ከሳዲቅ አህመድ
‹‹ፍትህ ይስፈን ንፁሀን ይፈቱ›› የሚሉ ዜጎችን ማሰር የኢፍትሃዊነት ትልቁ ማሳያ ነው! አንዋር አካባቢ ሰግደው የሚመለሱትን ፖሊሶች ለመያዝ እያዋከቡ ነው!
ሀ/ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ፖሊሶች ከደህንነቶች ጋር ሆነው በሰላማዊ ሁኔታ ተቃውሞ አሰምቶ ሲመለስ የነበረውን ህዝብ በመተንኮስ ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ ለማስገባት ያደረጉት ጥረት በህዝቡ ሰላማዊነት ምክንያት ሊከሽፍ ችሏል።አንድ ሰው ይዘው የነበረ ሲሆን ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ አስለቅቆታል።
‹‹አፈና፣ ግፍና ማስገደድ ይቁም!›› በሃይማኖታችን እና በዜግነት መብታችን ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን የሚገልፅ ብርቱ መፈክር