Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የወረዛ ዕምል ታዛ። (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

10489የወረዛዕምል ታዛ

ቀፎ  የጠነዛ

ጠንባዛ – ጠምዛዛ፤

የዘመን አበሳ

ለዛዛ።

ስንት ፍሬ ሞልቶ

ምርጥ ዘር አግቶ

ተዘሎ ተረስቶ

በቅንቅን ተበልቶ

በጎሳ ተዛብቶ።

ሊቀ ሊቃውነቱ

የቀለም አባቱ

ነበራት ለትብቱ

የቁርጡ – የጥንቱ።

ጭዱ ተከምሮ

በተኩላ ተወሮ

አለቀሰ ዘመን

በባዶ ተዋቅሮ፤

በጭድም ተማሮ

በግለትም አሮ።

ታሪክ እንዲህ ያራል

ትውልድም ይመራል

በቀፎ በረሮ።

ታነባለች እናት

ደም ነፍስ ነግሦባት

ወናነት ቀሶባት

ውሉ ተንፍሶባት።

ክምርና – ድርድር

የጠፍነት – ግብር

የዕብለቱ ሰንበር

መጫወቻ አሰር

አሻንጉሊት ነስር

እስር!

መፍቻ።

  • ግለት ጠብቆ ሲነበብ – የወያኔ ሰፊው መርሁ የነፃነት ትግሉም ያልደረሰብት ምንአልባትም ሳያወቀው እዬተከተለው ያለው ሰፊው ፖሊሲ ነው። ሌላ ቀን ሰፋ ድርጌ እመጠበታለሁ። ሁለተኛው የግለት ላልቶ ሲነበብ በ እሳት መፋምን ለማመልከት ነው። የቃሉ አግባብ በሰምም በወርቅም ያስኬዳል ተጠቅምቤታለሁ።
  • ይመራል። ያስተዳድራል የሚለውን አይደለም ከዚህ ላይ ላማመልክት የፈለግሁት። ይጎመዝዛል የሚለውን ለማመልክት ነው። ትውልድ በደመነፍስ ሲማራ ያሸማቅቃል ውርዴትም ነው ለእኔ በግሌ። ሸምቀቆ ነገር።
  • ታዛ አዎን አቶ ሃይለማርያም ባዶ ቀፎ ናቸው ቀን የሚጠበቅላቸው ዛሬ ያሉ ቢመስላቸውም ወልቀው የሚቀሩ።  ከእንጉልቻቸው ሲባንኑ ይደርሱበታል። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ እሳቸው ትቢያ ናቸው ተራግፈው የሚቀሩ። የቆዬ ሰው ያዬዋል። አሁንም መንፈሳቸውን የወያኔ ማንፌስቶ አብዝቶ ይጸዬፈዋል።  ግዱ ነው ያጠጋጋቸው። በዘነዘናቸው ነው እዬነገዱበት ያለው።
  • የወረዛ እርጥበት ያለው ግን እርጥበቱ እራሱን አሻግቶ ይፍራሳል ጠረኑ እምል ስለሚሆን ለትውልድ የሚቀፍ ይሆናል።

 

 

የእውነት አምላክ ፍርድ ይስጥ!

የበቀል አምላክም ቁጣ ይላክ – ለዕብለተኛው።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>