አብርሃ ደስታ
የሐውዜን ህዝብ እንደገና በህወሓት እየተጨፈጨፈ ነው። “ዓረና ነህ፤ ስምህ በዓረና መዝገብ ተገኝቷል” እያሉ ሰለማዊ ሰዎችን እያስፈራሩ ለህወሓት ይቅርታ ጠይቆ እንዲመለስ እያስጠነቀቁ ካልተሳካ ደግሞ በዱላ እየደበደቡ፣ በድንጋይ እየወገሩ፣ ጥያቄ ለሚያነሳ ሰው በፖሊስ እያሳሰሩ፣ ቤቱ እየፈተሹ ይገኛሉ። አንዳንድ በሐውዜን የሚገኙ ሙሁራን “ዳግማይ ጭፍጨፋ” ብለውታል። ዓረና ይህን ተግባር ይቃወማል።
የዓረና አባላት ያልሆኑ ሰዎች ስማቹ ተገኝቷል እየተባሉ የሚሰቃዩበት፣ ስም ዝርዝር ያልላከ ዓረና ስሙ የሚጠፋበት ስርዓት ተፈጥሯል። ደግሞ ዓረና ህጋዊ ፓርቲ አይደለም እንዴ? ሰው ዓረና የመሆን መብት የለውም እንዴ? የሐውዜን ህዝብ የዓረና አባልና ደጋፊ የመሆን መብት የለውም? የዓረና አባል ተብሎ እንዴት ይንገላታል? እንዴት ይታሰራል? የዓረና አባል መሆን ወንጀል መስራት ነውንዴ? ዓረና’ኮ ህጋዊ ፓርቲ ነው።
የህወሓት ስጋት ምን ያህል እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል። የሐውዜን ህዝብ ግን ዳግም እየተጨፈጨፈ ነው። ለህዝብ ካልቆምን ለማን ልንቆም ነው። ወይስ የሐውዜን ህዝብ ሊጨርሱት ፈልገዋል?! እንደ የሰኔው 15, 1980 ዓም ሙከራ!?
ህወሓት ግን ሰፈሩ የበላሹሎ!
https://www.facebook.com/abraha.desta2?fref=nf