ፍኖተ ነፃነት
ወ/ሮ ስንቅነሽ ገብረየስ አንድዬ ልጃቸውን የ1997 ምርጫን ተከትሎ በታጣቂዎች በተተኮሰበት ጥይት በግፍ ተነጥቀዋል፡፡ልጃቸውን አፈር ካለበሱ በኋላ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲን በመቀላቀል ልጃቸውን በግፍ የነጠቃቸውን ስርዓት ሲታገሉ ህይወታቸው እስካለፈበት ቅጽበት ድረስ ቆይተዋል፡፡
‹‹በዚህች አገር የስርዓት ለውጥ ሳልመለከት ሞት እንዳይቀድመኝ›› ይሉ የነበሩት ሰላማዊ ታጋይዋ ባደረባቸው ህመም ለህልፈተ ህይወት ተዳርገው በአዲስ አበባ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡
የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና መላው አባላት በወይዘሮ ስንቅነሽ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ወይዘሮ ስንቅነሽ ሊመከተቱት ይናፍቁት የነበረው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አስተዋእጾ እንዲወጣ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡