የህብር ሬዲዮ ሰኔ 15 ቀን 2006 ፕሮግራም
<...በአዋሳ አንድነት ሰልፉን እንዳያካሂድ ጫና የተፈጠረው ከከተማውና ከአካባቢው የፓርቲውን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ተከትሎ ሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ይሳተፋል ብለው ስላሰቡ ፍርሃት ገብቷቸው ነው። በቀጣዩ ሳምንት ወይም ከዚያ በሁዋላ በዚያው አዋሳ ሰልፍ እንጠራለን ከፈለጉ ድጋሚ ሁላችንንም ሰብስበው ይሰሩን ...> አቶ ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ም/የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለህብር ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<<... የዓለም የስደተኞች ቀን ሲታሰብ የስደተኛው ጉዳይ እንዳይረሳ ስደተኛው እዚህ መጥቶ እርዳታ ጠባቂ ሳይሆን ታታሪ ሰራተኛ ለአሜሪካ ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋጽዎ እንዳለው ለማሳየት ጭምር ነው...>>
አቶ ረዳ መሐሪ የአፍሪካ ኮሞኒቲ ሴንተር ማኔጂንግ ዳይሬክተር የዓለም የስደተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ ካደረግነው ቆይታ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<...በኡጋንዳ ያለው ስደተኛ የራሱን ማህበር እንዳያቁዋቁም በኢትዮጵአው አገዛዝ ሰዎች ሀሰተኛ ክስ ተከልክሎ ነበር አሁን ግን ማህበራችንን ልናቋቁም ነው...ዩ.ኡን.ኤች.ሲ.አር የስደተኛውን ችግር በአግባቡ ተረድቶ ሶስተኛ አገር እየሰጠ አይደለም ...>
ጋዜጠኛ ደረጄ በጋሻው የቀድሞ የአስኳል ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በኡጋንዳ የዓለም የስደተኞች ቀንና የኢትዮጵያውያን ስደት አስመልክቶ ከሰጠን ማብራሪያ(ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ያዳምጡ)
ዋልድባን እንታደግ ቡድን ዘንድሮም እየተንቀሳቀሰ ነው
ዜናዎቻችን
የተባበሩት መንግስታት በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማጣራት ልዩ የአጥኚ ቡድን እንዲልክ ተጠየቀ
በአዋሳ የአንድነትን ሰልፍ ለማደናቀፍ የጸጥታ ሰዎች ቅስቀሳ ያደረጉ 32 የፓርቲውን አባላትና አመራሮች በልዩ ልዩ ፖሊስ ጣቢያ አስረዋል
አንድነት ዛሬ በጫና ያላካሄደውን ሰልፍ አዋሳ ላይ ደግሞ ሊጠራ ነው
ኦብነግ በአፋርና በሶማሌ ተወላጆች መካከል የተፈጠረው ውጥረት እንዳሳሰበው ገለጸ
ለግጭቱ የአገዛዙ እጅ አለበት ብሏል
በመኢአድና በአንድነት አባላት ላይ ጥቃቱ ቀጥሏል
የመኢአድ አባል በካድሬዎች ተደብድበው ሞቱ
የእንግሊዝ መንግስት ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ጫትን ሕገወጥ አደረገ
በአዲሱ ሕግ ጫት ያዘዋወረ የ14 ዓመት እስር ይጠብቀዋል
ከኦሮሚያ ክልል በሺህ የሚቆጠሩ የአማርና ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በሀይል ከአካባቢው እንዲለቁ ተደርገዋል
ድብደባና ግድያ የተፈጸመባቸው አሉ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ