ዓረና-መድረክ እሁድ ሐምሌ 06 2006 ዓ/ም በራያ ዓዘቦ ወረዳ ሞኾኒ ከተማ “ዘመቻ ኣብረሃ ደስታ” የሚል መፎክር ያለበት ህዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል።
ዓረና-መድረክ ፖሊሲው፣ ስትራተጂውና ኣማራጭ ሃሳቡ ከራያ ዓዘቦና ኣከባቢው ህዝብ ለመወያየትና ለማስተዋወቅ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተዋል።
ዓረና-መድረክ የሃገራችን የፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ መልካም ኣስተዳደር፣ ሁላቀፍ ልማት፣ የሚድያ ነፃነት፣ ወዘተ ተግዳረቶች በማቅረብ ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ ኣማራጭ ሃሳቦች በማቅረብ ወደፊት ሃገራችን የምትመራበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምን መምሰል እንዳለበት፣ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እውን የሚሆንበት ኣግባብ፣ ባለፈው 17 የትጥቅ ትግል የተከፈለ መስዋእትነትና በኣሁኑ ሰዓት የተገኘው ለውጥ ምን እንደሚመስል ከራያ ህዝብ እንወያያለን።
ጀግናው የራያ ህዝብ የጀንነትና የጀግና ኣድናቂ ነው። የዚህ ህዝባዊ ስብሰባ መጠርያም የኣዲሱ ትውልድ ጀግና የሆነው “ኣብራሃ ደስታ” እንዲሰየም ተደርጓል። ስለዚህ “ዘመቻ ኣብራሃ ደስታ” ከራያ ህዝብ ጋር ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ የምንወያይበትና ኣብረን የምንታገልበት መድረክ ይሆናል።
የዓረና ስራ ኣስፈፃሚ ኣባል የሆነው ኣብራሃ ደስታ በኣሁኑ ሰዓት በኣዲስ ኣበባ ማእከላዊ በመባል የሚታወቀው ማረሚያ ቤት እንደሚገኝ ምንጮች ገልፀዋል።
ዓረና የኢትዮዽያ መንግስት ስለ ኣብራሃ ደስታ ሁኔታ እንዲያስታውቀን እናሳስባለን።
የራያ ዓዘቦና ኣከባቢው ህዝብ በሞኾኒ ህዝባዊ ኣዳራሽ ተገኝቶ ኣማራጫችን እንዲሰማና ሃሳቡን ቢያካፍለን እንላለን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው…!!!
“IT IS SO”