(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው እለት የአንዋር መስጊድ አካባቢ የሕወሓት አስተዳደር በንጹሃን የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ አሰቃቂ እርምጃ እየወሰደ በሚገኝበት ወቅት መርካቶ አካባቢ ለሥራ ጉዳይ ሄዳ የነበረችው የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤትና የሴቶች ጉዳይ አባል ወጣት ወይንሸት ሞላ በደህነንቶች ታፍና ከተወሰደች በኋላ ከፍተኛ ድብደባ ሲፈጸምባት ቆይቶ በዝግ ችሎት ቀርባ 14 ቀን የምርመራ ቀጠሮ ተጠየቀባት።
የነፃ አሳቢ ዜጎች መሰቃያ በሆነውና ከማዕከላዊ አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ውስጥ የምትገኘው ወጣት ወይንሸት ማንም ሰው እንዳይጠይቃት በፖሊሶቹ መከለከሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ዛሬ ረፋዱ ላይ ሜክሲኮ አካባቢ ያለ ፍርድ ቤት የቀረብቸው ወጣት ወይንሸት ምንም እንኳ ችሎቱ በዝግ ቢደረግም ጭንቅላቷ ተፈንክቶ፣ ቀኝ እጇ በፋሻ ተጠቅልሎና አንገቷ ታስሮ የተመለከቷት ሲሆን የህግ አማካሪ እንዳታገኝም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ መከልከሉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አረጋግጠዋል።