Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ በሚኒሶታ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ

$
0
0

olf ethiopia
(ዘ-ሐበሻ) በብርጋዲየር ጄነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ ዓመታዊ ስብሰባውን በሚኒሶታ ጁላይ 7 ቀን 2013 እንደሚያደርግ ለዘ-ሐበሻ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። ድርጅቱ ጁላይ 7 በሚያደርገው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ዘርና ጾታ ሳይለይ ማንኛውም ኢትዮጵያውያን እንዲታደሙ ጋብዟል።
ድርጅቱ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዘንድሮውን ስብሰባ ልዩ የሚያደገውን ምክንያት ሲገልጽ “ይህንን ስብሰባ ካለፉት ልዩ የሚያደርገው ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ወይም ብሔር እና ብሔረሰቦች እንዲሁም ሕጋዊ ከሆኑ ተቃዋሚዎች ጋር በመተባባር የወደፊት የኢትዮጵያን ህልውና እውነተኛ የዲሞክራሲ የሕግ በላይነት የማንኛውም ግለሰብና ድርጅት መብት የሚከበርባት አገር ለመመስረት እንደሆነ ከኦነግ የፖለቲካ ለውጥ መረዳት ይቻላል” ብሏል።
“በዚህ ስብሰባ ላይ የሚገኙ ፡ የሐይማኖት አባቶች ፡ የፖለትካ ድርጅቶች ፡ መካሪ አዛውንቶችና ፡ ታዋቂ ግለሰቦች በወቅታዊ ኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ለመመካካር በዚሁ ታሪካዊ ጥሪ ላይ ይገኛሉ፡፡” ያለው ኦነግ “ስለዚህ ፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ፡ ይህ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ጁላይ 7 2013 ከቀኑ 1፡00 ፒኤም እንድገኙልን በትህትና እንጋብዛለን። ብሏል።
በብርጋዲየር ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ ሕዝባዊውን ስብሰባ የሚያደርግበት አድራሻ የሚከተለው ነው።
አድራሻ : Best Western / Kelly Inn
161 St. Anthony Ave.
St. Paul , MN , 55103

July 7 , 2013 @ 1:00 Pm
አዘጋጅ ኮሚቴ
ጁላይ 7 የኦሮሞ ሰሜን አሜሪካ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በሚኒሶታ የሚደረግበት ሰሞን በመሆኑ ከሌሎች ስቴቶች እና ሃገራት የሚመጡ እንግዶች በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲታደሙ እድሉን ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>