ስለ HUMAN PAPILLOMAVIRUS መረጃ
የአባለዘር (Genital) human papillomavirus (HPV) በአሜሪካ በጣም የተለመደ፣ በአባለ ዘር ንክኪነት ምክንያት የሚተላለፍ በሽታ ነው። ወደ 100 ዐይነት የሆኑ HPV አሉ። አብዛኛዎቹ ተላላፊ በሽታዎች አንዳችም ዐይነት ምልክት የማያሳዩ እና በራሳቸው የሚጠፉ ናቸው። HPV በሴቶች፣ የማኅጸን ነቀርሳ (cervical cancer) የሚያስከ ትልና በጣም ዝቅተኛ በሆነ ሁኔታ በወንዶችና በሴቶች ጭምር በጣም ያልተለመደ ዐይነት ነቀርሳ ያስከትላል። በተጨማሪም በአባላ ዘር ላይ ኪንታሮት፣ እንዲሁም በላይኛው የእስትንፋስ ማስተላለፊያ ቧንቧችን (upper respiratory tract) እከክ መሰል ኪንታሮቶችን (warts) ያስከትላል። የ HPV በሽታ ምንም ዐይነት መድ ኃኒት የሌለው ሲሆን፣ የሚያስከትለው ችግር ግን በሕክምና ሊድን የሚችል ነው።
በዩኤስ በየዓመቱ ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ስዎች እና ወደ 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ተጨማሪ ሰዎች በበሽታው ይጠቃሉ። የ HPV በሽታ በግብረ ሥጋ ንክክ አማካይነት ይተላለፋል። ከ 50% ወይም እጅ በላይ የግብረ ሥጋ ተግባር ማካሄድ የሚያካሂዱ ወንዶችና ሴቶች በሕይወታቸው አንዴ በ HPV ጠንቅ ይለከፋሉ። በዩኤስ በየዓመቱ 12,000 ሴቶች የማኅጸን ነቀርሳ የሚይዛቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4,000 የሚሆኑት ሲሞቱ፣ ይህ የማኅጸን ነቀርሳ ተጠቂ ቁጥር ከብሔራዊው አማካይ መጠን በላይ በዲሲ ከፍ ብሎ ይገኛል።
ለ HPV በሽታ የሚሰጥ የመከላከያ ክትባት ሕይወት የሌለው (ሕያው ያልሆነ) ዐይነት ሆኖ ነገር ግን እንዲንሰራራ በማድረግ አራት ዋና የ HPV ተዋህስያንን ዐይነቶች የመከላከል ችሎታ አለው። እነዚህም 70% ወይም እጅ ያህል የማኅጸን ነቀርሳ የሚያስከትሉትን ሁለት ዐይነት እና እንዲሁም ወደ 90% ወይም እጅ የአባለ ዘር እከክ (genital warts) የሚያመጡትን ሁለት ዐይነት HPV ያካትታል። የHPV ክትባት አብዛኛውን የአባለዘር እከክ (genital warts) እና አብዛኛውን የማኅጸን ነቀርሳ (cervical cancer) ለመከላከል ያስችላል።
እነዚህ መከላከያዎች በሽታዎችን ለረጅም ጊዜ እንዲከላከሉ የሚጠበቁ ናቸው። ይሁን እንጂ የተከተቡ ሴቶችም ቢሆን የማኅጽን ነቀርሳ የማጣሪያ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት ክትባቱ የማኅጸን ነቀርሳ (cervical cancer) የሚያስከትሉን የ HPV ሁሉንም ጠንቆች የማይከላከል በመሆኑ ነው።
የ HPV ክትባት፣ የእድሜ ክልላቸው ከ 11-12 ዓመት ለሆኑ ታዳጊ ልጆች በየጊዜው የሚታዘዝ ሲሆን፣ እስከ 9 ዓመት እድሜ ላላቸው ልጆችም ቢሆን ሊታዘዝ ይችላል። ለወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች፣ በመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ንክክ ከመጀመራቸው በፊት፣ ለ HPV ተውሳክ ተጋልጠው ያልነበሩ በመሆናቸው የመጀመሪያቸው ከሆነው የግብረ ሥጋ ግንኙነታቸው በፊት የ HPV ክትባት ወስዶ መገኘት እጅግ ጠቃሚ ነው። ክትባቱ ከሁሉም ዐይነት የ HPV በሽታ ሳይሆን – ከጥቂት ዐይነት ይከላከላል። ሆኖም አንድ ወንድ ወይም ሴት ልጅ በ HPV ተውሳኮች በአንዱ ቀድሞውኑ ተይዘው የነበሩ ከሆነ ክትባቱ በሽታውን አያድንም። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን በ HPV በሽታ የተያዙ ወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች እንዲከተቡ ይመከራሉ። በተጨማሪም፣ የ HPV ክትባት በሴት ልጆች ላይ ከብልት ነቀርሳ በሽታ እና ሴት ልጅ ብልት ውጫዊው አካል ነቀርሳ (vulvar cancer) የሚከላከ ሲሆን፣ በሴቶች እና በወንዶች ልጆች ለሁለቱም ደግሞ ከአባለ ዘር እከክ (genital warts) እና የፊንጢጣ (anal cancer) ነቀርሳን ይከላከላል።
ክትባቱ በተጨማሪ እድሜአቸው ከ 13-26 ዓመት ለሆናቸው ሴቶች እና እንዲሁም ከ 13-21 እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወንዶች (ወይም በአንዳንድ ሁኔታ እስከ 26 ዓመት የሞላቸው) እና ከዚህ በፊት ወጣት በነበሩበት ዘመን ክትባቱን ሳይወስዱ የቀሩ ሁሉ እንዲወ ስዱ ይጠበቃል። ይህም ክትባት፣ አስፈላጊ ከሆኑ ከሌሎች ክትባቶች ጋር ሊሰጥ ይችላል።
የ HPV ክትባት እንደ ሦስት ተከታታይ ልከ መጠን ይሰጣል።
1ኛ ልከ መጠን፤ አሁን
2ተኛ ልከ መጠን፤ ከ 1ኛ ልከ መጠን ሁለት ወራት በኋላ
3ተኛ ልከ መጠን፤ ከ 1ኛ ልከ መጠን ስድስት ወራት በኋላ
ለሻጋታ ወይም ለእርሾ (yeast)፣ ለሕይወት አስጊ የሆነ አለርጂ ፣ ወይም ነፍሰ ጡር የሆኑ፣ ከመካከለኛ እስከ አስከፊ የሆነ በሽታ ያለባቸው ሁሉ መከተብ የለባቸውም። ክትባቱ የሚያስከትለው ጠንቅ አብዛኛውን ጊዜ ማሳከክን፣ ሕመምን፣ መርፌ በተወጉበት አካባቢ ላይ የሰውነት መቅላትን የመሳሰሉ ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ትኩሳት ያስከትላል።