Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: ይልቅ የኮክን (Peach)ጥቅም ልንገርሽ * ለዕድሜ፤ ለዓይን፤ ለቆዳ ውበትና ሌሎችም አስፈላጊሽ ነው

$
0
0

peaches-pile
በሊሊ ሞገስ

 ኮክ (Peach) መገኛው ቻይና ነው፡፡ አሌክሳንደር ዘግሬት ከቻይና ወደ ግሪክ እንዳመጣውም ይነገራል፡፡ ለአሜሪካ ያስተዋወቁት ደግመኮ ስፔናዊያን ናቸው፡፡ በዛፍ ላይ የሚበቅለው ኮክ ሶስት የዕድገት ደረጃዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው እስከ 50ኛው ቀን ይዘልቃል፤ ይህ ወቅት ተክሉ በፍጥነት የሚያድግበት ጊዜ ነው፡፡ በሁለተኛው ደረጃ በተክሉ ውስጠኛ ክፍል (ጠጠሩ) መጠንከር ይጀምራል፡፡ ነገር ግን የዕድገት ደረጃው ዝግ ያለ ነው፡፡ ‹‹final sweet›› ተብሎ በሚጠራው የመጨረሻ የእድገት ደረጃ ተክሉ ተወዳጅ ቀለሙን ይይዛል፡፡ ውሃ ይቋጥራል፣ ስኳር የሚይዘውም በዚህ ወቅት ነው፡፡

የጤና ጠቀሜታዎቹ

ዕድሜ ቀጥል ነው

ቻይናዊያን የኮክን የጤና ጠቀሜታዎች የተረዱት 10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነበር፡፡ ጠጠሩን ለህክምና ተግባር ከማዋላቸው ባለፈ ኮክን ‹‹longevity peach›› ብለው ይጠሩታል- ዕድሜ ቀጥሉ ኮክ እንደማለት፡፡ ዘመናዊው የህክምና ሳይንስ ጥንታዊ ቻይናዊያን ኮክን ለህክምና ያውሉበት የነበረው ዘዴ እና የሚሰጠው ጠቀሜታ ትክክል እንደሆነ መስክሯል፡፡

በቫይታሚን እና ሚኒራሎች የበለፀገ ነው

ኮክ በበርካታ ቫይታሚኖች እና ሚኖራሎች የበለፀገ ቢሆንም ዕድሜ ማራዘሙ የሚታወቀው ግን በውስጡ የያዘው ፖታሲየም ነው፡፡ ከኮክ ከፍተኛ መጠን ያለው ፖታሲየም ይገኛል፡፡ በሰውነታችን ውስጥ የፖታሲየም እጥረት ከተከሰተ ድካም፣ ጭንቀት፣ የጡንቻ መድከም፣ የቆዳ ችግሮች፣ ደካማ የማስታወስ አቅም፣ የደም ግፊት፣ የተለያዩ የልብ ህመሞች እና በጆሮዎች ውስጥ የመርገብገብ ድምፅ መሰማት ዋና ዋና ምልክቶቹ ናቸው፡፡ የሆድ ዕቃ ህመሞች፣ ተቅማጥና ከፍተኛ ላብ የሚታይባቸው ሰዎች የፖታሲየም እጥረት ሊያጋጥማቸውና ከላይ በተጠቀሱት ህመሞች በቀላሉ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

ቤታ ካሮቲን- ቫይታሚን ኤ

ኮክን ለጤና ተስማሚ ካደረጉት ንጥረ ነገሮች ውስጥ ቤታ ካሮቲን አንዱ ነው፡፡ ሰውነታችን ቤታ ካሮቲንን ወደ ቫይታሚን ኤ ይቀይረዋል፡፡ ቫይታሚን ኤ ደግሞ ለበርካታ የሰውነታችን ስራዎች አስፈላጊ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ ለንባብ የበቃ አንድ ጥናት በሰውነታቸው ውስጥ ከፍተኛ የቫይታሚን ኤ ያላቸው ሰዎች የዓይን ሞራ የመጠቃት ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው ብሏል፡፡ ሌሎች ጥናቶች ደግሞ ከፍተኛ የቫይታሚን ኤ መጠን ሰውነት ውስጥ ሲገኝ አደገኛ የሳንባ ህመምን ሊያስወግድ እንደሚችል በአይጦች ላይ የተደረጉ ጥናቶች አሳይተዋል ይላሉ፡፡

የዓይንን ጤንነት ይጠብቃል

Lycopene እና Lutein ተብለው የሚጠሩ መደባቸው ከ ካሮቲኖች የሆኑ ንጥረ ነገሮች፣ ልክ እንደ ቤታ ካሮቲን ኮክ የምናውቀው ቀለም እንዲኖው ይረዳሉ፡፡ በነዚህ ሁለት ንጥረ ነገሮች ላይ የተካሄዱ በርካታ ጥናቶች የሁለቱ በበቂ መጠን መገኘት ከዕድሜ ጋር በተያያዘ የሚከሰትን የአይን መድከም፣ ካንሰርን እና የልብ በሽታዎችን ይከላከላል፡፡

በፋይበር የበለፀገ ነው

ኮክ ከፍተኛ የፋይበበር ይዞታ አለው፡፡ ሁለት አይነት ፋይበሮች ናቸው ያሉት… በውሃ የሚሟሟውና የማይሟሟው፡፡ የሚሟሟው ለልብ ጤንነት ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ውሃ ስለማይዝ ነው፣ ይህ ደግሞ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ ይህም አንጀት ውስጥ ተከማችተው የሚገኙ ተረፈ ምርቶችን ለማስወገድ ያስችላል፡፡ በዚህ የተነሳም የአንጀት ካንሰር እንዳይከሰት ይረዳል፡፡ የአንጀት ግድግዳ መጽዳት ሰውነታችን ንጥረ ነገሮችን በተገቢው ሁኔታ እንዲጠቀም ከማስቻሉም በላይ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡ በውሃ የማይሟሟው ፋይበርም ቢሆን ጠቀሜታ አለው… የኮሌስትሮል መጠንን ዝቅ ያደርጋል፡፡

የቫይታሚን ሲ ዋነኛ መገኛ ብርቱኳን እንደሆነ የማያውቅ ሰው ጥቂት ነው፡፡ ኮክም በቫይታሚን የበለፀገ ነው፡፡ ቫይታሚን ሲ በሽታ ተከላካይ ሲሆን የበሽታ መከላከል አቅምን በማጎልበት ካንሰርን ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል አይረን አለው፡፡

የቆዳ ውበትን ይጨምራል

ኮክ በውስጡ የያዛቸው ሚኒራሎችና ቫይታሚኖች ቆዳችንን ጤናማ ከማድረጋቸውም በላይ ቀለሙን እና ማራኪነቱን እንደጠቀ እንዲዘልቅ ያደርጋሉ፡፡

ነውጠኛ ህፃናትን ያረጋጋል

የኮክ ተክል አበባው ከስኳርና ከማር ጋር ተፈልቶ እንዲጠጡ ሲደረግ እረፍት የለሽ ህፃናት እንዲረጋጉ የማድረግ አቅም አለው፡፡ 80 በመቶ የኮክ ክፍል በውሃ የተሸፈነ ሲሆን ጥሩ የፋይበር መገኛም ነው፡፡ ክብደታቸውን ለመቀነስ የሚፈልጉ ሰዎች አዘውትረው ኮክብ ቢመገቡ ይጠቀማሉ፡፡

የጥገኛ ተዋህሲያን ፀር

ኮክ በአንጀት ግድግዳ ተለጥፈው የሚኖሩ ፓራሳይቶችንና ትላትሎችን ጠራርጎ በማስወገዱ ይታወቃል፡፡ በፓራሳይቶችና ትላትሎች የተነሳ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮችም መፍትሄ ሰጪ ነው፡፡

የሆድን ጤንን ይጠብቃል

ኮክን በቋሚነት መመገብ የሆድን ጤንነት ይጠብቃል፣ ድርቀትንም ያስወግዳል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከኮክ የምናገኛቸው አንቲ አክሲዳንቶች (በሽታ ተከላካዮች) የትኛውም አይነት የካንሰር ዝርያ በሰውነታችን ውስጥ እባጭ እንዳይፈጥር ይከላከላሉ፡፡

ለበርካታ ህመሞች ፈውስ ነው

ኮክን በቋሚነት በመመገብ ብቻ ልንከላከላቸው ወይንም ልንፈውሳቸው የምንችላቸው በበርካታ ለህይወት አስጊ እንዲሁም ሌሎች ህመሞችና በሽታዎች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በደም ውስጥ እና ሰውነታችን ቲሹዎች ውስጥ የአልካሊኒቲ መጠን ሲቀንስ የሚከሰተው acidosis የደም ማነስ፣ አስም፣ የፊኛ እና የኩላሊት ጠጠሮች፣ ሮንካይትስ፣ ሆድ ድርቀት፣ ደረቅ ሳል፣ የጨጓራ ህመም፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ደካማ የምግብ መዋሀድ ስርዓት እና ለሌሎችም ህመሞችና በሽታዎች ፈውስና ተከላካይ ነው፡፡

በእያንዳንዱ 100 ግራም ኮክ ውስጥ የምናገኘው የካሎሪ መጠን 46 ብቻ በመሆኑ ክብደታቸውን ለመቀነስ የሚያስቡ ሰዎች በቋሚነት ቢወስዱት ክብደታቸው እንዲጨምር አያደርግም፡፡

ኮክ ትላትሎችን ከአንጀት አካባቢ ማስወገዱ ብቻ ሳይሆን እነዚህ ፓራሳይቶች ተደጋጋሚ ጥቃት እንዳይደርስብንና በሚያስከትሉት ጉዳት የተነሳ ለሌሎች በሽታዎች እንዳንጋለጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣል፡፡

ኮክ በተፈጥሮው ቶሎ ቶሎ የሚያሸና (diuretic) በመሆኑ የኩላሊትን ስራ ያቃልላል፣ ሽንት ቶሎ ቶሎ እንዲወገድ በማድረግ ፈሳሽ እንዳይቋጠር ያደርጋል፤ ይህም የመገጣጠሚያ አካላት ላይ የሚደርሰውን ህመምና ስቃይ ይቀንሳል፡፡ ኮክ Carotenoids በተሰኘው የቫይታሚን ኤ አይነት የበለፀገ ነው፡፡ ይህም ጎጂ የፀሐይ ጨረሮች በአይኖቻችን ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ይከላከልልናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

የኮክ ፍሬ ለሰው ልጅ ጤና ጎጂ የሆኑትን Cryogenic glycosides የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች ሲሰባበሩ ወደ hydrogen cyanide gases ይቀየራሉ፡፡

ይህ ዘገባ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 63 ታትሞ ወጥቷል።

ለፈለጉት የጤና ዘገባ Tenaadam.com

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>