6:00 ሰዓት / 5:00 PM ደብረ ጽዮን ከአዲስ አበባ፣ አዳማ ጋር የቴሌኮሚኒኬሽን መስመር ዘግቶነው የዋለዉ።ኔትዎርኩ እንደተለቀቀ፣ አሊያም የሰልፉ አስተባባሪዎች የነበረዉን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶዎችና ቪዲዮዎችን ይዘው አዲስ አበባ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሲመለሱ ይፋ ይሆናል። ከጠዋቱ 5:45 ሰዓት / 4:45 PM የአዳማዉ ሰልፍም በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። ፎቶዎችና ቪዲዮች እንደደረሱን እንለቃለን። በመኢአድ ጽ/ቤት ተደራዳሪዎች ፊርማቸውን እያሰፈሩ ነው። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የፊርማ ስነ-ስርዓቱ ይጠናቀቃል። ቀደም ብለን ለመጥቀስ እንደሞከርነው፣ አቶ አበባዉ መሃሪ የመኢአድ ሊቀመንበር ንግግር እያደረጉ፣ ድንገት ከዉጭ የድንጋይ እሩምታ በጽ/ቤቱ ላይ ዘነበ። ዱርዬዎች ለመረበሽ ሞክረዋል። በዚሁ ሂደትም በስብሰባዉ የነበሩት የአንድነት የፋይናንስ ክፍል ሃላፊ አዮ ጸጋዬ አላምረው በድንጋይ ተፈንክተዋል። መኢአድና አንድነት በዝግጅቱ ወቅት ፖሊስ ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀው የነበረ ቢሆን፣ ፖሊሲ በስፋራው አልተገኘም። ሕግና ስርዓት የሚያስጠበቀ ፖሊሲ ሳይሆን የተላኩት ድርዬዎች ነበሩ። ምናልባትም ፖሊሶቹ እራሳቸው የፖሊስ ልብሳቸውን አዉልቀው መጥተዉም ልሆን ይችላል። ተጨማሪ የደብረ ማርቆስ ፎቶ ! ቪዲዮዎች እንደደረሱን ይፋ እናደርጋለን። ከጠዋቱ 5:30 ሰዓት / 4:30 PM የደብረ ማርቆሱ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። አንዲት ጠጠር አልተወረወርችም። በንብረትም ሆነ በሰው ላይ ጉዳይ አልደረሰም። ብአደኖች «ሰልፉ ሕገ ወጥ ነው። ይረበሻል»ሲሉ ነበር። ነገር ግን ከሰላሳ ሺህ በላይ የሚሆን ህዝብ ድምጹን በሰላም አሰምቶ፣ በሰልም ተበትኗል። አቶ አበባዉ መሐሪ ንግግር ሊያደርጉ ባለበት ወቅት፣ ከዉጭ ድንጋይ በመወርወር ለመረበሽ ሙከራ ተደርጓል። የአቶ አበባዉ ንግግር ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ነበር። የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላ ፣ አቶ ጸጋዬ አላምረው በአገዛዙ ከተላኩ ዱርዬዎች በተወረወር ድንጋይ ፈንክቷቸዋል። አቶ አበባው ንግግራቸው ቀጥለዋል። አቶ አበባዉ «መዋድ ብቻ በቂ አይደለም። ለሌላው አርዓያ በመሆን ትግሉን በጥንካሬ መመራት አለብን» ብለዋል። ከጠዋቱ 5:15 ሰዓት / 4:15PM በአዳራሹ የተጠሩ እንግዶ፣ የፖለቲክ ድርጅት መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች ስፋራቸዉን ይዘዋል። በመኢአድ ጽ/ቤት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ የአንድነት ሊቀመንበር ንግግር አድርገው ጨርሰዋል። የፓርቲዎች የተናጥል ጉዞ የአምባገነኖችን እድሜ ያራዘመ ነው ሲሉ እንጂነር ግዛቸው አብሮ መስራት ድላን እንደሚያፋጥን ተናግረዋል። «ሁሉም ለአንዱ፣ አንዱ ለሁሉም መታገል አለበት» ኢንጂነር ግዛቸው አንዱዋለም አራጌ መኢአድና አንድነት እንዲዋሃዱ ብጥረት ያደርግ እንደነበረ የገለጹት ኢንጂነር ግዛቸው አንዱዋለም በዛሬው ቀን በሚሆነው ነገር በጣም ይደሰታል ብለዋል። አቶ አበባዉ መሐሪ ንግግር ሊያደርጉ ነው። ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት / 4:00 PM የደብረ ማርቆሱ ሰልፍ እየተጠናቀቀ ነው። በአዳማም እንደዚሁ። በኔትዎርክ ችግር አዳማ ስላለው ሰልፍ ዝርዝር ዘገባ ማግኘት አልተቻለም። በመኢአድ ጽ/ቤት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ የአንድነት ሊቀመንበር ንግግር እያደረጉ ነው። የፓርቲዎች የተናጥል ጉዞ የአምባገነኖችን እድሜ ያራዘመ ነው ሲሉ እንጂነር ግዛቸው አብሮ መስራት ድላን እንደሚያፋጥን ተናግረዋል። ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት / 4:00 PM በመኢአድ ጽ/ቤት አዳራሽ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፕሮግራም ሊጀመር ነው። የመኢአድና የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊዎች ስለ ፕሮግራሙ፣ አጠር ያለ ዘገባ አቅርበዋል። በቅድሚያ ከምርጫ 97 ወቅት በግፍ ለተገደሊ የሕሊና ጸሎይ ይደረጋል። ከዚያ የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዝቸው ሽፈራው ንግግር ካደረጉ በኋላ፣ የመኢአድ ሊቀምንበር አቶ አበባዉ ይቀጥላሉ። ከዚያም አደራዳሪዎች የቅድመ ዉህደቱን ሰንድ ይፈርሙና የድርጅቶቹ መሪዎች ፊርማቸውን ያኖራሉ። በመጨረሻ ከጋዜጠኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ። በአዳራሹ የተጠሩ እንግዶ፣ የፖለቲክ ድርጅት መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች ስፋራቸዉን ይዘዋል። ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት / 3:30 PM ናዝሬት/አዳማ ሰልፉ በድምቀት እየተካሄደ ነው። በርካታዎች ሰልፉን እየተቀላቀሉ ነው። ትልቅ የኔትዎርክ ችግር ግን አለ። በደብረ ማርቆስ በርካታዎች ሰልፉን እየተቀላቀሉ ነው። ብአዴን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በ እሁድ ቀን ሜካፕ ክላስ እንዲሰጣቸው መመሪያ በመስጠቱ ተማሪዎች ትምህርት አለ ተብለው ነበር። ካድሬዎች በየሰፈሩ እየሄዱ እውቅና ያገኘዉን ሰልፍ፣ ሰልፉ ሕገ ወጥ ነው፣ ረብሻ ይነሳል» እያሉ ሲያስፈራሩ ነበር። ነገር ግን እስከአሁን ድረስ ሰልፍ በሰለማ እየተደረገ ነው።፡ከተጠበቀዉ በላይ በርካታ ሕዝብ ተግኝቷል። ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት / 3:00 PM የአዳማው የተቃውሞ ሰልፍ መነሻውን ፖስታ ቤት አደባባይ አድርጎ በበቀለ ሞላ መንገድ አልፎ ወደ ቀይ መስቀል አቅንቶ በአስተዳደር ጽ/ቤት ዞሮ ሰልፉ በተጀመረበት ፖስታ ቤት አደባባይ ሰልፉ ይጠናቀቃል፡፡ አዳማ ያለውን ሰልፍ ለመዘገበ፣ የስልክ መስመር ከአዲስ አበባ አዳማ ማግኘት አልተቻለም። ኔትዎርክ እንጅሩ !!!!!! ዜናዎች እንዳገኝን እናሳወቃለን።፡ በደብረ ማርቆስ መፈክሮች እየተሰሙ ነው። ሰልፉ ደምቋል። የሕሊና እስረኞች በስም እየተጠሩ፣ በአስቸኳይ እንድፈቱ እየተጠየቀ ነው።፡«መብትን መጠየቅ ሽብርተኝነት አይደለም» እያሉ እነ አንድዋለም ጀግኖች እንጆ ሽብርተኞች እንዳልሆነ በመናገር ለሕሊና እስረኞች ያለዉን አጋርነት ሰልፈኛዉ እየተናገረ ነው። ከጠዋቱ 3:45 ሰዓት / 2፡45 PM በደብረ ማርቆስ ከሚታዩ መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡ «ሙስና የስርዓቱ መገለጫ ነው» «ዜጎችን ማፈናቀልና ማዋረድ ይቁም» «የኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና በአስቸኳይ ይቁም» «ልማትና ነጻነት አይነጣጠሉም» «የኑሮ ዉድነት የኢሕአዴግ ፖሊሲ ዉጤት ነው» «የኦሮሞ ተወላጆችን የገደሉ በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ» ከጠዋቱ 3:20 ሰዓት / 2፡30 PM ጁን 8 ዲሲ ሰዓት በደብረ ማርቆስም በአዳማም ሰልፉ ተጀምሯል። መፈክሮች እየተሰሙ ነው።«መብቱን መጠየቅ ሽብርተኝነት አይደለም !»፣ «ዉሸት ሰልችቶናል !» የደብረማርቆሱ የተቃውሞ ሰልፍ መነሻውን ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ አድርጎ፣ በአብማ ወደ መስቀል አደባባይ ያመራል። ለደብረማርቆስ ሰላማዊ ሰልፍ ከተዘጋጁት መፈክሮች አንዱ ይህን ይላል ከጠዋቱ 2:20 ሰዓት / 1፡20 PM ጁን 8 ዲሲ ሰዓት ነጻነት ! ነጻነት ! ነጻነት ! ቢሊሱማ ! ቢሊሱማ ቢሊሱም ! በድብረ ማርቆስና በአዳማ ሰልፉ ከአንድ ሁለት ሰዓት በኋላ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በዛሬዉ ቀን በመኢአድ ቢሮም ትልቅ ክስተት ይኖራል። አንጋፎቹ የአንድነት እና የመኢአድ ድርጅቶች ለመዋሃድ የቅድመ ዉህደት ፊርማ ይፈርማሉ። ያሏቸውን ጥቂት ልዩነቶች በዉይይትና በምክክር ፈተው፣ ወደ ዚህ ደረጃ መድረሳቸው በጣም ትልቅ ድል ነው። ከጠዋቱ 1 ሰዓት / 12፡00 PM ጁን 8 ዲሲ ሰዓት በቁጫ ወረዳ ሰልፍ ዛሬ ለማድረግ ዝግጅቶች ተደረጎ ነበር። ግን በዚያ ያሉ ካድሬዎችና ሃላፊዎች ህዝቡ ድምጹን የማሰማት መብቱ እንዳያከበር፣ እንቅፋት ፈጥረዋል። ከአዲስ አበባ የቅስቀሳ መኪና ና የተለያዩ የቅስቀሳ እቃዎችን ይዘው የሄዱ የአንድነት አባላት በወታደር ተከበው ከወረዳው ትላንት ማታ እንዲወጡ ተደርገዋል። ዳዊት ሰለሞን እንደዘገበው የዛሬዉን ሰልፍ በኃይል ካጨናገፉ በኋላ ሕዝብ በጣም መናገዱን የተረዱ የአካባቢው ባለስልጣናት ሰልፉ ለሚቀጥለው ሳምንት እንዲደረግ ጠይቀዋል። የአንድነት ፓርቲ በቁጫ ጉዳይ ላይ የሚያሳለፈዉን ዉሳኔ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንሰማለን። አንድ ነገር ግን እርግጥ የሆነው የቂጫ ወረዳ ሕዝብ ሕገ መንግስቱ የሚፈቅደለትን ድምጹን የማሰማት መብት ይጠቀማል። ዳዊት ሰለሞን ቁጫን በተመለክለተና የአዳማዉን እና የደብረ ማርቆስን ሰልፍ በተመለለተ የሚከትለውን ከሰባት ሰዓታት በፊት ጽፏል። «በብዙ ትግል የአዳማና ደብረማርቆስ አደባባዩች ነገ ተቃውሞ ይስተጋባባቸዋል የተለጠፉ ፖስተሮችን ከመቅደድ አንስቶ በቅስቀሳ ስራ የተሰማሩ አባላትን በማሰር በሁለቱ ከተሞች እንዲደረጉ የታቀዱ ‹‹ሰላማዊ››ሰልፎችን ለማክሸፍ የሰሩ ሃይሎች በስተመጨረሻ ህይወታቸውን ጭምር ለመስጠት በማይሳሱ ሰላማዊ ታጋዩች ጥንካሬ ድል በመመታታቸው ወደ ጎሬያቸው ለመግባት ተገደዋል፡፡ አሁን ከተሞቹ ለነገው ሰልፍ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቃቸው የሚጠበቀው የሰዓቱ መድረስ ብቻ ነው፡፡በቅስቀሳ ስራ ተሰማርተው የነበሩ አባት በነገው ሰልፍ የሚያዙ መፈክሮችን በማዘጋጀት ስራ ተጠምደዋል፡፡ህዝቡም የታፈነ ድምጹን በአንድነት በኩል ለማሰማት እየተዘጋጀ ነው፡፡በቁጫ አንድነት በተመሳሳይ ቀን ሊያደርገው የነበረ ሰልፍ ለቀጣይ ሳምንት እንዲተላለፍ የአካባቢው አስተዳደር መጠየቁ ተሰምቷል።» ከጠዋቱ 12 ሰዓት ሰኔ አንድ 2006 / 11፡00 PM ጁና 7 ዲሲ ሰዓት አሁን በደብረ ማርቆስና በአዳማ ነግቷል። ከጥቂት ሰዓት በኋላ ሰልፉ ይጀመራል። ላለፉት ሁለት ሶስት ቀናቶች በሁለቱ ከተሞች የነበረው ቅስቀሳ በጣም አስገራሚ ነበር። የአንድነት አስተባበሪዎችና ቀስቃሾች ከሕዝቡ ብዙ ማበረታታን ድጋፍ ሲሰሙ ነው ቀናቶቹን ያሳለፉት። በጣም የሚያስደስተው ደግሞ አብዛኛዉን የቅስቀሳና የዝግጅት ሥራ የሰሩት በአዳማ እና በደብረ ማርቆስ ያሉት የአንድነት አባላት ናቸው። የአንድነት ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ትልቅ ሥራ ነው የሰራዉ። ዜጎችን በክልላቸው እንዲህ አይነት ሥራ ሲሰሩ ማየት በጣም ያስደስታል።
↧