Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ፀረ ሙስና ኮሚሽን የምድር ባቡር የድሬዳዋ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ

$
0
0

112የፌደራሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የቀድሞ የኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር ኩባንያ የድሬዳዋ ተጠሪንና አራት ሌሎች የአመራር አባላትን፣ በሙስና ወንጀል በመጠርጠር በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡

ከድሬዳዋ በተገኘ መረጃ መሠረት ሰኔ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት የቀድሞው ዋና ተጠሪ አቶ አየለ ወልደ ዮሐንስ፣ የሐዲድና የሕንፃ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ገበየሁ፣ የሳብ ተሳሳብ ኃላፊ የነበሩት አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም፣ የአኬሌ ወርክሾፕ ኃላፊ አቶ ፍቅረ ማርያም አበባየሁና የንግድና ትራንስፖርት ተጠሪ የነበሩት አቶ ደርብ ጉደታ መሆናቸው ታውቋል፡፡

አቶ አየለን ጨምሮ አምስቱም ተጠርጣሪዎች በድሬዳዋ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀርበዋል፡፡ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ሥልጣንን ያላግባብ በመጠቀም፣ የመንግሥትን ይዞታ ለግለሰቦች በሕገወጥ መንገድ በማከራየትና የመንግሥት የግዢ ሥርዓት ሳይጠብቁ ግዢ በመፈጸም ክስ መመሥረቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባለፈው ሚያዝያ ወር በተመሳሳይ የድሬዳዋ ፖሊስና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ፖሊስ በጋራ በመሆን የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ጣዕመ ተኪኤን፣ ጉቦ በመቀበል ወንጀል በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ባረፉበት ሆቴል በቁጥጥር ሥራ ማዋላቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Source: Ethiopian Reporter


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>