Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሪያድ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት በገንዘብ እጥረት 3000 ህጻናትን በትኖ ሊዘጋ ነው * ወላጆች ለልጆቻቸው መበተን ዲፕሎማቱን ተጠያቂ ያደርጋሉ

$
0
0

Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ

በስደት ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በተመጣጣኝ ዋጋ ተቀብሎ በማስተማር ከፍተኛ አስተዋጾ እያበረከተ የሚገኘው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ላለትፉት ሁለት አስርት አመታት ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚመኩበት እና የሚኮሩበት ተቋም ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በወላጆች እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች መሃከል በተፈጠረው አለመግባባት ት/ቤቱ እንደተቛም ህልውናውን ጠብቆ ወደፊት መቀጠል እንደተሳነው የሚናገሩ ምንጮች ። ሰሞኑን የት/ቤቱ የኪራይ ዘመን እና የት/ቤቱ ህጋዊ ፈቃድ የግዜ ገደብ በመጠናቀቁን ተከትሎ በተቋሙ ህልውና ላይ የጋረጠው አደጋ አሳስቢ መሆኑን በመጥቀስ ከወራት በፊት በማን አለብኝነት ት/ቤቱን በበላይነት ተቆጣጥረው እንዳሻቸው ሲዘውሩት የከረሙት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሹማምንቶች በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ተከሰቱ የተባሉትን የተወሳሰቡ ችገሮች ደረጃ በደረጃ መቅረፍ ተስኗቸው እራስቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን የፌታችን አርብ ጁን 13 2014 አስቸኳይ የወላጆች ስብሰባ መጥራታቸውን ይገልጻሉ።

Saudi Arabia ethiopian school

በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን አቀነባሪነት በዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር አስፈጻሚነት ወላጆች በት/ቤቱ ጉዳይ አንድነት እንዳይፈጥሩ በብሄር ከፋፍለው በማጋጨት ዲፕሎማቱ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በሾማቸው የቦርድ አባላት ያለምንም ኦዴት የት/ቤቱ ገቢ እና ወጪው ሳይታወቅ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ « ሪያል» ዘረፋ እንደተፈፀመበት የሚናገሩ እንዚህ ምንጮች ዛሬ ት/ቤቱ አመታዊ ኪራይ መክፈል ተስኖት ጉዳዩን ወደ ወላጆች ማምጣት እራስን ከተጠያቂነት ለማዳን ከሚደረግ እሩጫ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ይናገራሉ። 3000 የሚሆኑ የስደተኛውን ማህበረሰብ ልጆች እንደሚያስተናገድ የሚነገርለት ይህ ት/ቤት ከእያንዳንዱ ተማሪ በወር እስከ 3 መቶ ሪያል በነፍስ ወከፍ እንደሚሰበስብ የሚገልጹት ውስጥ አዋቂዎች የት/ቤቱ ወረሃዊው ገቢ ብቻ ት/ቤቱ የራሱ የሆነ ህንጻ በማስገንባት ከኪራይ ነጻ መሆን ያስችለው እንደነበር አስታውሰው ከባለቤቱ በላይ አዋቂ ሆነው ት/ቤቱን በሞግዜትነት በሃይል ሲያስተዳደሩ የከረሙት እነዚህ ዲፕሎማቶች የት/ቤቱ ወላጆች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በአንድ ወቅት ት/ቤቱን ከኪራይ ጥገኝነት ለመላቀቅ የራሴ ነው ብለው የሚመኩበትን ት/ቤት ለማስገንባት እንቅስቃሴ ላይ እያሉ በአምባሳደር መሃመድ ሃስነ ተዕዛዝ መታገዳቸውን ይናገራሉ ። ይህ በዚህ እንዳለ ለዚህ ተግባር የሚውል ከወላጆች ከአካባቢው ማህበረሰብ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከነበረው 10 ሚልዮን ሪያል « በአሁኑ የኢትዮጵያ ምንዛሪ ከ50 ሚልዮን የሚበልጥ ብር » ውስጥ ግማሽ ያህሉ መሰብሰቡን የሚያስታውሱ ወላጆች ለገዘቡ ደህነት ሲባል በወቅቱ በአምባስደር መሃመድ ሃሰን ስም ከ 3 አመት በፌት አንድ ሳአውዲ አረቢያ የሚገኝ ባንክ ቤት ገቢ መሆኑን ይገልጻሉ። ዛሬ ት/ቤቱ እንደዚህ አይነት የተወሳሰቡ ችገሮች ውስጥ ባለበት ወቅት አመታዊ የኪራይ ገንዘብ አጥቶ አደጋ ላይ መውደቁን ለወላጆች ለማርዳት ዲፕሎማቱ እያሰሙ ያለው ጩሀት ተቀባይነት የሌለው እና ከ3000 በላይ የሆኑ ህጻናትን ሜዳ ላይ በትኖ ት/ቤቱን ለመዝጋት የሚደረገው ጥረት ከጀርባው ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ይነገራል ።

ከዚህ ባሻገር ዘንድሮ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን አዋጅ ለመተግበር ማንኛውም መምሀር የመኖሪያ ፈቃዱ በት/ቤቱ ሰር እንዲሆን ለማስቻል ት/ቤቱን በእጅ አዙር በባለቤትነት የተቆጣጠሩት ዲፕሎማቶች በጀመሩት ዘመቻ ከት/ቤቱ ካዝና አህዙ በትክከል የማይታወቅ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ያለምንም ማስረጃ ህገወጥ በሆነ መንገድ ወጪ መደረጉን የሚገልጹት ለጉዳይ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለመምህራኑ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ተመድቦል ተብሎ ለይስሙላ በቦርድ አባላቱ ከተነገረው 70 ሺህ ሪያል እና ለኮሚኒቲው ካፍቴርያ ድጎማ በብደር መልክ ተሰጥቷል ተብሎ ከት/ቤቱ ካዝና በሚስጠር ውጪ ከተድረገው ከ2 መቶ ዘጠናሺህ ሪያል ወይም « ከግማሽ ሚልዮን ብር » በተጨማሪ ቁጥሩ በወል የማይታውቅ ጥሬ ገንዘብ የት እንደገባ እና ለምን አገልግሎት እንደዋለ በግልጽ እንደማይታወቅ ይገልጻሉ ።
Saudi Arabia ethiopian school 2

ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በተለያዩ ዝቅተኛ ስራዎች ላይ ተመደበው ከሚሰሩ የውጭ ሃገር ዜጎች ያነስ ደሞዝ እይተከፈላቸው የስደት አለሙን ህይወታቸውን ለማሸነፍ የሚባዝኑት የት/ቤቱ መምህራን እና ሰራተኞች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን በት/ቤቱ ሰር ለማድረግ ከያንዳንዱ መመህራን የወር ደሞዝ እስከ ሁለትሺህ እና ከዛ በላይ መቆረጡን ያረጋገጡ ምንጮች መምህራኑ ህጋዊ ለመሆን ባላቸው ጉጉት ከሆድ ከማታልፍ ደሞዛቸው በየወሩ የህን ያህል ከፈሉ እይተባለ የሚጣልባቸው እዳ ከወር ደሞዛቸው ዝቅተኝነት ጋር ተዳምሮ በኖራቸው ያስከተለውን ቀውስ ለመታደግ ተጨማሪ ገቢ ፍለጋ በትርፍ ግዜያቸው የተለያዩ ተማሪዎችን በክፍያ በማስጠናት አሊያም ያለ እረፍት በተለያዩ የጉለብት ስራዎች ላይ ለምሰማራት መገደዳቸው በት/ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ አሉታዊ ተፀእኖ በማሳደሩ ወላጆች በት/ቤቱ ላይ የነበራቸው ተስፋ መጨለሙ ይነገራል። ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ አረቢያ ት/ሚንስቴር መ/ቤት ቀደም ብሎ ማንኛውም ተቋም በስሩ ት/ቤቶችን መከፈት ከፈለገ ጥራቱን የጠበቀ በሳውዲ አረቢያ የት/ሚ/ር ህግ መሰረት የተለያዩ ማስፈርቶችን ያሞላ ከኪራይ ነጻ የሆነ የግል ህንጻ ሊኖረው እንደሚገባ ባወጣው መመሪያ መስረት በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒ ት/ቤት ዲዛይኑ ለመጋዘን መዋል የሚገባው የመጸዳጃ እና የተማሪ እረፍት ቦታዎችን ያላሞላ ከመሆኑም በላይ ህጻናቱ ይማሩበታል የሚባለው ህንጻ በማርጀቱ በተማሪዎቹ ህይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አሰቃቂ አደጋ ከግመት በማስገባት የሳውዲ እሳት አደጋ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ከፍል ከሳውዲ ትምህርት ሚ/ር ጋር በመተባበር የት/ቤቱ ፈቃድ እንዲሰረዝ መወሰናቸውን ተከትሎ ት/ቤቱ በቀጣይ የትምህረት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱን መቀጠል እንደማይቸል ከት/ቤቱ የሚወጡ ሚስጥራዊ መረጃዎች ያመለክታሉ ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>