የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 27 ቀን 2006 ፕሮግራም
<< ...ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ተቃውሞ ፖለቲካ በርካታ መስዋዕትነቶች ተከፍለዋል ከነ ፕ/ር አስራት እስከ ዛሬው የነሀብታሙ ፣የሺዋስ እስር ማንሳት ይቻላል። ይህ ትልቅ ዋጋ ነው...ትግሉ ግን ለውጥ ማምጣት መቻል አለበት እኔ ለአንድነት እና መኢአድ ውህድ ፓርቲ በፕሬዝዳንትነት ብመረጥ ለውጥ የሚያመጣ ስትራቴጂ ነድፌያለሁ ...>>
አቶ በላይ ፈቃዱ የአንድነት ም/ፕሬዝዳንትና ለውህዱ ፓርቲ ከሶስቱ የአንድነት ዕጩዎች አንዱ ለህብር ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የኢቦላ ቫይረስ ስጋት ከምዕራብ አፍሪካ እስከ አሜሪካ (ልዩ ጥንቅር)
<...በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት የሚባለው የህወሃት ባለስልጣናትና ከፍተኛ የፓርቲውን ጄኔራሎች በሀብት ያንበሸበሸ ነው። ስራ አጥነቱን መቅረፍ አልቻለም ተሻርከው በውጭ ባለሀብቶች የአገሪቱን መሬት እና አንጡራ ሀብት እያዘረፉ ነው...የዚህን ስርዓት መቃወም አግባብ ነው ይህን ዛሬ ካላደረግን ነገ የት ሄጄ ነበር ይህ ሁሉ ውድመት ሲሄድ የሚል ጸጸት ያስከትላል...>>
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የዓለም ባንክ የቀድሞ የኢኮኖሚ አማካሪ በኢኮኖሚ ልማት ስም የሚንቀሳቀሱትን የህወሃት መሪዎች መቃወምን አስፈላጊነት ላይ የሰጡት ሙያዊ ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<< ...ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡ ላይ ግፍ እየፈጸሙ እዚህ አገር መጥተው በሰላም የፈለጉትን እንደማያደርጉ እያሳየናቸው ነው...ሕዝቡ ይህን ስርዓት ማንንም ሳይጠብቅ የራሱን እርምጃ መውሰድ መቻል አለበት...>>
ባለፈው አርብ በሎስ አንጀለስ የወያኔ ባለስልጣናትን ለመቃወም ከተጠራው ሰልፍ አስተባባሪዎች አንዱ አቶ መስፍን ሀይሉ ለህብር በስፍራው ከሰጡት ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)
ልዩ ጥንቅር የሎስ አንጀለሱን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ
ሌሎችም አሉ
ዜናዎቻችን
* የኬኒያ የደህንነት ባለስልጣናት በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባርና በሕወሃት አገዛዝ መካከል የሚደረገው የደፈጣ ውጊያ አሳስቦናል አሉ
* የአገዛዙ ባለስልጣናት በሎስ አንጀለስ ጠንካራ ተቃውሞ ገጠማቸው
- አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመና ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን ከስርዓቱ ጋር በመሰለፋቸው ወቀሳ ደረሰባቸው
* በሳውዲ ታጉረው ከሚገኙ ኢትዮጵአውያን ስደተኞች ሰሞኑን የእስር ቤት ግርግዳ ሰብረው የተጠፉት እየተፈለጉ ነው
* ታዋቂው የኢኮኖሚ ባለሙያ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ ኢትዮጵአውያን የአገዛዙን ባለስልጣናት መቃወማቸው አግባብ መሆኑን ገለጹ
* የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በእነ አቶ ሀይለማርያምና በሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ላይ የኢቦላ ቫይረስ ምርመራ እናደርጋለን አሉ
- የላይቤሪያና የሴራሊዮን መሪዎች ወደ ዋይት ሀውስ ከመሄድ ራሳቸውን አገለሉ
* ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ በምርጫ 2007ን መድረኩ በቀላሉ እንደማያየው ገለጹ
- ሕዝቡ <<ምርጫ እንድትሳተፉ>> ይለናል ብለዋል
ሌሎችም ዜናዎች አሉ