ተመስገን ደሳለኝ
ዕለቱ የሁለት ሺ ሶስት ዓመተ ምህረት የመስቀል በዓል የተከበረበት ማግስት፤ ሰሜናዊቷ የኤርትራ አዋሳኝ ወልቃይት ገና ከእንቅልፏ ሙሉ ለሙሉ ባለመንቃቷ፣ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ጎፈሪያቸው የተንጨ(ባረረ ፋኖዎች በውስጧ ካሉ ተቋማት ወደ አንዱ እያመሩ ስለመሆኑ የጠረጠረች አትመስልም፤ ከኤርትራ የተነሱት ፋኖዎች መዳረሻ በወረዳዋ ታዋቂ የሆነው አወርቅ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመሆኑ፤ ማንም ልብ ሳይላቸው ልክ እዚያው እንደደረሱ፣ ከፊሎቹ በሰለጠነ ወታደራዊ ስልት ትምህርት ቤቱን ከአጥር ውጪ በመክበብ ድንገተኛ ጥቃት የሚሰነዝር ኃይል ከመጣ ለመከላከል ሲያደፍጡ፤ የተቀሩት ደግሞ ወደ ውስጥ በመግባት በግቢው የሚገኙ መምህራን ሜዳው ላይ እንዲሰበሰቡ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ፤ በጥቂት ደቂቃዎችም ውስጥ ሁሉም በተባለበት ቦታ ተሰበሰበ፤ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በዕቅዱ መሰረት መፈፀሙን በጥንቃቄ ሲከታተል የነበረው የቡድኑ መሪ በቅድሚያ ስለራሱና ጓደኞቹ ማንነት እና ስለወከሉት ድርጅት አጭር ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ፣ የትግሉን ዓላማ በስፋት አብራርቶ አስረዳ፤ ሌሎች ጓዶቹም የፖለቲካ -—[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-