Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ፖሊስ በሐዋሳ ከተማ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አሰረ- የታሰሩትንም ደህንነት ማወቅ አልተቻለም

$
0
0

ፖሊስ በሐዋሳ ከተማ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አሰረ

1050አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በነገው እለት ማለትም ሰኔ 15/2006 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በራሪ ወረቀት በማደል ፤ ፖስተር በመለጠፍና በሞንታርቦ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አስሯል፡፡ በሞንታርቦ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)በነገው እለት በሀዋሳ ሀተማ ለሚያደርገውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ፖስተር በመለጠፍ፡በራሪ ወረቀት በማደልና በሞንታርቦ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ተይዘው በተለያዩ በከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዊች የሚገኙ ቢሆንም ማንም እንዳይጠይቃቸው በመደረጉ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም፡፡የሀዋሳ ከተማ ከተማ ፖሊስ መምርያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ስማቸውን መግለፅ እንደማይፈልጉና ማንም መጠየቅ እንደማይችል እንዲሁም መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነርን ስለሁኔታው ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

 

በእስር ላይ የሚገኙት አባላት የሞባይል ስልካቸውን ተቀሙ

1048974አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በነገው እለት ማለትም ሰኔ 15/2006 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ በፖሊስ ተይዘው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እንዲሁም በባህል አዳራሽ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙ የአንድነት አባላት ከማንም ጋር እንዳይገናኙ የሞባይል ስልካቸውን ተቀሙ፡፡ከስልካቸው በተጨማሪም በራሪ ወረቀቶቻቸውን ፖሊስ በሀይል ቀምተዋል፡፡

10464338_655647427853528_5549276093091202318_n 10390200_655645774520360_6136971251416251946_n 10487183_655644054520532_1488061453046983959_n\

1041

10


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>