Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: አፍሪካ- ‹‹ክሮስ ኤክስፖርት እናደርጋለን›› –የዓለም ዋንጫ ዕይታ በገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

$
0
0

ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

(ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ)

(ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ)


በዚህ አለም ዋንጫ ላይ የአፍሪካን ቡድኖች ስመለከት ምንም እድገትና ተስፋ አላየሁባቸውም፡፡ በአውሮፓ ስመ ጥር ተጨዋቾች ይዘው በእንቅስቃሴ ለመብልጥና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሸነፍ የሚያስችል ነገር አይታይባቸውም፡፡ጋና ከአሜሪካ ጋር ሲጫወት ተጀምሮ እስኪያልቅ ጋና ክሮስ ሲያደርጉ ነበር፡፡ በቀኝ በኩል ሮጠው ይመጡና ያሻማሉ፡፡እንደገናም ያሻማሉ …አሁም ያሻማሉ፡፡ገና ወደዚያ ሲመጡ እንደሚያሻሙ ያስታውቃል፡፡ ሻሞ መሆኑን የአሜሪካ ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆኑ ሜዳ ያለውም ተመልካችን በቴሌቪዥን መስኮት ስር ያለው ሁሉ ያውቃሉ ፡፡ የአሜሪካ ተጨዋቾች ረጃጅም ናቸው፡፡ ዝላይም ከጋና ይሻላሉ ፡፡ኳሱን አሜሪካኖች እንደሚያገኙ እየታወቀ ክሮስ ሲያደርጉ ለምን ይሄን እንደማይቀይሩ ግልጽ አልነበረም፡፡ያንን ሁሉ ክሮስ አሜሪካኖች በቴስታ መመለሳቸው ብቻ ሳይሆን ጋና እየተጠቃ የነበረው ራሳቸው ክሮስ አድርገው ከሚመለሰው ኳስ መሆኑ ሲታይ ዋጋ ቢስ ክሮስ ነበር፡፡የሚገርመው በቀኝ ያን ሁሉ ክሮስ አድርገው ባከነና አንድ ኳስ በግራ ሄደው ልጁ ስላልተመቸው ለአዩ በተረከዝ አቀበለው፡፡አዩ አገባው፡፡አሜሪካኖቹ እንዲህ አይነቱ አመጣጥ ይቸግራቸዋል፡፡ልጁ ለአዩ በተረከዝ ያቀበለው ስላልተመቸው ነው እንጅ ክሮስ ነበር የሚያደርገው፡፡መቀባበሉ የሚያዋጣ ቢሆንም ጋና የተቃኘው በክሮስ ነው፡፡እርግጥኛ ነኝ አሰልጣኙ በተረከዝ በመስጠቱ‹‹እንዲህ አይነት የቄንጥ አጨዋወት አልፈልግም ››እንደሚሉት ነው፡፡መቀባበሉ ከእዚያ በኋላ ሳይደገም በክሮስ ዘለቀ፤ አለቀ፤ ተጠናቀቀ፡፡ ካሜሩን ክሮስ፤ ናይጀሪያ ክሮስ…..የአፍሪካ ቡድኖች ክሮስ ኤክስፖርት የሚደርጉ ይመስል ስራቸው ይሄ ሆነ፡፡ ናይጀሪያ ከደካማ ኢራን ጋር አየነው፡፡ አንድ ተጨዋች ማለፍ እንኳን ቸግሯቸው ኳሱ ሲበላሽ የኛ ቡድን ቀሽም መሆኑ እንጂ ናይጀሪያ በዚህ አቋሙ ማለፍ አልበነበረበትም፡ናይጀሪያ ነጣቂ ቡድን ነው ፡፡ጉልበተኛና በመደምሰስ አጨዋወት ላይ ያተኮረ ሆኖ እነርሱ ጠንካራ በሆኑበት በጉልበት ጨዋታ ገባንና ተበልጠን ተሸነፍን፡፡ የተሸነፍነው ለመሸነፍ ስለገባን ነው፡፡እኛ ጥሩ በሆንበት ነገር ናይጀሪያን ብነገጥም እንጥለው ነበር፡፡አሁን ያየሁት ናይጀሪያ ደካማ ነው፡፡ ጨዋታወም አይስብም፡፡
song
…..በ1998 አለም ዋንጫ የነበረው ናይጀሪያ ከመቼውም የተሻለ ነው፡፡ ከፊት የሚመሩት እነካኑ፤ፊኒዲ፤ኦኮቻና ነበሩ፡፡ ካኑና ፊኒዲ መሮጥ አይችሉም፡፡ በረጅሙ ሲጣልላቸው አይታጉሉም ይተውታል፡፡ወደፊት ተቀባብለው ሲሄዱ ጎል እንደሚያገቡ፤ሊያገቡ እንደሚችሉና ተጋጣሚን ስጋት ውስጥ አንደሚከቱት ያስታውቃል፡፡እነርሱ መቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን እዚያ ቡድን ውስጥ ኳስ የማይችሉትን እንደግድግዳ ተጠቅመው እያስገቡ ይጫወቱ ነበር ፡፡ይሄ ቡድን ከሁለት አመት በፊት በአትላንታ ኦሎምፒክ በብራዚል 3ለ0 ተመርቶ 4ለ3 ሲያሸንፍ በክሮስ ሳይሆን እነካኑ የኳስ ሂደቱን ስላሳመሩት ነው፡፡ ቡድኑ ወደ ፊት ሲሄድ እንደሚያገባና እንደሚያስጨንቀ ያስታውቃል፡፡ያሁኑ ቡድን ኳስ ይዞ ለማጥቃት ሲሄድ ያ ኳስ እነርሱ ላይ ተመልሶ ጫና እንደሚፈጥር ያስታውቃል፡፡

……ካሜሩን ነገሮችን ሁሉ በጉልበት ለመጠቀም ይፈልጋሉ፡፡ በጉልበት ቢበልጡም፤ ደምስሰው ኳስ ቢቀሙም ያገኙትን ኳስ በትክክል ማቀበል አቅቷቸው ለባለጋራ እየሰጡ መጨረስ ብቻ ሳይሆን ተስፋ ያለው ነገር እንኳን አልታየባቸውም፡፡ያገኙትን ኳስ በማባከን ጨረሱ፡፡ ክሮሽያ 4ለ0 ሲያሸንፋቸው ጨዋታው ይደገም ቢባል እንኳን ካሜሩን በልጦ ላመሸነፍ እንኳን የሚችልበት ነገር አልነበረም፡፡ጉልበት ላይ መመስረታቸው ነገሮችን የሚቃኙበት እውቀት አልነበራቸውም፡፡ በክርን መትቶ በቀይ የወጣውም አፈጻጸሙን ሀይል ላይ ማድረጉ ቡድኑ የተመሰረተበትን ነገር ለማሳየት ይመስላል፡፡ ካሜሩን እንዲህ እንዲጫወት ጋና ክሮስ እንዲያደርግ ናይጀሪያ የግርግር ጨዋታን እንዲመርጥ መደረጉ አፍሪካ ውስጥ በእውቀት የሚጫወት ሰው ያለመኖሩ ሳይሆን አሰልጣኞች የመረጡላቸው አጨዋወት እንደሆነ ያሳያል፡፡ካሜሩን ፍጹም ከኳስ ውጭ ሆኖ ክሮስ ብቻ ሳይሆን ርግጫን ማዕከል ያደረገ ነበር፡፡1990አለም ዋንጫ የነበረው ካሜሩን መራገጥና ኳስ መጠለዝ ብቻ ነበር ፡፡ቡድኑ መልክ የሚይዘው ሮጀር ሚላ ሲገባ ነው፡፡ ሚላ እድሜው 38 ነበር፡፡ መሮጥ አይችልም (ከሌሎቹ ጋር ሲነጻጸር)ጉልበትአይጠቀምም፡፡፡ በተለይ ከእንግሊዝ ጋር ሲፋለጡ ተቀይሮ ገብቶ ጓደኞቹን እንደግድግዳ እየተጠቀመ ኳስ እየሰጠና እየተቀበለ እንግሊዝን ምጥ ውስጥ አስገብቶ ነበር፡፡ እሱ ሲገባ ክሮስ ቀረና ሚላ ላይ ተመሰረተ፡፡እሱ ሱገባ ካሜሩን ያስፈራለል ፡፡እሱ ቤንች ላይ ሆኖ ካሜሩን ይጠልዛል፡፡ ጉልበት ለመንጠቅ እንጅ ኳስ ለመቀባበልና ተቀባብሎ ባለጋራን ለማስጨነቅ አይጠቅም፡፡በካሜሩንና በእንግሊዝ ጨዋታ ላይ ሜዳውን ሚላና ጋስኮኝ ተቆጣጥረውት ነበር፡፡በተለይ እንግሊዝ ጋስኮኝ ላይ ተንጠልጥላ ጥሩ ለመምሰል ሞክራ ነበር፡፡ እንግሊዞች ከዚህ በፊትና አሁን ድረስ ከኋላ የተገኘውን ኳስ ለአጥቂ መጣልና ክሮስ በማድረግ የሚታወቁ ቢሆንም ጋስኮኝ በግሉ ይሄን እንዲቀይሩ ምኪንያት ሆኖ ነበር፡፡ ጋስኮኝ ደፋርነቱ ብቻ ሳይሆን ኳስ መቻሉ ከተከላካዮች ጋር ሄዶ በድፍረት ይቀበላል፡፡ ፊታቸውን አዙረው ለመሄድ ለተዘጋጁት እየጠራ ይሰጣል፡፡ እንደገና ይቀበላል፡፡ እንዲህ ሲያደርግ መሀል ሜዳው ከሁለት ወደ አራትና አምስት እያሳደገ የሰው ቁጥር እየጨመረ ወደ ፊት ፎርም ሆነው ስለሚሄዱ ማጥቃቱን በብዙ ቁጥር ከማሳደጉ ሌላ ባለጋራ ኳስ እንዳያገኙ አስችሎ ነበር፡፡ በታሪኳ እንግሊዝ ኳስ ተጫወተች የሚባለው ያኔ ነበር፡፡ይህም ጋስኮኝ ፎርም ባደራጋቸው ቅኝት ውስጥ በመግባታቸው ነው፡፡ ከዚያ በኋላ እነ ቤካም መጡ፡፡ ቤካም የመሀል ሜዳውን በቁጥር ማሳደግ ቀርቶ ያገኘውን በረጀሙ ለአጥቂ ሲጥል ጋዜጠኞችም አደነቁት ፡፡ያ ኳስ ግን እየመጣ እንግሊዝን ጫና ውስጥ እንደሚከታት እንዴት እንደጠፋቸው አስገራሚ ነበር፡፡ ጋስኮኝ መሀል ሜዳው ላይ ሁለት የነበሩትን ወደ አምስት ያሳድጋል፡፡ ቤካም መሀል ሜዳ አራት የነበሩት ወደ ሁለት ያወርድና ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ እንግሊዝና በእውቀት መጫወት እስከዛሬ ተጣልተው‹‹ጊዜ ከሚባክን ኳስ ይባክን››በሚለው ስልት ቶሎ ጎል ጋር ለመድረስ ያገኙትን ከየትም እየጠለዙና ተጠልዞ በሚመለሰው ኳስ እጠየተጠቁ አሉ ፡፡

………. ሰሞኑን አልጀሪያንም አየሁት፡፡አልጀሪያ ዘጠና ደቂቃ ሲከለከል ለአንድ አጥቂ እየጣሉ የተጣለለትም ሳያገኝ እንዲሁ ባከኑ፡፡መርተውም ተመርተውም ሲከላከሉ አፍሪካ የግርግር ቡድን እንደሆኑ እያስመሰከሩ ነው፡፡ በ12ተኛው አለም ዋንጫ ጀርመንን የመሰለ ሀያል ቡድን አልጀሪያ መጫወቻ አድርጎት ነበር፡፡ የተከላከለው ጀርመን ነበር፡፡አልጀሪያ 2ለ1 እየመሩ ያጠቁ ነበር፡፡አጥቂው መስመር ሳላ አሳድ፤ላካድራ ቤሉሚና ራባህ ማጃር እየተመራ በኳስ ቅብብል ጀርመንን አርበድበደውት ነበር፡፡የዛሬው አልጀሪያ ግን እነዚያን መምስል ቀርቶ ማስታውስ አልቻለም፡፡በተለያ አሳድን የመሰለ ቴክኒካል ተጫዋች አልጀሪያ ቀርቶ ለአፍሪካ እስካሁን አላፈራችም ፡፡ያሁኑ አልጀሪያ ፈጣንና ተከታካች ነው፡፡እንዲህ ሲባል ደግሞ ቀላል ነው ተብሎ በነሀሴ አዲስ አበባ ላይ የሚደረገው ግጥሚያ….ግን ያን ግዜ እንዴት ነው መግጠም ያለብን?

በሩጫ..በርግጫ…..በጡጫ..በቁንጥጫ…በቡጥጫ….ፈጣንና ጉልበትን ጠንከር ያሉ ስለሆነ ማስቸገራቸው አይቀርም፡፡ በተለይ ብቻ ለብቻ ካገኙ አስቸጋሪ ናቸው፡፡ቤልጀም ኳስ ስለሚቀባበል ነው ያስቸገራቸው፡፡ቤሌጅየም በጉልበት ቢገባ አልጀሪያ ማሸነፍ ይችል ነበር፡፡አሁንም እኛ በጉልበት ላይ ከተመሰረትን አልጀሪያ ደስ ነው የሚለው‹‹በምፈልገወው መንገድ መጣችሁልኝ›› ብሎ ፈገግ ብሎ እንደሚቀበለን ነው፡፡የኛ ትልቁ ችግራችን የኛን ጠንካራ ነገርና የነርሱን ደካማ ነገር ሳናውቅ መግጠማችን ነው፡፡ አሁን እንደተለመደው በጉልበት ለመቋቋም መሞከራችን አይቀርም፡፡ በጉልበት አንችላቸውም ካሁኑ በኳስ ለመብለጥ መዘጋጀት ካልቻልን ያገኘውን ኳስ እየሰጠን ለመንጠቅ መሯሯጥ ነው፡፡……….
spain

ስፔይን ወይስ እንግሊዝ?

ስፔይን ትላንትና በቺሊ ተሸንፎ ከአለም ዋንጫ በጊዜ ተሰናብቶ ተመልካች ሆኗል፡፡ ዣቪ ቤንች ላይ ነበር፡፡እዚያወ ቤንች ተቀምጦ ሲመለከት‹‹ይሄ ቡድን እንግሊዝ ነው ስፔይን?›› ብሎ እንደሚጠይቅ ይገመታል፡፡ በስፔይን ማሊያ እንግሊዝ፡፡ ፈጣንና በመልሶ ማጥቃት እንዴት እንደሚጫወቱ አሳዩን፡፡ ከቲኪ ታካ ወጥተው በተቃራኒው ሲሄዱ እንዳላዋጣቸው በዚህ ሁለት ጨዋታ አይተውታል፡፡ በቲኪ ታካ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫና የአለምን ዋንጫ አግኝተዋል፡፡አሁን ግን ቲኪ ታካን እየተገበሩ እንዳልሆነ እየታየ ነው፡፡ የቲኪ ታካ ዘመን አበቃለት እየተባለ ነው፡፡ቲኪ ታካን እየተጫወቱ ከተበለጡ ነው ዘመኑ አበቃለት የሚባለው፡፡

ስፔይን በተለይ በዚህ ሁለትጨዋታ ቲኪ ታካ ውስጥ የሉበትም፡፡ ኮስታ ላይ ነው የተመሰረቱት ‹‹ሁሉም ነገር ወደ ኮስታ›› ብለው ጎል ፍለጋ ማዕከል አድገው ነበር የገቡት፡፡ቲኪ ታካን እየተጫወቱ የአውሮፓና አለም ዋንጫ ሲወስዱ ባለጋራ እንደይተገብሩ ሲሞክር አልቻለም፡፡አሁን ግን የሚተገብሩት ከቲኪ ታካ ውጭ ባለ ነገር ነው፡፡ አሁን እነርሱ ቲኪ ታካን እየተጫወቱ ተጋጣሚ ይሄን እንዳይተገብሩ ስለከለካቸው አልነበረም፡፡እንደዚህ ቢሆን ኖሮ ተቸግረው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እነሱ ሳይከለከሉ ከዚህ ነገር ወጥተዋል፡፡አሁን ድሮ ስፔን ወደነበረችበት አጨዋወት ነው የገቡት፡፡በዚህ ደግሞ ጉልበት ስለሌላቸው(ከሌላው ጋር በንጽጽር) ተጋጣሚን መብለጥ አልቻሉም፡፡ ቶሎ ቶሎ ነው ወደ ግብ የሚሄዱት(ይሄ ደግሞ የቲኪ ታካ ባህሪ አይደለም)፡፡አካሄዳቸው ደግሞ በግል ነው፡፡ሲፈጥኑ ይበታተናሉ፡፡ ሲበታተኑ በግል ይገኛሉ፡፡ በግል ሲገኙ ደግሞ ባለጋራ ለመንጠቅ አመቺ ሆነለት፡፡በፊት አንድ ሰው ኳስ ሲይዝ ብዙ ተቀባይ አለለት። ተቀባይ እንዳለው እሱ ስለሚያውቅ ወደ ግል አይገባም፡፡ ኳሱም ከአደጋ የተጠበቀ ነው፡፡አሁን ግን አንድ ሰው ኳስ ሲይዝ ከሚረዳው ይልቅ ነጣቂው ቀድሞ ይደርሰበታ፤ ይሄን ግዜ ወደ ግል ይገባል፡፡ ኢኔስታ ብዙ ኳስ ተነጥቋል፡፡በፊት ኳስ ሲነዳ ሌሎችን ለማስለቀቅ ቢሆንም ተቀባይ አለው፡፡ አሁን ግን የሚቀበለው ስለሌለ አፍርጠው ይቀበሉታል፡፡ ስፔይን በቲኪ ታካ አጨዋወት ግብ ጋር በብዙ ንክኪ ይደርሳሉ፡አሁን አሎንሶን ሆነ ከኋላ ያለው ራሞስ ኮስታን ነው የሚፈልጉት፡፡ ምክንያቱም ግብ ቶሎ ይፈልጋሉ፡፡ግቡን በሂደት ሳይሆን ከዚያ ውጭ ባለው ነገር ነው የሚፈልጉት፡፡ለዚህም ነው ወደ ፊት ቶሎ ቶሎ የሚጥሉት፡፡ ይሄ ደግሞ ቡድኑ እንዲበታተን ምከንያት ሆኗል፡፡ሰሞኑን ባደረጉት እንቅስቃሴ አንድ አክሽን ተጀምሮ እስኪያልቅ ሶስትና አራት ሰው ቢሳተፍ ነው፡ሌላው ሲባክን ይውላል፡፡በፊት ቲኪ ታካ ሲያደርጉ አንድ አክሽን አስኪያልቅ ሃያ እና ሀያ አምሰት ሰው ይሳተፋል(አንድ ሰው ሁለትና ሶሰት ጊዜ ስለሚነካ)..አሁን ቶሎ ስለሚሄዱ ኳስ የሰጠ ባለበት ለሚቀር ኳሱ ባለጋራ ሜዳ ሲገባ የሰው ቁጥር ያንስና ይነጠቃሉ፡፡ስፔን አሁን ባለጋራውን ሊያጠቃ በሚሄድበት መንገድ እነርሱም በዚሁ መንገፈድ ስለሚገኙ ተቸገሩ፡፡(ከቺሊ ጋር ተመሳሳይ አጨዋወት ውስጥ ስለገቡ)፡፡ ስፔይን በራሱ መንገድ ሳይሆን በቺሊ አጨዋወት ስለገባ ቺሊ አልተቸገረም፡፡ስፔይን ሁለቱንም አጨዋወት አይተውታል፡፡(ቲኪ ታካውና ከዚያ በተቃኒ ያለውን) የትኛው እንደሚያዋጣ አይጠፋቸውም፡፡ ግን እንዴት እንመልሰው ነው ጥያቄው፡፡አሁን ኳስ ከኋላ ሲበላሽ እርምት ተብሎ የሚወሰደው ኳሱን ከዚያ ማራቅ ነው በፊት፡፡ ከኋላ ሲበላሽ ተጫዋቹ የተበላሸበት ረዳት በማጣቱ እንደሆነ ያውቁና ብዙ ሆነው በመምጣት በመርዳት ተያይዘው ወደ ፊት ይሄዳሉ፡፡አሁን ነገሮች በግል ለማረም ይሄዳሉ፡፡ከተጨዋች ይልቅ የነጣቂ ቁጥር እያበዙ ነው፡፡ በፊት ብዙ ሆነው ስለሚሄዱ ቦታዎችን እየዘጉ ስለሚጓዙ ቢነጠቁ እንኳን እዚያው ይነጥቃሉ፡፡ ተጋጣሚም ቢነጥቅ መውጫ አያገኝም፡፡አሁን ተበታትነው ስለሚሄዱ ቡዙ ክፍተት ስላለ በተከፈተው ቦታ ይጠቃሉ፡፡በዚህ ሁለት ጨዋታ ቡድኑ ከቲኪ ታካ ወጥቶ ታይቷል፡፡የትኛው እንደሚያዋጣ እነርሱ ያወቁታል፡፡ ጀርመን በጉልበት አጨዋወት የታወቀ ነው፡፡በጉልበት ጨዋታ በአውሮፓና በአለም ሻምፒዮነ ተደጋጋሚ ዋንጫ ወስደውበታል ፡፡ነገር ግን ዋንጫ የወሰዱበትን የጉልበት ጨዋታ ትተው ወደ ኳስ ቅብብል መጥተዋል፡፡አሁን በያዙት ጨዋታ ዋንጫ ባያገኙም አልተውትም፡፡
england world cup
ዋንጫ ባገኙበት የጉልበት ጨዋታ ማንም አያደንቃቸውም ነበር፡፡የአለም ህዝብ ጀርመንን ማንሳት የጀመረው ከደቡብ አፍሪካ የአለም ዋነጫ በኋላ ነው፡፡ይሄንን እነርሱም አውቀውታል፡፡ባለፈው አለም ዋንጫ ሻምፒዮና ባይሆኑበትም ይሄን ጨዋታ አያዋጣም ብለው አልተውትም ፡፡እነርሱ ይሄን ጨዋታ ሲተገብሩ ተጋጣሚ እንዳይጫወቱ ሊያደርግ አልቻለም፡፡በዚህ ጨዋታ ለማሸነፍ አልተቸገሩም፡፡ይሄን አጨዋወት ራሳቸው ካልተውት በስተቀር ባለጋራ ለማቆም ይቸገራል፡፡ በነገራችን ላይ ጀርመኖች በተፈጥሮ ቴክኒካል ተጫዋች ባይኖራቸውም ኳስ መቀባበል ከጉልበት አጨዋወት ይሻላል ብላው እየሞከሩም እየበለጡበትም ነው፡፡( መሀል ላይ ከኢትዮጵያ ሰፈር ውስጥ 3 የሚያህል ተጫዋች ቢወሰዱ እንደ ስፔን ጥግ ይደረሱ ነበር) ስፔይን ግን በራሱ ነው ከዚህ ነገር የወጣው፡፡የህብረት ስራ ማህበሩ ከፈረሰ ወደ ግል ይዞታ ተጠቃለለ ማለት ነው፡፡ስፔን በፊትም እነ ዣቪ ላይ ነው የተመሰረተው እንጂ አሰልጣኙ ለዚህ የሚሆን ተጫዋች መርጦ ስልጠናውን ሰጥቶ የሰራው ቡድን አይደለም፡፡ ቢሆን ኖሮ ይህንኑ እንቅስቃሴ የሚቀጥሉ ልጆች እያስገባ ከዚያ ነገር እንዳይወጡ ያደርግ ነበር፡፡ አጨዋወቱን ቢፈልገውም የሚያስገባቸው ልጆች እንቅስቃሴውን የሚያሳድጉ ሳይሆን የሚያበላሹ ናቸው፡፡ እንግሊዝ በ1990 አንድ ጋስኮኝ ለብቻው ፎርም አድርጎ ኳስ እንዲጫወቱ ያደርግ ነበር፡፡ ጋስኮኝ ሲወጣና ቤካም ሲመጣ ነገሩ ተለያየ፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles