሳ) ሚስት ክልል ሶስት በፕሮፖጋንዳ ክፍል ውስጥ የምትሰራ፤
የብራሃኔ አበራ ታጋይ የልጅ ልጆች
1. ውዲቱ አጋዡ፤- መከላከያ ውስጥ የነበረች፤
2. ፍሬህይወት አጋዡ፡- የኢህአዴግ ቢሮ ውስጥ ያለች፣ የውዲቱ አጋዡና የፍሬህይወት አጋዡ እናት የብርሃኔ አበራ ታላቋ ልጃቸው ዋርቃ ናት፡፡
የብርሃኔ አበራ የእህት ልጆች
1. እንወይ ገብረመድህን የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር (የአዲሱ ለገሰ ሚስት የነበረች)
2. ቢያድጎ፤
3. የዋግህምራ አቃቢ ህግ ሹም-ወይዘሮ እንወይ ገ/መድህን የአንድ ወንድ ልጅና የሁለት ሴት ልጆች እናት ናቸው፡፡ የወ/ሮ እንወይ ልጆች አባት አቶ ብርሃኑ ነጋሽ ዛሬ ነዋሪነታቸውን አሜሪካ አገር ያደረጉ ሲሆን፣ ከባለቤታቸው ጋር የተለያዩት ወ/ሮ እንወይ ገና ወደትግል ሜዳ ከመግባታቸው በፊት ነበር፡፡ ወ/ሮ እንወይ ወደ ትግል ከገቡ በኋላ ከአቶ አዲሱ ለገሰ ጋር አንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ጋብቻ መስርተው ነበር፡፡ የአሁኗ የአዲሱ ለገሰ ሚስት የሰቆጣዋ ታምር ተሻለ ነች፡፡ ወ/ሮ እንወይ በአሁን ሰዓት ትዳር የላቸውም፡፡ ወ/ሮ እንወይ ትግሉን ሙሉ በሙሉ የተቀላቀሉት ከ1978 ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኢህዴን ወደ ብአዴን ከተለወጠ በኋላ ነው፡፡ ምንም እንኳ በበረሃው ዘመን የነበራቸው የፖለቲካ ንቃት የኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ሊያደርጋቸው የሚችል የነበረ ቢሆንም፣ ኢህዴን ከሕወሓት የፖለቲካ ፕሮግራም የገለበጠውን ‹‹ፊውዳሊዝም አስፈጊ ጠላታችን በመሆኑ (Threa-tening enemy) በፕሮግራማችን ውስጥ መስፈር አለበት›› የሚለውን አመለካከት ወ/ሮ እንወይ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ አብዮትና ደርግ ጠራርገው የጣሉት ስርዓት የሌለ ስለሆነ፣ ስለሌለ ፊውዳሊዝም መሰረታዊ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጠላት ነው ብሎ ፕሮግራማችን ውስጥ ማስፈር የለብንም›› የሚል አቋም ነበራቸው፡፡ ይህ አቋማቸው እንዲያውም የኢህአፓን ፕሮግራም ተከታይ አስብሏቸው ስለነበረ ነው በጣባው ኮንፍረንስ የኢህዴን ማ/ኮ አባል ሆነው ሳይመረጡ የቀሩት፡፡
4. ሌላኛዋ የብርሃኔ አበራ የአክስት ልጅ፡- የአቶ ታምራት ባለቤት ሁለት ልጆቿን አሜሪካ ይዛ የገባችው ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ ናት፡፡
የዚህ ቤተሰብ የእርስ በእርስ ግንኙነት ሁኔታ
በትጥቅ ትግሉ ዘመን ይህ ቤተሰብ እርስ በራሱ በጣም ይደጋገፍ ነበር፡፡ ከእንወይ ገ/መድህን በስተቀር እስከ 1983 እንወይ ገ/መድህን ከዚህ ቤተሰብ እንዲገለሉ ያደረጋት ታደሰ ጥንቅሹ ነበር፡፡ በ1975 ዓ.ም የኢህዴን የህቡዕ አባላት ተጋልጠው የህይወትና የአካል አደጋ ደርሶባቸው ነበር፡፡ ይህን የህቡዕ አባላት እንቅስቃሴ በጊዜው ይከታተለው የነበረው ታደሰ ጥንቅሹ ነበር፡፡ የእቡዕ አባሎቻችንን ያጋለጠችው እንወይ ነች ብሎ ስላስወራባት ነው እስከ 1983 በመጠኑም ቢሆን ከዚህ ቤተሰብ የተገለሉት፡፡
ሌላኛዋ የዚህ ቤተሰብ አባል ሆና ይኸን ያህል የጎላና እፍ እፍ የቤተሰብ ፍቅር ያልነበራት ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ ነች፡፡ እንዲያውም ወደመጨረሻው አካባቢ የአንድ ቤተሰብ አባል ሆነው በባሎቻቸው የስልጣን ከፍና ዝቅ ማለት፣ በአኗኗርና በአለባበስ በወ/ሮ ሙሉ ግርማይና በሌላው ቤተሰብ አባላት ከፍተኛ አለመግባባት ተከስቷል፡፡ ከዚህም በላይ አቶ ታምራት የግንቦት 20 ትምህርት ቤት ይማሩ በነበሩ የዚህ ቤተሰብ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ፈንጠዝያ ተፈጥሮ ነበር፡፡
ዘ-ሐበሻ ድረገጽን ሁልጊዜ ያንብቡ። በየሰዓቱ አዲስ ነገር አያጡም።
በትጥቅ ትግሉ ወቅት የዚህ ቤተሰብ ተሳትፎና መስእዋትነት
በመግቢያዬ የዘረዘርኳቸው የዚህን ቤተሰብ አባላት ዋና ዋናዎቹን ነው፤ እንጂ ጠቅላላ በብአዴን ውስጥ ያሉትን ኢህዴን ውስጥ የታገሉት በቁጥር 60 ናቸው፡፡ በትጥቅ ትግሉ ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎ በትክክል ማየት እንድንችል ከዚህ ቀጥዬ ስም ዝርዝራቸውን የማቀርብላችሁ በኢህአዴን ውስጥ እንደታጋይ ታቅፈው ጊዜው ይጠይቅ የነበረውን የትጥቅ ትግል ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ የወታደራዊ ስልጠና (ተአለም) ያልወሰዱትን ነው፡፡
1. እንወይ ገ/መድህን
2. ኃይሉ ፈንቴ
3. የሺሀረግ ፈንቴ
4. ገነት ፈንቴ
5. አሸናፊ ፈንቴ
6. አለሚቱ ፈንቴ
7. ብርሃኔ አበራ ከማስታውሳቸው የዚህ ቤተሰብ አባላት ከፊሎቹ ናቸው፡፡
ሁሉም ሰው መገንዘብ እንደሚችለው በአንድ የሽምቅ ውጊያ ስልታዊ ንቅናቄ ውስጥ የሚገኙ የድርጅት አባላት በሙሉ ትግሉ የሚጠይቀውን የወታደራዊ ስልጠና ወስደው ቢያንስ ራሳቸውን መከላከል በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መገኘት አለባቸው፡፡ ሙያና ምንም አይነት የመጀመሪያ ደረጃ የውጊያ እውቀት የሌለው ታጋይ ጠላት ኃይሉን አጠናክሮ ወደ ድርጅቱ ቤዝ አምባ ሊገባ በሚዘጋጅበት ጊዜ ከእቃ ጋር አብሮ መሸሽ ነበር የመጨረሻ እጣ ፈንታው፡፡ ይህ በደፈናው የሚቀርብ የንድፈ ሀሳብ ትንተና ሳይሆን ኢህዴን ውስጥ በተግባር የታየ ሀቅ ነው፡፡ ይህ ቤተሰብ በትጥቅ ትግሉ ዘመን መሽጎ የኖረው ጠላት ይደርስበታል ተብሎ በማይገመተው የኢህዴን ቤዝ አምባ ውስጥ ነው፡፡ የትጥቅ ትግሉ የሚጠይቀውን የውዴታ ግዴታ ይህ ቤተሰብ ሊፈፅም ባለመቻሉ በተለይ በ1978 አካባቢ በሌላው የድርጅቱ አባላትና ይኸን ቤተሰብ ጉያው ውስጥ በሸጎጠው የኢህዴን ማ/ኮ አባል መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡
በወቅቱ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ይህ ቤተሰብ ለመስእዋትነት ዝግጁ አይደለም፤ የሌላውን የድሀ ገበሬ ልጅ ላብና ደም እየጋጠ መኖር የሚፈልግ ነው፤ የኢህዴን ማ/ኮ ለዚህ ቤተሰብ (የነማዘር ቤተሰብ) አባላት ልዩ እንክብካቤ ያደርጋል የሚሉ የሰላ ሂሶች ነበሩ፡፡
ከላይ ስለዚህ ቤተሰብ የገለፅኳቸውና ያነታርኩ የነበሩ ጥያቄዎች ምን ያክል ትክክል መሆናቸውን ለማየት ከ60 የቤተሰብ አባላት ውስጥ ስንቶቹ የህይወት፣ ስንቶቹ የአካል መስእዋትነት ከፈሉ የሚለው ጥያቄው በትክክል ይመልሰዋል፡፡ ከዚህ ቤተሰብ ውስጥ የህይወት መስእዋትነት የከፈለችው አድና (ታሪክ) ፈንቴ ብቻ ነች፡፡
በጥይት የቆሰሉ
1.ነፃነት (አምራየ) አበራ በ1977 ዓ.ም ቀስታ ውስጥ ልዩ ስሙ አቡነይ ጋራ በተባለ ቦታ በተካሄደ ውጊያ ዳሌዋ ላይ መጠነኛ የመቁሰል አደጋ የገጠማት ሲሆን በሌላ ውጊያ በጌምድር ክፍለ ሀገር ደጎማ ከተማ በተካሄደ ውጊያ ቀኝ እጇን በብርቱ ቆስላለች፡፡
2.መዝሙር ፈንቴ በ1977 ዓ.ም ዋግ አውራጃ ልዩ ስሙ ተላቁዝቁዛ ይገኝ ከነበረው የኢህዴን ቤዝ አምባ ከራሱ ከመዝሙር ፈንቴ ቤተሰብ ጥይት እግሩ ላይ የመቁሰል አደጋ ገጥሞታል፡፡ ሲጠቃለል ከስድስት ግለሰቦች ውጪ በዚህ ቤተሰብ ላይ የደረሰበት የአካልም ይሁን የህይወት መስእዋትነት የለም፡፡ ስለዚህ የኢህዴን አባላት ለዚህ ቤተሰብ መስእዋትነት ከፈሉ እንጂ ይህ ቤተሰብ ለኢህዴን የከፈለው መስእዋትነት ኢምነት ነው፡፡ እንዲያውም በደም ጎጆ በተገነባ ቤት ውስጥ ተንደላቀው ኖሩ እንጂ ስለነ ‹‹ማዘር›› (ብርሃኔ አበራ) ቤተሰብ ሲነሳ እኔም ጆሮ ዳባ ልበስ ብዬ የማሳልፈው ሀቅ አለ፡፡ የዚህ ቤተሰብ አንድ የእህል ወፍጮ ከቤተሰቡ በላይ እንዳገለገለ መርሳት እኔም የበላሁትን ቂጣ መካድ ይሆንብኛል፡፡
(ዘ-ሐበሻን ያንብቡ0