Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ልዩ ስሙ ዱንቻ አማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ተፈናቀሉ ‪

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

በጋምቤላ ክልል ከቴፒ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ጎደሬ ልዩ ስሙ ዳንቻ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚኖሩ እና በተለያየ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አማርኛ ተናጋሪ ኢዮጵያውያንን ከሃገራችን ውጡልም በማለት ማፈናቀል መጀመሩን ከአከባቢው የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
news
ከሶስት ቀን በፊት በለሰለሰ መልኩ የተጀመረው እና በመዠንገር የወያኔ ቅጥረኛ ካድሬዎች የሚመራው የማፈናቀል ድርጊት በአሁኑ ወቅት ወደ ግጭት ተለውጦ ሃይልን በመጠቀም ላይ ሲሆኑ ከአከባቢው የሚኖሩ ውጡ የተባሉ አባወራዎች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ንብረቶቻቸውን በመተው ወደ ቴፒ ከተማ እየተሰደዱ መሆኑን ታውቋል።

በዛሬው እለት የአማርኛ ተናጋሪ ዜጎችን መኖሪያ በ እሳት በመለኮስ ያቃጠሉ ሲሆን በአከባቢው የሚሰጠው የሚኒስትሪ ፈተና መቋረጡን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል። ትምህርት ቤቶችን እና የመንግስት መስሪያቤቶች የተዘጉ ሲሆን በ3 ኦራል መኪኖች መጥቶ ከተማው እና ገጠራማ አከባቢዎች ላይ የፈሰሰው የወያኔ የጦር ሰራዊት ግጭቱን ከማባበስ ውጪ ምንም አይነት መረጋጋት ሊፈጥር ያልቻለ ሲሆን ወታደሮችን ባዩ ጊዜ የአከባቢው ካድሬዎች =ጭራሽ ብሶባቸው ዜጎችን ሲያሳድዱ ተስተውሏል። ሲሉ ምንጮቹ የላኩልን መረጃ ይጠቁማል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles