Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ቴዲ አፍሮ በሚኒሶታ የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርት አቀረበ፤ 38ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በዚሁ መድረክ አከበረ

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረው የዝነኛው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ። በሚኒሶታ ግዛት በሚኒያፖሊስ ዳውን ታውን በተካሄደውና ብዙ ሕዝብ በታደመው በዚህ ወደ ፍቅር ጉዞ ኮንሰር ላይ ቴዲ ድንቅ ብቃቱን ዳግም አሳይቶ ለሕዝቡም ጥሩ ምሽት እንዲያሳልፍ ምክንያት ሆኗል።

በሚኒያፖሊስ ከተማ እየተደረገ ባለው የኦል ስታር ጨዋታዎች የተነሳ ወደ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት የሚመጣው ሕዝብ የመኪና ፓርኪንግ ለማግኘት የተቸገረ ከመሆኑም በላይ አንዳንድ ሰዎች በዚህ የተነሳ ኮንሰርቱን ሳይታደሙ ሊቀሩ እንደቻሉ ዘ-ሐበሻ አረጋግጣለች።

በዚህ ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ባንድ አቡጊዳ፤ ቴዲ ሊዘፍን መድረክ ላይ ሲወጣ ዘፈኑን ስልት በመለወጥ ወደ”ሃፒ በርዝ ደይ” ሙዚቃ በመቀየር ቴዲ አፍሮን ሰርፕራይዝ አድርገውታል። በመድረኩ ላይ ከሕዝቡ ጋር 38ኛ ዓመቱ የተከበረለት ቴዲ ከሕዝብ ከፍተኛ የሆነ ፍቅር የተቸረው ሲሆን እርሱም ለአድናቂዎቹ “ከሁለት ዓመት በኋላ ባላቴና መባሌ ይቆማል” ሲል ተናግሯል።

ቴዲ አፍሮ በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርቱ 2 አዳዲስ ነጠላ ዜማዎችን ለሕዝብ ያደረሰ ሲሆን ኮንሰርቱ በጣም ድንቅ እንደነበር የታደሙት ሰዎች ለዘ-ሐበሻ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።

ቪድዮዎች ይመልከቱ

Teddy Afro Rocks Minnesota (Video)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>