የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አቶ ሐብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺን ባሳለፍነው ማክሰኞ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ፖለቲከኞቹን በህገ መንግስቱ በተጠቀሰው መሰረት እጃቸውን በያዘበት 48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት ሊያቀርባቸው ባለመቻሉ ጠበቆቻቸው ክስ መመስረታቸው ታውቋል፡፡ ታሳሪዎቹን በማዕከላዊ የማግኘት መብታቸውን የተነፈጉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉና ጠበቃ ገበየሁ ይርዳው በዛሬው ዕለት በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመገኘት ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ያሰራቸውን ሰዎች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲያቀርባቸውና የሚገኙበትንና የተያዙበትን ምክንያት እንዲያስረዳ የክስ ፋይል ከፍተዋል፡፡
↧