ከሥርጉተ ሥላሴ 20.06.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
…. ለቀጣዩ ቀናት
…. ውል ብሏል ለውል
…. ሽውታ ለናፍቆት
ሕትምት!
አደራውን ልኳል
ወገኑን – ተማምኗል
አርበኝነት ሆኗል፤
ተጥዷል!
የብዕር አባቱ
80 ነው ባቱ
ብራና እትብቱ
ትህትና ነው ቤቱ
በኽረነቱ!
የቁምነገር ሃብቱ
ፍልስፍናው በርቱ!
ጽናቱ – ስበቱ
ትዕግስቱ – ውበቱ
ማሰብ ነው ዕለቱ
ቀን – ተሌት፣ – ህብስቱ፤
ተስፋ – ማ – ሟተቱ
ያሥራቱ!
ይናገረው – ዘመን
ይዳኘው – መንገዱን፤
ይሄው ነው ዕውነቱ፤
ድርጊት ባለቤቱ
ችሎቱ!
የግንባር ሥጋ ነው
ለሃቅ ያደረ ነው።
መሠረተ – ህብር
የሥጦታው – ደንበር
የመከራ ገበር።
ጥማቱ …
ፍጥረቱ —
ፈቅዶ – ህማማቱ
ፍቅረ – መለኮቱ
ህይወቱን – ለናቱ
ውስጡን – ለልዕልቱ
መክሊቱ!
አልፋ ነው መለከት
ኦሜጋማ – ስብከት
አብነት!
ተግባሩ ነው ፍልፍል
ፏፋቴ ፈለፈል
ተናግሮታል ወለል
ዓለም መስክሮታል፤
መንፈስ – መዝኖታል
ምርጥ ሰው ብሎታል።
ሰማይም ሰጥቶታል
ቀድሞ ቀብቶታል፤
ሁሉን ሽልሞታል
ቅብዕ —– ሰክኖለታል!
ለአባ ትርጉም ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእንኳን ደስአለህ ሥጦታ፤ 19.06.2014 ዙሪክ ሙዚዬም – ፓርክ።