Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አበራ ለማ፡ ለባሉ ግርማ፡ አስቦ ወይንስ ሌላ? (ከማተቤ መለሰ)

$
0
0

ከማተቤ መለሰ

 

bealu girma 1አቶ አበራ ለማ፡ ሰሞኑን ”የማይጮኹት ባሉ ግርማን የበሉ ጅቦች” በሚል እርዕስ የጻፈውን በኢትዮ ሚዲያ ድህረ ገጽ ላይ ሳነብ” በአቆማዳው ገመሰኝ” ቢለው ተው ወንድሜ በውስጡ ዲንጋይ ይኖርበታል አለው የሚባለው ብሂል ነው። በሃሳቤ የመጣብኝ። እውነት ከ30 አመት በፊት አድራሻው ስለጠፋው ስለ ብርቅየው የብዕር ሰውና ንጹሁ ኢትዮጵያዊ ሰለ አቶ ባሉ ግርማ ተቆርቁሮ ያነሳው ሃሳብ ቢሆን በበኩሌ እሰየው ነበር።

 

ግን በእርግጠኝነት መታከኪያ ፈልጎ እንጅ ለባሉ ግርማ ተቆርቁሮ አይደለም። አበራ ለማ በተፈጥሮው የሚጨነቀው ለጥቅሙና ለጥቅሙ ብቻ እንጅ ለሰው እንዳልሆነ አሁን የምንኖረው አብረን አንድ አገር ማለትም ኖሮዌይ ስለሆነ በቅርበት የማውቀው በቤተሰቡ ላይ ሳይቀር የፈጸመውና የሚፈጽማቸው ዲርጊቶች ማረጋገጫዎች ናቸው። በአስነዋሬ ምግባሩም መንስኤ ነው በሚኖርበት ሃገር ከማህበረ ሰቡ ተገልሎ ያለው።

 

አበራ ለማ የግል ስብናውን ለመገንባት በጣረበት፡ በዚያ ዝባዝንኬ መጣጥፉ፡ የአለቃው አለቃ የነበሩትንና እውቁን ጋዜጠኛ ዛሬም ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት በብዕራቸው በመታገል ላይ ያሉትን። አቶ ሙሉጌታ ሉሌን የሚከስበት ጭብጥ፡ ሰለ ባሉ ግርማ ፕሬዘዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም አናግረውታል የሚል ነው። አቶ ሙሉጌታ ተጠርተው ከሆነም በአንድ እርዕሰ ብሄር የነበራቸውን ክብር ማሳየቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ለአቶ ባሉ ግርማ መገደል ምክናያት ነው የሚለውን ነጥብ አላመላከተንም።

 

ከዚህም በላይ፡ አቶ ክፍሉ ታደሰ፡ ”በያ ትውልድ” መጻፋቸው እንደገለጹት አበራ ለማ ኢህአፓ ነህ በማለት የገደለውና በእነ እርገጤ መድበው የክስ መዝገብ ተራቁጥር 27 ላይ ስሙ ተጠቅሶ በሌለበት የተከሰሰበት ሟች ሰው አይደለምና ነውን? የሚለውን ጥያቄ ካነሳን፡ ዛሬ አበራ ለማ የሟች ወንድማችንን የአቶ ባሉ ግርማን አጽም መታከክ የፈለገበት ምክናያት ሰባዊነት ሳይሆን፡ ከወያኔ ጋር ያለው የጥቅም ግንኙነት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታዋት ነው።

 

ሌላው አበራ ለማ በጽሁፉ፡ ባሉን የበሉ ጅቦች ሲል፡ ምን ለማለት ነው የሚለው ጥያቄም መታለፍ የሌለበት ነው። በእሱ ቤት ቅኔ መሆኑ ነው፡ ድንቄም ተቀኘች? እሱ በሁለተኛ ቋንቋው ሲቀኝ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሆኑት ጎጃሞች፡ አይገባቸውም ብሎ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ምክናያቱም ሰማቸውን በመደርደር የአንድ መንደር ሰዎች እያለ በፍጹም ጭፍን ጥላቻ የሚያብጠለጥላቸው፡ ትውልደ ጎጃሞችን ነው። ከጅብ ጋር ለማዛመድ የሞከረበት አንደምታም፡ በጅምላ አንድን ህዝብ እንደህዝብ ማዋረዱ ነው፡ በእሱ ቤት። ኢትዮጵያ ውስጥ ጌቶቹ የኦህዴድ ካድሬዎች አማረኛ ተናጋሬውን እየመረጡ በመግደል፣ በማሰርና በማፈናቀል፡ ከግፎች ሁሉ የከፋ ግፍ እየፈጸሙበት ነው። ሐገር ጥለን በመሰደድ እንኳን በሰላም እንዳንኖር፡ እንደ አበራ ለማ አይነት ሰዎች፡ በእየወሩ ሃገር ቤት በመመላለስ፡ ከአለቆቻቸው መመሬያ እየተቀበሉ፡ ተሰዶ ለወገኑ ነጻነት ከምር

2

የሚታገለውን ኢትዮጵያዊ በመዝለፍና በማሸማቀቅ ስራ ላይ ተጠምደዋል፡ በአበራ ለማ ያልተገራ ስድ አንደበት የሚዘለፉ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ። ብቻ አይደሉም፡ ነጻነቴን እሻለሁ በማለት ወያኔን የሚቃወም ሁሉ እንጅ። ለዚህ ማስረጃው ኖረዌይ በሚኖሩ የነጻነት ታጋዮች ላይ በእየ ጊዜው የሚፈጽመው ድርጊት ነው።

 

ዛሬ 30 አመት በሗላ፡ በባሉ ግርማ ሰበብ፡ የተሳበው የጭዋታ ካርታም፡ ሰለ እውነት ለእሱ በመቆርቆር ሳይሆን። ወያኔ ከጀግኖች ሁሉ የላቀውን ጀግናና እውነተኛውን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን፡ በማፈኑ፡ ከሃገር ቤት ጀምሮ በመላው ዓለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያውያን  በጋራ ለመታገል ያለውን ፍላጎት ማሳየቱ ወያኔን ያልተጠበቀ የብራ መብረቅ የወረደበት ታክል ስላስደነገጠው፡ መላ እንዲፈልጉ ካድሬዎቹን በማራወጥ ላይ ሲሆን፡ አበራ ለማም በድርሻው ይህንን የትግል ግለትና የአንድነት እንቅስቃሴ አቅጣጫ ያስቀይስልኛል ሲል ያሰበውን፡ ለጌቶቹ መታያ ይሆን ዘንድ ያቀረበው መሆኑን ልብ ልንልለት ይገባል።

 

በተረፈ አገራችንን ጥለን ተሰደናል፡ በእያለንበት ደግሞ የምናገኛትን ዳቦ በሃገር ናፍቆት እንባ እያራስን እንዳንበላ፡ በእየ ሳምንቱ እየተመላለሱ ተጭነውት የሚመጡ መርዘቸውን  እየደፉበን ያሉ እንደ እነዚህ አይነት አስመሳይ ምንደኞች በእየቦታው እየፈሉ ነው፡፡ ጎበዝ ምን ይሻላል? ከዚህ በሗላ ጨረቃ ላይ አንወጣ፣ የት እንድረስ? አሞትን ኮስተር፣ ትንፋሽን ክትት አድርጎ ከምር ከመታገል በቀር።

 

ቸር እንሰንብት

 

ሃምሌ 6 ቀን 2006

 

 

 

 

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>