በሳውዲ አረቢያ የምንኖር ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምንት ተከታይ ወገኖች «ጸሎታችን በቤታችን » በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያውን ምእራፍ ትግል በድ ህረገጽ «ህ» ብለን መጀመራችን ግልጽ፡ነው። ይህን ትግላችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እይተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል። ይህ ሰላማዊ ትግላችን ብዥታ የፈጠረባቸው ጥቂት የመንግስት ካድሬዎች እና በራሳቸው መንፈሳዊ አዙሪት ተዘፍቀው የሚሰቃዩ ጽንፈኛ ግለስቦች ስለትግላችን መነሻ እና መዳረሻ ግራ ተጋብተው ሲወራጩ የስተዋላል ። በዚህም መስረት ጥያቄው ህጋዊ እና ሰላማዊ ለመሆኑ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያህል ጥቂት ለማለት ወደድን ።
ከሳውዲ አረቢያ በመቶ ኪሎ ሜተር ርቃ የምትገኝ ባህሬን በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሰር የሚተዳደሩ 3 አበያተ ክርስቲያናት እንዳሉ አይተናል አድምጠናል ። በየመን «ሠነዓም» ኢትዮጵያውያኑ ምእመናን ባቀረቡት ጥያቄ ሂደቱ የቱንም ያህል ፈታኝ እና ተስፋ አስቆራጭ፡ እንደነብር ቢነገረም በስተመጨረሻ ውጤታማ ሆኖል ። ይህ በዚህ እንዳለ እንደተጠቀሱት ሃገራት የሳውዲ መንግስት በአንድ ቀን ጀምበር አወንታዊ ምላሽ ይሰጠናል የሚል እምነት ባይኖረንም የአንድ ሺህ ኪሎ ሜተር መንገድ በአንድ እርምጃ ይጀመራል እንዲሉ « ፀሎታችን በቤታችን » የትግላችን መነሻ መሆን እንዳለበት እናምናለን ። ለዚህም ሰላማዊ ሃይማኖታዊ የጸሎት ስፍራ ጥያቄ ስኬታማነት የዲፕሎማቶቻችን ትበበር ወሳኝ ሆኖ አጊተነዋል። በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመና ወገኖቻችን ተሰባስበው በደስታ ግዜ ምስጋና በሃዘን ግዜ የተማጽኖ ጸሎታቸውን ለፈጣሪያቸው የሚያደርሱበት እና ሃይማኖታዊ ግንዛቤዎቻቸውን የሚያዳብሩበት በጅዳ ቆንስላን ጽ/ቤት ግቢ እና ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ፈጹም አማራጭ የምይገኝላቸው ቦታዎች መሆናቸው ይታመናል። ስለሆነም በግዜያዊነት የምንሰባሰብበት ቦታ እንዚህ ግቢዎች ውስጥ የስጠን ዘንድ ጥያቄ ማቅረብ መብት ነው። በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ዲፕሎማቶቻችን የቱንም ያህል የእስልምና ህይማኖት ተከታይ ይሁኑ ጥያቄያችንን እስከተቀበሉ ድረስ ዲፕሎማቱ ባህሬን እና የመን ውስጥ ለዜጎቻቸው የጸሎት ቦታ ተጠበው ከኦርቶዶክስ ምዕመናን ህዝባቻቸው ጎን ቆመው ውጤት ካስመዘገቡት የመንግስት ዲፕሎማቶች ህገመንግስታዊ መንፈስ ውጭ ድብቅ አጀንዳ የሚያራምዱ ናቸው ብለን አናምነም ።
ሰለሆነም ሃገር እና ህዝብን ወክለው የተቀመጡ የመንግስት ዲፕሎማቶች እና በኤንባሲው ስር የሚገኙ ምቹ ተቋማት እያሉን ዜጎች በፀሎት ቦታ እጦት ድንበር አቋርጠን በህሬን ድረስ መሄድ አይጠበቅብንም። በአጭሩ ጥያቄያችን ጅዳ ፡ ሪያድ ጂዛን ከተማ ውስጥ የሚገኙ የኮሚኒቲ ማዕከላት ግዜያዊ የጸሎት ስፍራ እንዲዘጋጅለን እይተደረገ ያለ ተማጽኖ ነው ። ይህ “ ፀሎታችን በቤታችን” ጥያቄ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የፀሎት ቦታ ጥያቄ አስመልክቶ በመሆኑ ሃገራችን ውስጥ ካለው ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ወቅታዊ ሁኔታዊች ጋር ምንም አይነት መስረታዊ ግንኙነት የለውም።። «ፀሎታችን በቤታችን » በሚል መረህ ቃል በመላ ሳውዲ አረቢያ የተጀመረው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ጥያቄ የትኛውንም ሃይማኖት ሆነ የፖለቲካ ድርጀት መብት እና ነጻነት የማይነካ በመሆኑ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ዘር ሃይማኖት ፖለቲካዊ አመለካከት ሳይለየው ድጋፋን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ ።
ዛሬ «ፀሎታችን በቤታችን » ስንል በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ግቢ በሪያድ እና በጅዚን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ውስጥ አነስተኛ የእምነት ቦታ ይፈቀድልን ነው ፡፤ይህ መሪ ቃል በኢትዮጵያን ሙስሊም ወገኖችን ዘንድ ተቀባይነትን ከማግኘቱም በላይ ከጎናችን ቆመው ለእቅዳቻችን መሳካት ከፍተኛ አስተዋጾ በማድረግ ላይ የገኛሉ፡፤ እኛ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖች በአንጻሩ ከሙስሊሙ ወንድሞቻችን ጎን ቆመን ለሃይማኖታቸው ነጻነት እያደረጉ ያለውን ሰላማዊ ትገል በተለያየ መንገድ ድጋፍ ፋችንን በመግለጽ ላይ መሆናችን የማይታበል ሃቅ ነው። ይህ በአንድነት ላይ የተመስረተው ጽናታችን ያስበረገጋቸው ጥቂት ዲፕሎማቶች እና በራስቸው የፈጠራ መንፈሳዊ አዙሪት የስከሩ ጽፈኛ ግለሰቦች በህዝበ ሙስሊሙ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖች መሃል እየተሽሎከለኩ መርዘኛ አስተሳሰባቸውን ሲረጩ ይስተዋላል፡፡፤ ይህ በፍጹም ተቀባይ ነት የሌለው እና ህዝባችን በጋራ መከላከል የሚገባው ሴጣናዊ አስተሳሰብ ነው ፡፤ ሁለቱ ሃይማኖቶች ማለት የኦርቶዶክ እና የእስልምና ሃይማኖት ምዕመናን የማይነጣጠሉ አንዱ የሌለውን በደል እና ጭቆና ማየትን የማይሻ ለዘመናት ተከባብረው እና ተቻችለው የኖሩ ወደፊትም የሚኖሩ ህዝቦች ለመሆናቸው አብነት መጥቀስ አያሻም። ዛሬም ኢትዮጵያውያኑ የኦርቶዶክስ ምዕመናን ሳውዲ አረቢያ ያሉብንን የጸሎት ቦታ ጥያቄ ለመፍታት በምናደርገው እቅስቃሴ ግራ ሳይጋቡ ድጋፋቸውን እየገለጹ ያሉ ወገኖቻችንን ስናመሰገን እነዚህ ወገኖች እስከ መጨረሻው ከጎናችን ቆመው አጋርነታቸውን እንደሚገልጹ አንጠራጠረም ። ትግሉ ተጀምሯል !! ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጠም ! « ፀሎታችን በቤታችን» ግዜያዊ አሰባሪ ኮሚቴ ጅዳ ሳውዲ አረቢያ