የህብር ሬዲዮ ሰኔ 29 ቀን 2006 ፕሮግራም
<...በአቶ አንዳርጋቸው ከየመን ተላልፎ መሰጠት ላስቆጣው በአገር ውስጥና በውጭ ላለው ኢትዮጵያዊ ግንቦት ሰባት የትግል ጥሪ አቅርቧል ። ይህ ትግል በወያኔ ብቻ ሳይሆን በእንግሊዝና በየመን መንግስታት ላይ የሚደረገውን ተቃውሞ ይጨምራል። በአገር ውስጥና በውጭ የስርዓቱ ደጋፊዎችና ከዚህ ስርዓት ጋር የጥቅም ግንኙነት ያላቸውን የሚመለከት የትግል ጥሪ ነው ሕዝቡ ፈጣንና ተግባራዊ ምላሽ ይሰጣል..>>
አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የግንቦት ሰባት የህዝብ ግንኙነት የድርጅቱን ለሕዝብ የተላለፈ ጥሪ አስመልክቶ ከሰጡን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)
<<...በተናጠል ትግል አያዋጣም በፊት በሐሰት ክስ የግንቦት ሰባት አባል በሚል ከነእስክንድር ፣ከአንዷለም ፣ከእነ ኦባንግ ሜቶ ጋር አስራምስት ዓመት ተፈርዶብኝ ነበር ። ትግል በተደራጀ መንገድ ነው ስለዚህም የአቋም ለውጥ አድርጌ ከአባልነት እስከ አመራር ሰጪነት ለመሳተፍ ድርጅት ለመቀላቀል ነው የአቋም ለውጥ ያደረኩት...>>
ጋዜጠኛ አበበ ገላው በድርጅት ውስጥ ገብቶ ለመታገል መወሰኑን አስመልክቶ ስለ አዲሱ አቋሙ ከሰጠን መግለጫ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የዓለም ዋንጫ ሰሞነኛ ውሎ ከአስገራሚ ክንውኖችና አጓጊ ውጤቶቹ ጋር (ልዩ የስፖርት ዘገባ)
<<...ሕዝቡ አንድ አርጋቸው አንድ አድርገን እያለ ነው...ቁጣችን የአንድ ሰሞን ሆኖ ከዚህ ቀደም ጀግኖችን አስበልተን ቁጭ ብለናል አሁን እንደዚያ መሆን የለበትም ተቃዋሚዎች አንድ ላይ ሕዝቡ አንድ ላይ መቆም አለበት...>>
ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ በሰሜን አሜሪካ የስፖርት በዓል ላይ በአቶ አንዳርጋቸው ተላልፎ መሰጠት ጉዳይ የሕዝቡ ስሜት ምን ይመስል እንደነበር ካደረግንለት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<<...በአንዳርጋቸው ላይ የደረሰው በማናችንም ላይ የደረሰ ጥቃት ነው። ሁላችንም በአንድ ላይ የምንቆምበት እንጂ ይሄ የግንቦት ሰባት፣ይሄ የሸንጎ፣ይሄ የኢህአፓ የሚባልበት አይደለም ጥቃቱ የጋራ ነው...በውጭ የሚገኘውም ኢትዮጵያዊ በጋራ መቆም ከቻለ ብዙ ትርጉም ያለው ተጽኖ ማምጣት ይቻላል..>> ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
ዜናዎቻችን
ሱዳን ባልታወቁ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች አስር ወታደሮቼ ተገደሉ አለች
አርበኞች ግንባር በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የተወሰደው0ን በመቃወም እርምጃ እወስዳለሁ አለ
የኦጋዴን ነጻ አውጭ ከመቶ በላይ የአገዛዙን ወታደሮች መግደሉን አስታወቀ
አዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸውን የአገዛዙ ሰዎች የት እንዳደረሱ ማረጋገጫ እየጠየቅሁ ነው አለ
የቀድሞ ሰራዊት አባላት በቬጋስ ታላቅ ጉባዔ አዳሔዱ
ማህበራቸውን የሚመሰርቱ መሪዎችን መረጡ
ለሕዝባችን ዛሬም አለን ብለዋል
ሌሎችም ዜናዎች አሉ