ትልቁ የኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ስበስብ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሽንጎ) የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት የሁኑት ፕሮፊሰር አቻምየለህ ደበላና ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እሁድ ግንቦት24 ቀን2006 (ጁን1፣2014) ፣በሲያትል(አሜሪካ) ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል።
በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ሁለቱም የሽንጎው ተወካዮች በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ፣ በሽንጎው ራዕይና እንቅሰስቃሴ እና በዜጎች ተሳትፎ ላይ ሰፊ ገለ ጻአድርገዋል። የፕሮፊሰር አቻምየለህ ደበላና የዶ/ር አክሎግ ቢራራን ገለጻ በማስከተልም ስፊ ጥያቄና መልስ እና አርኪ ውይይት ተካሂዷል።
ሸንጎ ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባዋችን በተለያዩ ሀገሮችና ከተሞች ውስጥ በማካሄድ በአለም ዙሪያ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ላይ የተደቀነውን አደጋ ለማስወገድ የሚስችል ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰቡን እንደሚቀጥል ታውቋል።
ከዚህም በተጨማሪ ሸንጎው ዲፕሎማቲክ እንቅስቃሴ በማካጠናከር ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ከፍተኛ ድጋፍን ለማስገኘት ሰፊ እንቅስቃሴ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
በስያትል የተካሄደውን ስብሰባ ላሰተባበሩ እንዲሁም በስብሰባው ላይ ለተገኙ ሁሉ ሽንጎ ምስጋናውን አቅርቦ፣ ይህ ትብብር ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እንደሚያደርግ ገልጧል። በሲያትል የኢትዮጵያ ወጣቶች ስብስብ፣ እንዲሁም ሞሲሊም ወገኖቻችን በተለይ ደግሞ ነጃሽ ጀስቲስ በመባል የሚታወቀው ድርጅት አባላት ላደረጉት ትብብር ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል።