Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: 10 አስደንጋጭ የህክምና ስህተቶች

$
0
0

 

የህክምና ስህተቶች በየጊዜው ይከሰታሉ፡፡ እንደውም በአገረ አሜሪካ በየዓመቱ 200 ሺህ ሰዎች ይሞታሉ፡፡ አንዳንዶች በአጋጣሚ የአካል ጉዳት ያገኛቸዋል፤ ወይም ደግሞ ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል፡፡ በእርግጥ ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት እንደማይጠፋ ሁሉ ሐኪሞችና ነርሶችም ሰዎች ናቸውና ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በጣም የማይሆኑ ስህተቶች ወይም ደግሞ በቀላል ጥንቃቄ ሊወገዱ የሚችሉ አስገራሚ ክስተቶች ሲፈፅሙ ይስተዋላል፡፡ ታዲያ ይህ የጤና ነው ማለት ይቻል ይሆን? እስኪ በታሪክ ውስጥ የማይረሱ የሚባሉትን እናንሳ እና የየራሳችንን አስተያየት እንሰንዝር፡፡

 

medical mistakes1. በተሳሳተ ጭንቅላት በኩል የተደረገ ቀዶ ጥገና፡-
በ2007 እንኳን በሮድ አይላንድ ሆስፒታል በሶስት ሰዎች ላይ ትክክለኛ ባልሆነ የጭንቅላት አቅጣጫ ላይ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸዋል፡፡ እንግዲህ ይታያችሁ በአንጎል ላይ መሳሳት ማለት ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል፡፡ ሁለቱ ስህተቶች ወዲያውኑ በመታወቃቸው ፈጣን ማስተካከያ ተደርጎላቸዋል፡፡ የሶስተኛው ታማሚ ግን ወዲያው ባለመታወቁ ከሶስት ሳምንት በኋላ በ86 ዓመታቸው ለህልፈት በቅተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም የሐኪሞቹ ፈቃድ ለሁለት ወራት ያህል እንዲታገድ ሆኗል፡፡

 

2. የተሳሳተ የልብ ዝውውር፡-
በ2003 በዲውክ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ የተደረገው ስህተት ደግሞ ጄሲካ ሳንቲለን እየተባለ ለሚጠራው የ17 ዓመት ልጅ የተደረገና ከደም አይነቱ ጋር የማይሄድና የተሳሳተ የልብ ዝውውር ነበር፡፡ በዚህ የተነሳም የልጁ ሰውነት ወዲያውኑ መስራት አቆመ፤ ከፍተኛ የአንጎል ጉዳትም ደረሰበት፡፡ ይሁን እንጂ ወዲያውኑ በትክክለኛ ልብና ሳንባ ለመተካትና ችግሩን ለማስተካከል ጥረት ቢደረግም ልጁን ከሞት ማትረፍ አልተቻለም፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሆስፒታሉ የትኛውንም አይነት ዝውውር ከማድረጉ በፊት ሁለት ጊዜ የማረጋገጥ ደንብን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

 

3. የሁለት ልጆችን ደም ያፈሰሰ መድኃኒት 
በፊልም አክተሩ ዴኒስ ኩይድና ሚስቱ ኪምበርሌዊ ባፊንግተን መንትያ ልጆችን መታቀፋቸው አስደሳች ቢሆንም ከፍተኛ የሚዲያ ትኩረትን የሳበው ግን ልጆቹ ከፍተኛ መጠን ያለውና ሔፓሪን የተባለውን አደገኛ መድኃኒት በስህተት መውሰዳቸውን ተከትሎ ባጋጠማቸው አደጋ የተነሳ ነበር፡፡ እነዚህ መንትያ ህፃናት እንደተወለዱ ላደረባቸው ኢንፌክሽን በደም ስር የሚወሰድ አንቲባዮቲክ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን የደም ስራቸው አካባቢ የደም መጓጎል እንዳይፈጠር 10 ዩኒት ሔፓሪን መውሰድ ሲገባቸው ለትልልቅ ሰዎች የሚሰጥ 10,000 ዩኒት ሔፓሪን በስህተት እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ በዚህ የተነሳም ደማቸው በከፍተኛ ደረጃ በመቅጠኑ ከሰውነታቸው ውጭም ሆነ ውስጥ የደም ፍሰት አጋጥሟቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በሚገርም ገጠመኝ ከ41 ሰዓታት በኋላ ደማቸው መወፈር በመቻሉ ከሞት ተርፈዋል፡፡ ስህተቱ የተፈጠረው በሐኪም የታዘዘውን የልጆች ሔፓሪን አሳስታ የሰጠችው በፋርማሲዋ ምክንያት ነው፡፡ የልጆችም ሆነ የአዋቂዎች ሔፓሪን ብልቃጥ ደግሞ ተመሳሳይ በመሆኑ ነርሷ ልብ እንዳትል አድርጓል ይላል ዘገባው፡፡

 

4. ቆለጥ ያሳጣ ስህተት
ቤንጃሚን ሁትን በመባል የሚጠራ የአየር ኃይል ባልደረባ ወደ ህክምና ያመራው ከሁለቱ የቆለጥ ፍሬዎቹ ውስጥ የግራው በመሟሸሹና በውስጡም የካንሰር ሕዋስ ሳይዝ እንዳልቀረ በሐኪም ስለተጠረጠረ ነበር፡፡ ይህ የቆለጥ ፍሬ ቢወገድም በአንዱ መውለድ ይችላል፤ የወንድ የዘር ፍሬም (sperm) ማምረት ያስችለዋል፡፡ በመሆኑም በቀዶ ጥገና እንዲወገድለት ቆዶ ህክምና ተደርጎለት ሲወጣ ግን የተወገደው የቆለጥ ፍሬ የግራው ሳይሆን ጤናማውን የቀኙ ሆኖ ነበር የተገኘው፡፡ በዚህም ስህተት ይህ ግለሰብና ሚስቱ የሎስ አንጀለስን ሆስፒታል በመክሰሳቸው 200 ሺህ ዶላር ካሳ አስከፍለዋል፡፡

 

5. እግር እግር የሚል ስህተት

 

እጅግ አስገራሚ የተባለውና የ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግራ አጋቢ ስህተት የተፈጠረው በ52 ዓመቱ ደሊኪንግ ላይ ነበር፡፡ በ1995 በጣም ለተጎዳው እግሩ መቆረጥ እንዳለበት የተነገረው ኪንግ በቀዳጁ ሐኪሙ ስህተት የተነሳ ግን የተቆረጠው ሌላኛው እግሩ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ኪንግ በመጨረሻ ሁለቱንም እግሩን እንዲያጠያ ሆኗል፡፡ ስህተቱ የተፈጠረው ግለሰቡን ለቀዶ ህክምና ዝግጁ እንዲሆን ባደረጉት ነርሶች ነበር፡፡ ለቀዶ ህክምና ዝግጁ እንዲሆንና አስፈላጊው አጠባና ምልክት የተደረገው በጤናማው ላይ በመሆኑ ሐኪሙ በስህተት ሊቆርጡት በቅተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ፈቃዳቸው ለ6 ወር የታገደ ሲሆን ለኪንግም የ250 ሺህ ዶላር ካሳ ከፍለዋል፡፡ በነገራችን ላይ በእኛም አገር ይህ መሰል ስህተት አጋጥሟል፤ በአዲስ አበባ ውስጥ፡፡

 

6. በተሳሳተ ወንድ ያረገዘችው ሴት

 

ሁለት ባልና ሚስት በተለመደው የግበረ ስጋ ግንኙነት መውለድ ያልቻሉ በመሆናቸው በልዩ የሰው ሰራሽ አረባብ ቴክኖሎጂ፣ እንዲፀንሱ ወደስነ ተዋልዶ ክሊኒክ ይሄዳሉ፡፡ እነዚህ ባልና ሚስት ቶማስና ናንሲ በመባል የሚጠሩ ሲሆን የሀኪሙ ኃላፊነት ቶማስን የዘር ሕዋስ (sperm) ከናንሲ የዘር ህዋስ (ova) ጋር በብልቃጥ ውስጥ በማደባለቅና ፅንስን እንዲፈጠር በማገዝ በመጨረሻ ወደናንሲ ማህፀን እንዲረገዝ ማዛወር ነበር፡፡ በዚህም ጥበብ ያረገዘችው ናንሲ የወለደቻት ልጅ የቆዳ ቀለሟ ጠይም መሆኑ ግራ አጋባት፡፡ ናንሲም ሆነች ባሏ በዘራቸው ፈረንጅ እንጂ ጥቁር አልነበሩም፡፡ በዚህ የተነሳ የአባትነት የደም ምርመራ (DNA) ለሶስት ጊዜ ሲደረግ በሁሉም ላይ ያሳየው ጄሲካ የተባለችው ህፃን አባቷ የእናቷ ባል አልነበረም፡፡ ማለትም ጄሲካ አንድሪው ልጅ አይደለችም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትም ሐኪሙ የናንሲን እንቁላል ሲያዋህድ የተጠቀመው የባሏን ሳይሆን በተመሳሳይ ችግር የመጣን የአንድ ጥቁር ስፐርምን በስህተት በመጠቀም ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው የአንድሪው ስፐርም የጥቁሩን ሚስት አስረግዟል ማለት ነው፡፡ በስህተት የተቀያየሩ ባሎች እንበላቸው ይሆን?

 

7. አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ

 

ይህ ደግሞ በ84 ዓመቷ አዛውንት ላይ የተደረገ ስህተት ሲሆን በቀዶ ጥገና እንዲወገድ የተወሰነው የሐሞት ከረጢቷ ሆኖ ሳለ ተቆርጦ የተጣለው ግን የቀኝ ኩላሊቷ ነበር፡፡ ይህ የሆነው የላብራቶሪ ውጤቱን አሳስቶ በማንበቡ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሳይቆረጥ የተተወው የሐሞት ከረጢት በራሱ ጊዜ ድኖ ጤነኛ መሆኑም ሌላኛው አስገራሚ ክስተት ነበር፡፡ መጀመሪያውኑም ቀዶ ጥገና አያስፈልገውም ነበርና፡፡ በዚህ ተነሳም ሐኪሙ ከፍተኛ ካሳ የከፈለ ሲሆን ከዚህ ክስተት በኋላ ያለ ሌላ ሐኪም የበላይ ተመልካችነት ቀዶ ጥገና እንዳያከናውን ታግዷል፡፡

 

8. በሆድ ውስጥ የተረሳ መጎተቻ

 

በሲያትል በሚገኘው የዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር የተደረገው ስህተት ደግሞ በሆድ ውስጥ ዕጢ ለማውጣት በተደረገ ቀዶ ጥገና 30 ሳንቲ ሜትር የሚረዝም አጋዥ መጎተቻ (retractor) መሳሪያ ሊረሳ መቻሉ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ወዲያው ስህተት መፈጠሩ በመታወቁ መሳሪያው እንዲወጣ ቢደረግም ለታካሚው ግን 97 ሺህ ዶላር ካሳ ከመክፈል አልዳኑም፡፡

 

9. በስህተት ራሱን ያጠፋው ግለሰብ

 

ሼርማን ሲሞር የተባለ ግለሰብ በከፍተኛ የሆድ ህመም ሲሰቃይ የነበረ ሲሆን ለዚህም ሲባል ሆዱን በግልፅ ለማየትና መነሻውን ለማወቅ ቀዶ ህክምና ይደረግለታል፡፡ ይሁን እንጂ ቀዶ ጥገናው ከተካሄደ እስከ መጀመሪያዎቹ 16 ደቂቃዎች የሰመመን ማደንዘዣ አልተሰጠውም፡፡ ማደንዘዣው ከተሰጠው በኋላ ወዲያው ሊያደነዝዘው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ህመም ይጋለጣል፡፡ ይሁን እንጂ በተወሰነ መልኩ ስለደነዘዘ ከሐኪሞቹ ጋር መነጋገርና ስቃዩን ማስረዳት አልቻለም ነበር፡፡ ከሆስፒታል ከወጣ በኋላ ቀዶ ጥገናውን እያስታወሰ በመረበሹ የተነሳ ክፉኛ በመሰቃየቱ ራሱን ሊያጠፋ ችሏል፡፡

 

10. ጡት አልባ ያደረገ ውሳኔ
ዳሪ ኤሰን በመባል የምትጠራ የ35 ዓመት ሴት ጡቶቿ ካንሰር አለባቸው በሚል ምርመራ የተነሳ ሁለቱም እንዲቆረጡ ይታዘዛል፡፡ ይሁን እንጂ ኤሰን አይቆረጡብኝም ብትልም ከሐኪም በላይ አይደለሽም በሚል በመጨረሻ እንዲቆረጡ ይደረጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱም ጡቶቿ ምንም አይነት ካንሰር አልነበረባቸውም፡፡ በዚህ ስህተት የተነሳ ክስ የመሰረተችው ኤሰን ከፍተኛ ካሳ ተቀብላለች፡፡ ጡቶቿንም በገንዘቡ ማስመለስ ችላለች፤ ሰው ሰራሽ ጡቶች በማስገጠም፡፡

medical mistakes


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles