በርከት ያላችሁ የዘ-ሐበሻ አንባቢያን ዛሬ በጉጉት እየተጠበቀ ያለውን የሚኒሶታውን ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ቀጣይ ሁኔታን የሚወስነውን ምርጫ በተመለከተ ‘ውጤቱ ምን ሆነ?’ ስትሉ በስልክ፣ በኢሜል እና በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች በጠየቃችሁን መሠረት የቤተክርስቲያኑ አሁን ያለበት ሁኔታን እነሆ።
በፍርድ ቤት በታዘዘው መሠረት ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንጠቃለል የሚለውም፤ እንደነበርነው በገለልተኛነት እንቆይ የሚለውም ወገን በድምጽ ብልጫ የቤተክርቲያኑን ሁኔታ ለመወሰን ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። ወደ 5 ፒኤም አካባቢም የድምጽ መስጠቱ ሂደት ተጠናቋል። የፍርድ ቤት ዳኛና ከሁለቱም ወገኖች የተወከሉ ሰዎች ባሉበት የድምጽ ቆጠራው እየተካሄደ ነው።
የድምጽ ቆጠራው ውጤት ዛሬ ማምሻውን ይለቀቅ፤ አይለቀቅ ዘ-ሐበሻ ያወቀችው ነገር ባይኖርም ውጤቱን እንደሰማን ለአንባቢዎቻችን እናቀርባለን።
በምርጫው ውስጥ ከተሳተፉ ወገኖች ለማረጋገጥ እንደቻልነው በሁለቱም ወገኖች የቆሙ ካህናት በየተቃራኒው ወገን ተቃውሞ ሲሰማባቸው ነበር።