ለረዥም ጊዜያት ሲያነጋግር የቆየው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ እንደነበረው በገለልተኛነቱ ይቆይ ወይም ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ይቀላቀል የሚለው ጉዳይ ምላሽ ሊያገኝ ሰዓታት በቀሩት በዚህ ሰዓት፤ ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንቀላቀል ከሚለውና ቤተክርስቲያኑን በጌታ ትንሣኤ ቀን ረግጠው ከወጡት ወገኖች የተወከለችው ጠበቃ የፊታችን እሁድ ሜይ 11 ቀን 2014 እንዲደረግ የተወሰነውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲታገድ ለፍርድ ቤት ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ሆነ።
ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲቀላቀል ከሚፈልገው ወገን የተወከለችው ጠበቃ ምርጫው ሊደረግ 11ኛው ሰዓት በቀረው ሰዓት ላይ እንዲህ ያለውን ጥያቄ ማቅረቧ ብዙዎችን አስገርሟል።
በዚህም መሠረት ወደ ሃገር ቤት ሲኖዶስ እንቀላቀል የሚለው ወገን በጠበቃው አማካኝነት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ በመደረጉ የፊታችን እሁድ የደብረ ሰላም መድሃኔዓለም ምርጫ በታቀደው መሠረት ይካሄዳል። ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ምዕመናን ሕዝብ በእሁዱ ምርጫ እንዲሳተፍና ቤተክርስቲያኒቱን እንዲያድን በተለያዩ መንገዶች እየበተነ ያለው ፍላየር የሚከተለው ነው።