Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አርቲስት ኪሮስ ዓለማየሁ የክብር ዶክትሬት ሳይሰጠው ቀረ

$
0
0

አብርሃ ደስታ እንደዘገበው የመቐለ የዩኒቨርስቲ የ2006 ዓም የትምህርት ዓመት ዛሬ ቅዳሜ አስመርቋል። በምረቃው ለተወሰኑ ጥሩ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ታዋቂ ግለሰቦች የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ ተጠቅሶ ነበር። ለክብር ዶክትሬት ማዓርግ ከተጠቆሙ (1) አርቲስት ኪሮስ አለማዮሁ፣ (2) ነጋድራስ ገብረሂወት ባይከዳኝ፣ (3) አባ መልአኩ፣ (4) ዶ/ር ታረቀኝ በርሀ ይገኙባቸዋል። ከነዚህ የተጠቆሙ ግለሰቦች በመቐለ ዩኒቨርስቲ ሰኔት የተመረጡና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የተሰጣቸው ነጋድራስ ገብረሂወት ባይከዳኝ፣ አባ መልአኩ እና ዶር ታረቀኝ በርሀ ናቸው። አርቲስት ኪሮስ አለማዮሁ ግን የክብር ዶክትሬቱ ሳይሰጠው ቀርተዋል። ኪሮስ አለማዮሁ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር መቐለ ቅርንጫፍ ነበር የተጠቆመው። ስለ ኪሮስ ስራዎች ከሦስት ሰዓታት በላይ የፈጀ የሙሁራን ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ነበር። ብዙ የመቐለ ወጣቶችም ኪሮስ የክብር ዶክትሬት ይሰጠዋል ብለው ሲጠባበቁ ነበር፤ ይገባው ነበርና።
Kiros alemayehu zehabesha
ኪሮስ አለማዮሁ ለምን ሳይሰጠው እንደቅረ ማወቅ ቀላል ነው። ኪሮስ በህወሓቶች የሚሰጠው ክብርና ስለ አሟሟቱ ማወቅ ዛሬ ለምን የክብር ዶክትሬቱ እንዳልተሰጠው መገመት ይቻላል። ደግሞ የህወሓቶች ባህሪ እናውቀዋለን። አሁን ህወሓቶች ኪሮስን ያስቀሩበት ምክንያት ብዘረዝር የነሱን ያህል ጠባብ እሆናለሁ። ስለዚህ ህወሓቶችን ለመተቸት ብዬ የሰጡትን ምክንያት ብነግራችሁ እነሱ ያሉበት የአውራጃዊነት ጭቃ መርገጤ ነው። ከነሱ ጋር ለመከራከር የነሱን ሐሳብ ማንሳት አለብኝ። የነሱን ሐሳብ ለማንሳት ደግሞ እነሱ ወደሚገኙበት የጠባብነት ደረጃ ራሴን ዝቅ ማድረግ አለብኝ (ከነሱ የተሻልኩ ነኝ እያልኩ ነው፤ ከነሱ የተሻልኩ መሆኔ ለማረጋገጥ ወደነሱ የ አውራጃዊነት ደረጃ መወረድ ያለብኝ አይመስለኝም። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ መዘባረቅ ይቅርብኝ)። መቐለ ዩኒቨርስቲ ለኪሮስ የክብር ዶክትሬት ባይሰጥም እኛ ህዝብ ባለፈው ኪሮስን በዘከርንበት ግዜ ህዝባዊ ክብር ሰጥተነዋል። ከዩኒቨርስቲ ክብር የህዝብ ክብር ይበልጣል ባይ ነኝ። ዩኒቨርስቲም ኮ ከህዝብ አያልፍም።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ለኪሮስ የክብር ዶክትሬት ሳይሰጥ ሲቀር የጎንደር ዩኒቨርስቲ ግን ለ አስቴር አወቀ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል። የመቐለ ዩኒቨርስቲ ኪሮስን አስቀርቶ ለሦስት ሰዎች ብቻ የክብር ዶክትሬት ሲሰጥ የጎንደር ዩንቨርስቲ ግን አስቴር አወቀን ጨምሮ ለ አራት ታዋቂ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል። የጎንደር ዩኒቨርስቲ ለ አስቴር አወቀ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ዶር ሙሉ ዉበቱና አትሌት መሰረት ደፋር የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዩኒቨርስቲው ክብር ቢሰጠውም ባይሰጠውም ኪሮስ አለማዮሁ የትግርኛ ዘፈን ንጉስ ነው።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>